ጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደቀደሙት አባቶቹ ታሪኩን በወያኔ መቃብር ላይ ያድሳል! (ከጎጃም ዓለም ዓቀፍ ትብብር)

ህወሃት ኢትዮጵያውያንን እርስ በእርስ ለማስተላለቅ ቆርጦ ተነስቷል። የትግራይ ተገንጣይ ቡድን – ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ለ40 ዓመት የዘረኝነት መርዙን ቢረጭበትም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን መከፋፈልን ተጸይፎ የህወሃትን ክፉ ዘረኛ ፖሊሲ መቃብር ባወረደበት ባሁኑ ሰዓት ያለ የሌለ ሃይሉን በመጠቀም የባርነት ቀንበሩን እንደገና በህዝቡ ላይ ለመጫን ያለረፍት ሲባዝን ይታያል። ባለፉት ጥቂት አመታት ህዝቡ ህወሃት ይውረድ እያለ በመላው ያገራችን ክፍሎች ህዝባዊ ተቃውሞውን ቀን ተቀን እያቀጣጠለው ይገኛል። ይህ ህዝባዊ ተቃውሞ ያስጨነቃቸው የህወሃት ጉጂሌ መሪዎች ህዝቡን እርስ በእርስ ለማጋጨት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ይህን ህዝብን የማጋጨት እኩይ ተግባራቸውን በተለየዩ ቦታዎች ሞክረው በጥቂት ቦታዎች ብቻ ቢሳካላቸውም በአብዛኛው በህዝቡና በአካባቢው ህዝባዊ ታጣቂ ሃይሎችና ለህዝብ በወገኑ አስተዳደር ሃላፊዎች ሊከሽፍባቸው ችሏል። ይህ ያበሳጫቸው የወያኔ ጎሰኛ መሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶችና ከፍተኛ ተቋማት ፊቱን በማዞር አገራችን ነው ብለው ለመማር በሄዱበት አድገው ያልጨረሱ ታዳጊ ተማሪዎችን በጅምላ እየቀጠፈ ይገኛል።

በተለይ ሰሞኑን በአዲግራት፤ በወልድያ፤ በደ/ታቦር፤ በአምቦና በተለያዩ የአገሪቱ ከፍተኛ ተቋሟት ወስጥ በወያኔ ነፍሰ ገዳዮች ለተገደሉት ኢትዮጵያውያን የተሰማን መሪር ሀዘን መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን። ከተማሪዎች በተጨማሪም በጨለንቆ ሰላማዊውን ህዝብ ኑ እንነጋገር ብለው ከሰበሰቡ በኋል ናዚዎች አይሁዶችን በአሽዊትዝ እንደፈጁት በሚመስል መልኩ ከሃያ በላይ ንጹሀን ኢትዮጵያውያንን በወያኔ አገልጋይ ወታደሮችና በትግሬ ወያኔ ድህንነቶች ቅንብር በጅምላ ተረሽነዋል። ይህን አረመኔአዊ እኩይ ተግባር በጥብቅ እያወገዝን ገዳዮች መቸውንም ቢሆን ከፍርድ እንደማያመልጡ አንጠራጠርም። ይህን አይነት በአለም የተከለከለን ዘር የማጥፋት ወንጀል ለማጋለጥ ይረዳን ዘንድ ህብረተሰቡ መረጃ በማቀበል እንዲተባበረን በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እናሳስባለን። ይህ ሁሉ የወገን እልቂት እየተካሄደ ያለው በወያኔ ጉጅሌ መሪዎች በቀጥታ እየታዘዙ መሆኑኑ እንረዳለን። እነዚህ የሞቱት ወገኖቻችን የትግሉ ሰማእታት ሲሆኑ ደማቸው በከንቱ  ፈሶ እንደማይቀር አንጠራጠርም። ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እየተመኘን በአንፃሩ በወያኔ በኩል ሌላውን በጅምላ እየገደሉ የኔ ለሚለው ለአንድ ትግሬ ብሄር ጥበቃ እና  ልዩ እንክብካቤ ያሳየው ከመጠን ያለፈ ማንአለብኝነት አገሪቱ በአንድ ቡድን ብቻ  እየተገዛች ለመሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ይህ መድሏዊ አፓርታይድ ስራዓት በፍጥነት ካልተወገደ መጪው ዘመን እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ያመላክታል።

ወያኔ ትግራይን ለመገንጠል ጫካ ከገባ ግዜ ጀምሮ ይዞት የተነሳው ዘርን መሰረት ያደረገ በተለይ አማራን እንደጠላት ፈርጀው መነሳታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። በዚህ እኩይ ተግባራቸው በለስ ቀንቷቸው ታላቂቷን ኢትዮጵያን ከተቆጣጠሩበት ግዜ ጀምሮ በቻሉት መንገድ ሁሉ ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት በተለይ አማራውን ነጥለው እንደጠላት ሲገድሉትና ሲያሳድዱት ኖረዋል። የተወሰኑ አካሎችም ይህንን ግፍ አንድነትን መሰረት ባላደረገ መልኩ ሲታገሉ የሚፈለገውን ያክል ውጤት ተገኝቶ ይህንን ዘረኛ ስርዓት ማስወገድ አልተቻለም። ሆኖም የስርአቱ ለከትየለሽ ግፍ ሞልቶ በመፍሰሱ የህዝቡ ትግል በየአቅጣጫው ላይቀለበስ ተቀጣጥሏል። ይህንን እልህ አስጨራሽና ከህፃን እስከ አዛውንት ህይወት እየተከፈለበት ያለ ትግል ፍፃሜ ያገኝ ዘንድ በአንድነት በማስተባበር እና በመምራት ወያኔን ከነሴራው እስከወዲያኛው ማስወገድ የሚመለከታቸው ሁሉ ግዴታ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

በተለያዩ ሃገሮች በታሪክ እንደምናውቀው ዘረኝነት ለሰው ልጅ ትልቁ የእልቂት መንስኤ ነው። በአገራችንም የዘረኝነት ፈጣሪ ትግሬ ወያኔንም ወደ መቃብር እየከተተው ነው። አበው ” በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም “ እንዳሉት ለአንድ አገር እድገት ትልቅ መሰረት በሆኑት ከፍተኛ ተቋሞች እንዲሁም በመላ የአገሪቱ ከተሞች እየታየ ያለው ህዝባዊ ማእበል ይህንን ያሳያል። የትምህርት ምኩራብ በሆኑ ዩኒቨርስቲዎች ለጋ ወጣቶች ከተለያዩ የአገራቸው ልጆች ጋር እንዳይገናኙ በዘር ሸንሽነው ያደራጁት ይህንን ልዩነት ይዘው እንዲያድጉና በጥላቻ ተለያይተው ለመገዛት እንዲመቹ ነበር። የወጣቶችን ትኩስ መንፈስና ስሜት ተጠቅመው የዘሩት ዘር ሙሉ በሙሉ ባያፈራም የሚያሳዝኑ ጉዳቶች ማድረሳቸው ግን አልቀረም። በነዚህ ዩኒቨርስቲዎች የሽማግሌው የስብሃት ነጋና የዘመዶቹ ልጆች፣ የአባይ ፀሃዬ፣ የስዩም መስፍን፣ የአርከበ እቁባይ፣ የጌታቸው አሰፋና የሌሎችም ዘራፊ ወያኔ ልጆች የሉም። እነሱማ አባቶቻቸውን ተክተው ልጆቻችንን ሊገዙ በቻይናና በምዕራቡ ዓለም ትልልቅ ትምህርት ቤቶች በተዘረፈ የህዝብ ሃብት ይማራሉ። ከፊሎችም በሀሺሽ ናውዘዋል። በየዩኒቨርስቲና ልዩ ልዩ ተቋማት ያላችሁ ወጣት ኢትዮጵያውያን ሆይ፤ እንደ እናንተ ባሉ ምስኪን ኢትዮጵያውያን ላይ እጃችሁን አታንሱ! ጥላቻን የዘራው፣ ተስፋችሁን ያጨለመው፤ የወያኔ ዘረኛ ስርዓት ነው።

ህወሃቶች ኢትዮጵያውያንን በየጎጣቸውና ጠባብ መንደራቸው ግርግም እንደገባ ክብት በአካባቢያቸው ተወስነው፣ የየክልሉ የወያኔ አሽከሮች ተሹመውባቸው፣ እንዳይንቀሳቀሱ ሲያግዱ ወያኔዎችና ቤተሰቦቻቸው መላ ኢትዮጵያን የመዝረፍ መብት ተጎናፅፈዋል። ለኦሮሞው አጥንቱን ከስክሶ ያስጠበቃት ኦጋዴን እንዳይኖርባት ሲገደልና በግማሽ ሚሊዮን የሚቆጠረው ሲፈናቀልባት እትዮጵያችን ለህወሃት ባለስልጣናት ግን የግላቸው እቃ ሆናለች። አማራው ከጠላት እየተዋደቀ እስከ ኦሜድላ ላስጠበቀው አገሩ ለጉቫ፣ ለዳንጉር፣ ለፓዊ ባዕድ ሆኖ እየተባረረ የባንዳ፤ የሹምባሽ ልጆች እንደ ቅኝ ገዢ ልዩ መብት አግኝተው መሬቱንና ማዕድኑን ያለማንም ከልካይ ይዘርፋል፤ አሶሳ ለኦሮሞውና ለአማራው ውጭ አገር ሆና ይመስል ይፈናቀልባታል፤ ጋምቤላን አኝዋኩ ጠብቆ መቆየቱ ሃጢያት ሆኖበት በመቶዎች ተገድሎ የተረፈው ተባርሮ የህወሃት ባለስልጣናት እና ዘመዶቻቸው በብቸኝነት ኢንቭስተር ሆነውበታል፤የምክር ቤት አባልም ሆነዋል። ጉራጌ ሠርቶ ያሳደጋት አዲስ አበባ ባዕዱ ሆና ከመርካቶ ተባርሮ እነሃጎስ ሱቆቹን የነጠቁት መሆኑን መናገር ሀቅ አንጂ ዘረኝነት አይደለም። ወድ አትዮጵያውያን – ይህን ጭቆና አይሉት ባርነት ዘረኛ ስራዓት በአንድላይ ተባብረን ልንጥለው ይገባል።

ቻይናና ወያኔ ከነዘመዶቹ የሚፏልሉባት የዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንዴት ለዜጎቿ አትሆንም? ሁሉም በጠባብ የዘር አጥር ውስጥ ታስሮ ወያኔና አገልጋዮቹ መላ አገሪቱን ሲዘርፉ ለምን ይፈቀዳል? የኦሮሞ ቄሮዎች፣ የአማራ ፋኖዎች የጠየቁት “እናንተ ማን ናችሁና ነው ሌሎችን አስራችሁ አገር የምትዘርፉት?” እያሉ ነው። በዚህም ሳያበቃ ለሶስት ዓመት በተካሄደው ህዝባዊ ትግል የተደናገጡትና የጌቶቻቸው አልጠረቃ ባይነት ያሳሰባቸው፣ አገልጋይነታችውም የሰለቻቸው ትግሬ ያልሆኑት የኢህአዴግ አባላት የህዝባቸውን ሮሮ ከመስማት አልፈው ወያኔን እየተገዳደሩ ይገኛል። ለህወሃት በኦሮምያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ ወዘተ    እንደወትሮው መዝረፍ ይቅርና መንቀሳቀስም እየከበዳቸው መጥቷል። በዚህም አያበቃም፤ የወያኔን አገዛዝ ህዝቡ በቃህ ስለአለው ፍፃሜው ቅርብ ነው። አርባ ኪሎሜትር ድንበር አልፎ የገባን የሱዳን ወታደር ተመለስ ማለት ፈጽሞ ያልፈለገው ወያኔ ብእርና ድብተር ብቻ የያዙትን የዩኒቨርስቲ ልጆች በመግደልና በሰደፍ በመቀጥቀጥ አገልጋይ ገረድ ሰራዊቱን በመጠቀም እድሜውን ለማራዘም ሲውተረተር ይታያል። ሰሞኑን በተለያዩ ያገሪቱ ዩንቨርስቲዎች የሟቾቹን ማንነትና በከፍተኛ ተደብድበው ለአካል ጉዳት የተዳረጉትን መረጃ እንድታቀብሉን ከወዲሁ ማሳወቅ እንወዳለን። “በሸንጎ ቢረታ ሚስቱን ገብቶ መታ” እንዲሉ። ህወህት የዘራውን የዘረኝነት መርዝ እንዲጋተው ይገደዳል ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ለረጅም ጊዜ በቆየ የአብሮነት ባህሉ ዘረኝነትን አርክሶታልና።

ውድ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፦ አሁን የተጀመረው የነጻነት ትግል ፍሬ እንዲያፈራ እርስ በእርስህ እየተባበርህ ጠላትህ ወያኔን ከመመከት አልፈህ አሳደህ ምታው እኛም ሁልግዜ ከጎንህ የማንለይ አገር ወዳድ ኢትይጵያውያን በሚፈለገው መጠን ትግልህን ለመርዳት ከመቸውም ግዜ በላይ ዝግጁ መሆናችንን ከወዲሁ እናረጋግጥልሃለን።

 

ወያኔ ይደመሰሳል!!

በወያኔ መቃብር ላይ እትዮጵያችን እንደገና ሃያል ሆና ትገነባለች!!

 ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

 

ጎጃም አለምአቀፍ ትብብር

 Gojjam Global Alliance

ጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደቀደሙት አባቶቹ ታሪኩን  በወያኔ መቃብር ላይ ያድሳል! (ከጎጃም ዓለም ዓቀፍ ትብብር)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.