በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) የተላለፈ መልዕክት

የተከበራችሁ የአማራ ልጆችና የአማራ ወዳጆች፡-

በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው በደልና ሰቆቃ መልኩን እየቀያየረና መጠኑን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሰፋ አሁን ላይ እጅግ አሰቃቂ የሚባል ደረጃ ላይ ደርሷል። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ አፈናና ግድያው በተናከረ መልኩ ቀጥሏል። የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ለዚሁ ፀረ-አማራ ተልዕኮ ማስፈፀምያ ግንባር ቀደም በመሆን የአማራን ተማራዎች በግልም ይሁን በቡድን እያጠቁ ይገኛሉ። ይህንን በአማራ ተማሪዎች ላይ ያነጣጠረ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንቅስቃሴም ፀረ-አማራ ከሆኑ ተማሪዎች ባሻገር የተቋማቱ አመራሮችና የጥበቃ አባላት ጭምር እየተሳተፉበት እንደሚገኝ በአዲግራት ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ያለውን የተቀናጀ ድብደባና ግድያ እንደማሳያ ማንሳት ይቻላል። በተቋሙ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ደህንነት መጠበቅና ማስጠበቅ የዩኒቨርስቲው ሃላፊዎች ሆኖ ሳለ ተቋሙ ባለው የአማራ ህዝብ ጥላቻ ለአማራ ተማሪዎች ከለላና ጥበቃ ሳያደርግ በተቃራኒው ለድርጊቱ ተባባሪ ሆኖ ተገኝቷል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ውስጥም የተከሰተው ይህ ፀረ-አማራ እንቅስቃሴ የአማራ ተማሪዎችን ህይወት አሰከፍሏል። ተማሪዎቹም ከዮኒቨርስቲውም ሆነ ከሚመለከታቸው ተቋማት እርዳታ ያገኙበት ሁኔታም የለም። እውቀትን ለመሸመት ቀያቸውን ትተው የሄዱ ተማሪዎች የትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ሰነድ ይዘው ሳይሆን ሞተው የሚመለሱበት፣ የተረፉትም በከፍተኛ ድብደባ የጎደለ አካላቸውን ይዘው፣ ገሚሱም ለከፍተኛ የጤና ችግር ተዳርገው በቂ የህክምና ክትትል ሳይደረግላቸው ይገኛሉ። ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የአማራ ተማሪዎች ህይወት በግፍ አልፏል።

በደህንነት መሥርያ ቤቱ የሚደገፉ የትግሬ ተወላጅ ተማሪዎች በሚያስነሱት ብጥብጥ በመላ አገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች የጥቃት ዒላማ ተደርገዋል። ይህ ሁኔታም ሊሻሻልና ሊቆም የሚችልበት ምንም አይነት የህግ ስርዓት በአገሪቱ ላይ ባለመኖሩና በአሁኑ ሰዓት ይህ ፀረ-አማራ እንቅስቃሴ በመላው የትግራይ የትምህርት ተቋማት እየተዛመተና እየተስፋፋ መገኘቱ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅትን በእጅጉ ያሳስበዋል።

በመሆኑም በየትኛውም የትግራይ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ የአማራ ልጆች በተቻለ አቅም የተቋማቱን ግቢ እየለቀቁ በመውጣት አንፃራዊ ሰላም ወደሚያገኙበት የትውልድ ቀያቸው በመመልስ ያለአግባብና ያለፍትህ አማራ በመሆናቸው ብቻ የተነጠቁትን የመማር፣ የመዘዋወርና የመኖር መብት ከመላው የአማራ ህዝብ ጎን በመሆን መልሰው እንዲጎናፅፉ፣ ስለነፃነታቸው እንዲታገሉና የመኖር መብታቸውን እንዲያስከብሩ እናሳስባለን።

በመላው የሀገሪቱ ክፍል የሚገኝ የአማራ ህዝብም የሞት ሽረት ትግል የሚያደርጉበት ወሳኝ ሰዓት ላይ መሆኑን ተገንዝቦ ራሱን በአማራዊ አስተሳሰብ በማደራጀት እና በአካባቢው ያሉ ሚስጥራዊ አደራጀጀቶችን በመቀላቀል ለማይቀረው የነፃነት ትግል ራሱን እንዲያዘጋጅና በቁርጠኘነት እንዲታገል የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት መልዕክቱን ያስተላልፋል።

አማራ ያሸንፋል!!
የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.