አፍቃሪ ህወሃት ድህረ ገጽ፣ አይጋ ፎረም በኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰብ ዙሪያ አንድ ዘገባ አውጥቷል (ግርማ ካሳ)

አፍቃሪ ህወሃት ድህረ ገጽ፣ አይጋ ፎረም በኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰብ ዙሪያ አንድ ዘገባ አውጥቷል። አይጋ ፎረም ከኦህዴድና ከብአዴን የተወሰኑ አመራሮች ጠንካራ ተቃዉሞ እንዳቀረቡ ገልጾ “ማጆሪቲው” ግን የነርሱን ሐሳብ እንዳማይጋራ ነው ዘግቧል። በተለይም ከኦህዴድ አንድ አመራር “የሕወሃት የበላይነት አለ፣እኔና ሌሎች ተገለናል” የሚል ብሶት እንዳቀረበ የዘገበው አይጋ፣ ሌሎች የኦህዴድ አመራሮች ግን ይሄን ብሶት አቅራቢ አመራር የተናገረዉን እንዳልተቀበሉት ነው የጻፈው። ሲያክልም የሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ አሁን እየተነጋጋረ ያለው በግለሰቦች ብሶት ሳይሆን የጸረ-ፌዴራል ስርዓቱና ጸረ-ኢሕአዴግ አስተሳሰቦች እንዴት መዋጋት እንደሚቻል በሚለው ላይ እንደሆነ አይጋ ያትታል።

አይጋ “some current and former OPDO leaders” በሚል ብሶት አቅራቢ የኦህዴድ አመራርን የተቃወሙ ያላቸው፣ ከአሁኖቹ፣  እንደ ወርቅነህ ገበየሁ ያሉ ጥቂቶች ከነባሮቹ ደግሞ እነ ኩማ ደመቅሳ ያሉ ሊሆኑ እንደሚችል መገመት አያስቸግርም። እንጂ አብዛኛው የኦህዴድ አመራር አባላት ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።

ልክ እንደ አብዛኛው ኦህዴድ አብዛኛው ብአዴን ጠንካራ አቋም ያለው ስለመሆኑ ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም። የብአዴን ነገር ግራ የሚያጋባ ነው። ከኦህዴድ እነ ወርቅነህ ገበየሁን፣ ከብአዴን የተወሰኑትን፣ እንዲሁም ደሃዴኖችን በሙሉ ህወሃት ከጎኑ ማሰለፍ ከቻለ በኢሕአዴግ ውስጥ የማጆሪቲ ብሎክ ሆኖ ሊወጣ ይችላል።

በኢሕአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ውስጥ ከሕወሃት ዘጠኝ፣ ከድሃዴን ዘጠኝ፣ ከብአዴን ዘጠኝ፣ ከኦህዴድ ዘጠኝ አባላት ነው ያሉት። ኦህዴድና ብአዴን ግንባር ቢፈጥሩም ማጆሪቲ ሊሆኑ አይችሉም። 18 ድምጽ ነው የሚኖራቸው። ማጆሪቲ ለመሆን 19 ድምጽ ያስፈልጋል። ከኦህዴድ ወርቅነህ ገበየዉ ከብአዴን አለምነህ መኮንን የሕወሃት ደጋፊ እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። ስለዚህ ህወሃትና ድሃዴን አንድ ላይ ሆነው፣ ወርቅነህና አለምነህን ጨመረው 20 ድምጽ ይኖራቸዋል። ያ ማለት ማጆሪቲ ሆኑ ማለት ነው። እንግዲህ በዚህ መልኩ የተወሰነውን ዉሳኔ ሳይሆን አይቀርም አይጋ ማጆሪቲ ብሎ የሚያወራው።

ሆኖም ኦህዴድና ብአዴን በኢሕአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እነርሱ ውስጥ ባሉ ጥቂት ከሃዲዎች ምክንያት አብላጫ ሆነው ባይወጡም፣ ሌሎች ሁለት ሕጋዊ አማራጮች አሏቸው፡

– በፓርላማ ከ547 መቀመጫ ከ300 በላይ ድምጽ የብአዴን እና የኦህዴድ ነው። በመሆኑም የፓርላማውን መድረክ በመጠቀም ጠቅላይ ሚኒስትሩን በማባረር አዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር መሾም ይችላሉ። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተርም የደሀንነትና የመከላከያ መዋቅሩ ሊቀያየር ይችላል።

– ብአዴን እና ኦህዴድ ከኢሕአዴግ ውስጥ በመውጣት የራሳቸውን ግንባር መፍጠር ይችላሉ።

የአይጋ ዘገባ የሚከተለው ነው –

=====================

The News on Aigaforum reads as follows:

EPRDF Politics:Time of Reckoning Inline image 1
According to a reliable source the Executive Leadership is in do or die session so to speak! Although there were some disagreement from a strong minority on how to proceed the majority has prevailed and the meeting has started in earnest. According to our source a certain number from the OPDO and ANDM leadership were in the strong minority group while the rest were in the majority group. The meeting has started by listening to an individual leader grievances. According to our source the grievance heard so far was presented by former OPDO leader. His grievance was about TPLF supremacy and how he and his likes were marginalized. Our source told us even though TPLF leadership has admitted to some of their own weakness, most including some current and former OPDO leaders have disagreed with the assertion of the problem in Oromia is caused by TPLF supremacy!Our source told us the meeting is not all about individuals but about getting rid of the anti federalism and anti EPRDF thoughts that are being exhibited across the country. Apparently EPRDF is dead serious the current negative political developments are inspired by internal dissent. According to our source there will be noting that will not be addressed in this meeting.It is a make it or break it meeting and change is certain in many Federal and Regional institution! Aigaforum Dec 14, 2017

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.