በኢህአዴግ ውስጥ ያለው ክፍፍል ሊጠገን በማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል  – ናኦሚን በጋሻው

በኢህአዴግ ውስጥ ያለው ክፍፍል ሊጠገን በማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

• በስብሰባው ላይ የቀድሞ አመራሮቹን ማሳተፍን በተመለከት ውዝግብ ነበር። ለምሳሌ ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ እና በ 1993 ዓም የህወሃት ስንጠቃ ወቅት ገለል የተደጉት ጭምር እንዲሳተፉ በሕወሓት በኩል ተጠይቋል። ይሁን እንጂ የኦህዴዶቹ አቶ ለማ መገርሳ እና ዶ/ር አብይ አህመድ እንዲሁም ጓዶቻቸዉ ይህ የማይታሰብ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዉ በብዙ ማሳያ የታገዘ ሃሳባቸዉን አቅርበዋል።

• የአማራና የኦሮምያ ክልል ጋዜጠኞች በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገብተው ለመዘገብ መከልከላቸው ጥያቄ አስነስቷል።

• ያለ ክልላዊ መንግስት ጥሪና ፈቃድ የፌደራል መንግስት ጣልቃ እየገባ በተደጋጋሚ ህዝብ ላይ የሚፈፅመው ወንጀል ለችግሩ መባባስ ትልቁ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።

• የሕወሓት ተወካይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በኦህዴድ እና ብአዴን መቀራረብ ላይ ከባድ ትችት አቅርበዋል። ይህን ትችት ተከትሎ ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሯል። ኦህዴድ እና ብአዴን ረግጠው ወጥተው ነበር። ነባር የሚባሉት የቀድሞው አመራሮች ሸምግለዋል።

• ሕወሓት ተሓድሶ በማድረግ እነ አቶ አባይ ወልዱን ሲያነሳ አቶ ለማና አቶ ገዱ ግን አሁንም በስልጣን መሆናቸውን የሕወሓት ተወካዮች በተቃውሞ አንስተዋል።

• በችግሩ አፈታት እና መፍትሔ ዙሪያ ልዩነት አለ። በሕወሓት የቀረበው ጥቂት እስረኞችን መፍታት፣ አገር ቤት ከአሉ “ተቃዋሚዎች” ጋር መደራደር፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶችን ይዞ እርቅ ማካሄድ የሚል ሲሆን በዚህም ዙሪያ ልዩነቶች ተሰምተዋል።

• የልዩነት ፓለቲካ ይቅር ሁሉን አቀፍ ውይይት የሚል የቀረበ ሃሳብ ቀርቦ ውድቅ ሆኗል።

• በሕዋሓት የቀረበው አጋር ድርጅቶችን ከኢህአዴግ ጋር የማዋሃድ አጀንዳ ተቀባይነት አላገኘም።

• እስከአሁን ድረስ ያለው ለእያንዳንዱ አባል ድርጅቶች የተሰጠው ውክልና የህዝባቸውን ቁጥር ያላገናዘበ መሆኑን ኦህዴድ እና ብአዴን አንስተዋል።

• እነ ደብረጽዮን አሁን በአገሪቷ ዉስጥ የተፈጠረዉን ችግር “ጥቂት አመራሮች” ባሏቸዉ የኦህዴድ እና የብአዴን ጓዶች ላይ ለማላከክ ቢሞክሩም በአንፃሩ የኦህዴዱ ዶ/ር አብይ አህመድ እየተፈጠረ ላለዉ ቀዉስ ድብረጽዮን እና ጓደኞቻቸዉ ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ እንደነገሯቸዉ በዚህም ምክንያት ዉጥረት እንደነበር መረዳት ተችሏል።

• በስብሰባዉ እረፍት ሰአትም ኦህዴዶች ለብአዴን የልብልብ እንደሰጧቸዉና ለማ እና ዶ/ር አብይ ምን ቢደረጉ እንደሚሻል ህወሃቶች እና ጥቂት የደኢህዴን ሰዎች ይመካከሩ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.