በአዲግራት ከተማ ረብሻ: ስህተትን በስህተት ማረም አይቻልም #ግርማ_ካሳ

አሁን ከመሸ በአዲግራት ከተማ ረብሻ እንዳለ እየተሰማ ነው። በዚህ ሰዓት የተኩስ ድምፅ ያለማቋራጥ ይሰማል እያሉ ነው ተማሪዎች። የተወሰኑ ወጣቶች ዓላማቸው ባይታወቅም ወደ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዘልቀዋል እየተባለም ነው።

አክሱም ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎች ያለ ምግብና ውሃ ዶርም ቆልፈው ተቀምጠዋል። መቀሌ ዩኒቨርሲቲም ስጋት ላይ ናቸው።ተማሪዎች ደግሞ ወደ ቤተሰብ ለመሄድ ቢወስኑም መውጣት አልቻሉም።እናም ድረሱልን እያሉ ነው።

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በትግራይ የአማራ ተማሪዎች ላይ የሚፀመውን ጥቃት ድብደብና ማዋከብ በመቃወም ዛሬ ምሽት ወረቀት ሲበትኑ አምሽተዋል።

በመላዋ ሐገሪቱ እየሆነ ያለው የሚያሳዝን ነገር ነው። የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚይሳፍር ። ይሄም በቀጥታ የሕወሃትና ኦነግ የዘር ፖለቲክ ያመጣው ጣጣ ነው።

ወገኖች፡

ስህተትን በስህተት ማረም አይቻልም። እልህ፣ ቂም በቀል ለማንም አይበጅም። ወደ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ሁላችንም ተመልሰን ሰዉን በዘሩ ሳይሆን በስብናውና በኢትዮኦያዊነትኑ መመለከት ያስፈልጋል።

የትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራንና ብሎገሮች በትግራይ ክልል የተጀመረው ጸረ-አማራ ዘመቻና ጥቃት በአስችኳይ እንዲቆም ከፈተኛ ዘመቻ እንድታደርጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ሕወሃት የትግራይ ሕዝብ እንዲጠላ ያደረገው አንሶ ሌለ ጠባሳና ቁርሾ መጨመር አያስፈልግም። ከትግራይ ዉጭ ብዙ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉ መርሳት የለብንም። ዘረኝነቱና ጥላቻው ገደብና ልጓም ካልተደረገለት እሳቱ በየቦታው ሁሉንም ነው የሚበላው።፡

በአማራው ክልል ኖሮ የማያውቅ የጥላቻ መንፈስ እያየን ነው። ሕወሃት ማለት የትግራይ ህዝብ ማለት አይደለም። አንርሳ ሕወሃቶች የአማራው ክልል ካደረሱበት ግፍና ስቃይ በላይ ራሳቸው አማራ ነን የሚሉ ብአዴኖች ያደረሱት ግፍ ይበልጣል። በሁለት በሶስት እጥፍ። በመሆኑም ራሳችንን ለጥላቻ አሳልፈን መስጠት የለብንም።፡መታመም የለብንም። ዘረኘት በሸታ ነው።

አንድ ጊዜ በመቀሌ (ካሳ ተከለብርሃን ያለቀሰበት) የሕዝብ ለሕዝብ ጉባዬ ተደርጎ ነበር። በቅርቡ ደግሞ በጎንደር። ሆኖም ጥላቻው ዘረኝነቱ ጨመረ እንጅ አልቀነሰም። በመሆኑም ይሄ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል የለበጣና የተራ ፕሮፖጋንዳ ስራ ሳይሆን፣ ተጨባጭ ፣ ስር ነቀል የሆኑ ተግባራዊ ስራዎች መሰራት አለባቸው፡

1) የወልቃይት የኮሚቴ አባላትን ጨምሮ የታሰሩ የሕሊና እሰረኞች በሙሉ መፈታት አለባቸው።

2) የወልቃይት ጥያቄ ፍታዊ ምላሽ ማገኘት አለበት።፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.