ትህነግ ከፋይም፣ ከፋፋይም ነች! ( ጌታቸው ሽፈራው)

ትህነግ ከፋይም፣ ከፋፋይም ነች!

ፕሮፖጋንዳ፣ መወድስ፣………ለሚፅፉላት፣ በህዝብ ላይ ለሚፅሁፍት ጥሩ ክፍያ፣ እውነታውን ለሚፅሁፍ ደግሞ ዘብጥያ አዘጋጅታለች!

እነ እስክንድርን ዋጋ እያስከፈሉ ነቆራ፣ መወድስና አሉባልታ ሲፅፉ ለሚውሉት ፅንፈኛ ካድሬዎች እየከፈሏቸው ነው! ይህኔኮ ጠቀም ያለ ገንዘብ የሚሰጣቸው የአድዋ ሰፈር ልጆች ይሆናሉ!

በእኔ ግምት!

~ የተከፋዮችን ፅሁፍ “ሼር” እና “ታግ” አድርገው የሚያስነብቡ የአድዋ ሰፈር ፌስቡከኞች የ100 ብር ካርድ

~ ሸር አድርገው የሚያስነብቡ የዚሁ ሰፈር ልጆች የ75 ብር ካርድ

~ ከተከፋዮቹ ፅሁፍ ወይም ” የተቃዋሚ” ፅሁፍ ስር ስድብ፣ ዘለፋ… …እንዲሁም ትህነግን በማወደስ የፃፉ የ50 ብር ካርድ ( እንደስድብና መወድሱ ይዘት የሚጨመር ይሆናል)

~ like የምትለዋ ስር በፈገግታ፣ በማላገጥ…… ድርጅታዊ ተጋድሎ ያደረገ… … እንደተጋድሎው መጠን የሚጨመርለት ሆኖ 25 ብር የሚሞላላቸው ይመስለኛል።

~ ሁሉም እንደተጋድሎው መጠን ወደ እነ ዳንኤል እርከን የሚያድግበት እድል ይኖረዋል

~ ተመሳሳይ ስራ ለሚሰሩ የ”አጋር ድርጅት ካድሬዎች” ካርድ የሚሞላላቸው በውስጥ መስመር “ደግ አደረክ” ካሏቸው በቂ ነው። አንዳንዴ ስልክ ሲደዋወሉ “ቆይ እኔ ልደውልልህ” ብለው ይደውሉላቸዋል! አይበቃም?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.