የጎንደር ፣ ወልዲያ ፣ አዲግራት እና አክሱም ውሎ

ጎንደር፤

ቴወድሮስ እና ማራኪ ግቢወች ተማሪ መውጣት ተከልክሏል። መነሻው ወንድሞቻችን እየተገደሉ እና መውጫ አጥነው እኛ ልንማር አይገባም እሚል ነው። የኦሮሞ እና አማራ ተማሪወች ግፍ እና ግድያ ሊቆም ይገባ እሚል መፈክር ይዘው ተማሪወች ሰልፍ ወጥተዋል።

ቀበሌ 18 ቦሌ ጋርደን አካባቢ ከከተማው ወደ ቴወድሮስ እና ማራኪ ግቢ እሚወስደውን መንገድ ልዩ ኃይል ፖሊስ ዘግቶ ጭስ ቦንብ እየተኮሰ ነው።

~~~~~~
ወልዲያ

የትግራይ ተማሪዎች ተለይተው ወልዲያ ስታዲየም ውስጥ በአጋዚ እየተጠበቁ ነው። የቀረው ተማሪ ግቢ ውስጥ በአጋዚ እየተደበደበ ነው።
~~~~~~
አዲግራት

የተገደሉት የዐማራ ተማሪዎች ናቸው። በዚህም ምክንያት በርካታ ዐማራ እና ኦሮሞ ልጆች ታስረው እየተሰቃዩ ነው። አሁንም ድረስ ከፍተኛ ተከስ አለ። ተማሪዎች ከነጋ ምግብ አልቀረበላቸውም። ብጥብጡ በአዲስ መልክ ጀምሯል።

~~~~~~
አክሱም

በቀን 29/03/2010 በግቢው ” ባህል ማዕከል” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር በተሠበሠበው ተማሪ ላይ መነሻው የማይታወቅ ድንጋይ ውርወራ በመጀመሩ የተነሳ በተፈጠረ ግርግር አንድ ተማሪ ላይ አካላዊ ጉዳት ከደረሰ በኃላ ሊቆም ችሏል፡፡

ትናትናና ዛሬ የፀጥታ ኃይሎች በአቅራቢያ ቢገኙም ዋስትና ሊሆኑ አልቻሉም። ተማሪዎች ከግቢ መውጣት አይችሉም። ወደ ቤተሰብ ለመሄድ የሚፈልጉ ልጆች ታግደዋል።

MULUKEN TESFAW

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.