የህሊና መሬት (ሥርጉተ ሥላሴ )

 

ከሥርጉተ ሥላሴ 20.12.2017 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።

„የተሰወረ ጥበብ እንደ ተሰወረ ወርቅ ነው። የሁለቱስ ጥቅማቸው ምንድን ነው? ጥበቡን ከሚሰውር አዋቂ ሰው፤ ስንፍናውን የሚሰውር ሰነፍ ሰው ይሻላል።“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፴ እስከ ፴፩)

 • መቅድም።
ሥርጉተ ሥላሴ

ዛሬ ከጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም አንድ ጹሑፍ አነበብኩኝ። „ትግራይ  በእውቀት እስክትራመድ…  ከፋሲል የኔዓለም http://www.zehabesha.com/amharic/?p=84015 ቀልቤንም ሳበው እና ከውስጤ ሆኜ አደመጥኩት። ብስል ዕይታ ነው። በዚህ መሰል የህሊናን መሬትን በጭብጥ ሃቅ የማልማት ተግባር ብንሰማራ ኖሯ ዛሬ ካለንበት ዕለታዊ የሃዘን ማቅ እንዲህ ችግሩም ሳይውጠን፤ መቅዘፊያችንም ሳይሰንፍ ወይንም ሳይደክም በቃችሁ ማለት ይቻል ነበር። ግን የተሰወረውን ውስጠ ወይራ መፍታት አቅቶን እንሆ 27 ዓመት ሆነ። ነገስ?

 • ብጡል።

በቅድሚያ ስለ ጋዜጠኛ ፋሲል የእኔአለም ያለኝን ዕይታ ገልጬ እሱ ባነሳቸው ነጥቦች ላይ የማጠናከሪያ ሃሳብ አቀርባለሁ። ግን እንዴት ሰነበትክ ወንድሜ።

እግረ መንግዴንም ከጋዜጠኛ ፋሲል የእኔአለም ያዬኋዋቸውን ቁም ነገሮች ዛሬ ማንሳት ፈለግሁ። አፃፃፉን በቅንነት ባለጉዳዮችም እነ ቤተ – ተጋሩ በአውንታዊነት ማዬት ይገባቸዋል የሚል ዕይታ ስላለኝ።  የመጀመሪያው ውስጡን ለማሳዬት ይደፍራል። ይህም በመሆኑ ቃለ ምልልስ ሲያደርግ እንደ ውስጡ ሆኖ ነው። የማይመቸውን ነገር ሳያቆላምጥ እንደ ወረደ ነው የሚያቀርበው። መበሳጨቱን ሳያለብስ ወይንም መመሰጡን ሳይሸፍን እንደ ተፈጥሮው። ሁለተኛው ቂም አያውቅም፤ ይህ በእኔ ያዬሁት ነው። እሱን በሃሳቡ በተከታታይ ሞግቸዋለሁ። ግን ቂም አልያዘብኝም። እንዲያው ወጣቶች አንደ ነገሩኝ የአኔን ጹሑፍ ሁሉ አንድ ቀን አዬር ላይ እንደዋለው ሰምቼለሁ። ይህን ሲነግሩኝ መገረም ብቻ ሳይሆን እንደ ነፃነት ትግሉ አቅም አድርጌ ነበር የተመለከትኩት። የሚያነስ ብዙ ነገር አለ። ሃሳብ መፍራት፤ ቅንነትን መፈታተን። ስለሆነም ፈተናውን በአጥጋቢ ውጤት አልፏል። መታደል ነው። ሌላው ትዕቢት የሚባል ቁራጭ ባህሪ የለበትም። በማናቸውም ጊዜ ባልገባችሁ ወይንም ቅር ባላችሁ ወይንም መረጃ ልተሰጡት ብትፈልጉ አክብሮ በትህትና መልስ ይሰጣል ያውም ውግዘ ተ – አርዮስ ለምትባለው ለሥርጉተ – ሥላሴ። እኔን እንደ ተፈጥሮዬ መቀበል የሁሉም ችግር ነው። እኔ ደግሞ እንደ ተፈጥሮዬ ለመኖር የፈቀድኩት ዛሬ ሳይሆነ ስፈጠር ነው። ቤተሰቦቼ ሳይቀሩ አያውቁትም ወይንም አይፈቅዱትም። እኔ ከተፈጥሮዬ ውጪ ልኑር ብል ደግሞ ፈጽሞ አያምርብኝም። እንዲያው አሁን ልቅበጥ፤ ቤት ውስጥ ሞቅ ያለ ድምጽ ላሰማ ብል፤ ወይንም ስሜቴን ደበቅ አድርጌ ልጻፍም ብል እበላሻለሁ። ስለሆነም ሥርጉተን ከነተፈጠሮዋ የተቀበለ ጋዜጠኛ ቢኖር ከቀደምት አናጋፋ አለቆቼ ውጪ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ነው። ይሄ ለእኔ የመንፈሴ መዳህኒት ነው። የጹሁፌ ታዳሚዎች የማከብራችሁ የሀገሬ ልጆች በውነቱ እኔ ከጋዜጠኛ ፋሲል ጋር የዘወትር ደንበኛ አይደለሁም። ግን ጥቂት ምልክቶቹን ስመረምር ውስጡን ተርጉመውልኛል። ስለሆነም ባለጉዳዮቹ እነ ቤተ – ታጋሩ የሰጠውን ሃሳብ በቅንነት ተመልክተው ራስን ለመለወጥ መትጋቱ አትራፊ መንገድ ሊሆናቸው ይችላል ብዬ አስባለሁ። „ተፈጥሮን ተመክሮ“ ካልሆነባቸው፤ … ተበደልንም እኮ ይላሉ¡

 • ህሊና።

በተረፈ „ትግራይ በእውቀት አስክትራመድ“ የሚለው እርእሱ 26 ዓመት አኮ አንድ ትውልድ ነው። ስለሆነም ወንድምዓለም ተራምዳለች ነው የሚባለው። ተቋም ሁናለች ነው የሚባለው። ሀገር ሆናለች ነው የሚባለው። እርምጃዋ በተለያዬ መንገድ በጥቂቱ ማዬት ይችላል። ለመነሻ እንሆ …

 • አንደኛው — ትግራይ ያለው የመማር ማስተማር ሂደት በልዩ ሁኔታ ታቅዶ ነው የሚከወነው። ግልብ ነገር ከዛ የለም። ማግስትን በሚያደራጅ ሙሉ እቅምና መሠረት በያዘ፤ ዘመኑን ባገናዘበ ሥልጡን ትልም እና ሁለገብ ብቃት ነው የሚከወነው። በኮንፒተር ተደግፈው እኮ ነው የሚማሩት። ዕወቀት የሀገር ባላ እና ወጋግራ ነው።
 • ሁለተኛው — ሌላ ቦታ ተወልደው ያደጉ የትግራይ ልጆችም ቢሆኑ ት/ቤት ሲሄዱ የተለዬ ሁኔታና አያያዝ ይጠብቃቸዋል፤ የቤተ መንግሥት ሰው ናቸው። ለዚህም ነው መታወቂያ ካርድ ላይ ብሄረሰብ አንዲጻፍ ቃለ ማንፌሰቶው የዘከረው። ይህ ስልት በቀጥታ ተጠቂውን ወደ ማጥቂያ መስምር ያስገባዋል። ያ ተጠቂ በቆይታው የብረት ቀንብር አንገቱ ላይ ተንጠልጥሎለት ሲሆን አያያዙም የዛያኑ ያህል በጭቆና እና በአድሎ የሰባ ነው። ልክ የጀርመኑ ናዚ ቤተ እስራኤሎችን ለጥቃት ሲያሰማራ መለያ ኮድ ይሰጣቸው እንደ ነበረው። ለእኛ ደግሞ ብሄረሰብ የመለያ ኮድ ነው። ይህም ብቻ አይደለም በሌሎች ብሄረሰቦች ዘንድም ተጠቂዎች ተነጠይ እንዲሆን ይደረጋል። መምህሩ ማህበረ ተጋሩ ከሆነ ደግሞ ሌላም ዲል ያለ ሰቀቀን ለተጠቂው ብሄረሰብ፤ ሞቅ ያለ አቀባበል ለንገሳዊው ይሆናል። በፈተና ማርክ አሰጣጡም ይህ ሂደት ለተጠቀሚው ካለሳንሱር የእንክብካቤ ይለፍ ያሰጠዋል። እንግዲህ ይሄ ከትግራይ ውጪ ነው። ትግራይ ላይ ደግሞ ለዛው ለንጉሣዊው ቤተሰብ ሳቢ፣ አጓጒ፤ ለሌላው ደግሞ የከረፋ፣ የሚጋፋ ጠረኑ የማያስቀርብ ጭቆና ይሆናል። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶው ሌላውን ዘር እያጠፋ የራሱን ዘር በአስተማማኝ ሁኔታ በሁሉም ሴክተር መሠረት የሚያስዝ ነው። አፈጻጸሙም የ አምክንዮ አቅም አለው። የስትራቴጂ ድክመት አይታይበትም።
 • ሦስተኛው — 26 ዓመት ሙሉ የትግራይ ተማሪዎች/ ትግራይ ላይ „ከባድም“ ጦርነት በስተቀር በሰላም እና በጸጥታ ውስጥ ሆነው ማደጋቸው እራሱ ሌላ የሥነ – ልቦና Self Confidence አቅም ለተማሪዎች ይፈጥራል። ከዚህ በላይ ኢትዮጵያን የሚመሩ፤ የሚገዙ ብቁ ፍጥረቶች ስለመሆናቸው፤ ዘራቸው የነጠረ ደም ስለመሆኑም ይነገራቸዋል ሳይሆን ይማሩታል። እንደ አንድ ሥርዓተ ትምህርት። በደነደነ፤ ሙሉ ልብ ነው ትምህርታቸውን የሚከታተሉት፤ ይህም በራሱ/ ሌላ ተጨማሪ በራስ የመተማመን extra Self Confidence ሁኔታ ይፈጥራል። እርግጥ አሁን እንደሚታዬው ከመጠን አልፏል። ማን ነክቶን? እንዴት ተደፍረን? ነው ያዬነው ከወልደያ ክስተት በኋዋላ ሆነ የባብር ሃዲዱን በሚመለከትም የነበረው አዬር እንደሚነግረን። ይህ ለወጣቶቹ አሉታዊነትም አለው። በማህበራዊ ሂደት፣ በትዳር ምሥረታ፤ በመኖሪያ አካባቢ፤ በሥራ ቦታ፤ በትምህርት ተቋማት የጠብ አጫሪነትን ናፋቂነትን ያመነጫል፤ ወጣቶችን ወደ ግትርነት እንዲሄዱ ይጋብዝ ይመስለኛል። በራስ መታማመን ከመጠን ካነሰ የበታችነት ስሜት ሲፈጠር፤ ከመጠን ካለፈ ደግሞ የማንአህሎኝነትን እብጠትን ይፈጥራል። አሁን ይህን የሚያመጣጥንላቸው ባለቤት ያገኙ አይመስለኝም ወጣቶች።
 • አራተኛው — በእስር ከቤተሰብ የሚነጠል፤ ከሥራ ተፈናቅሎ የሚበተን ቤተሰብ ትግራይ ውስጥ አለመኖሩ የቤተሰብ ሰላማዊ ህይወት ተጠብቋል። ማህበረሰብ የቤተሰብ መሰረት ነውና። በዚህ ሁኔታ ልንጽጽር የሚሆን ጭብጥ ባነሳ፤ የአንድነቱ የአቶ አንዱአለም አራጌ ልጆች፤ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ የጋዜጠኛ ውብሸት የሌሎችንም የፖለቲካ አስረኞች እና „የድምፃችን ይሰማ“ እስረኞች ልጆች፤ በዬቀኑ የሚገደሉት ወላጆች፤ ወደ እስር የሚጋዙት ወገኖች ልጆች ደግሞ በሥነ – ልቦና ተጠቂነት ሰለባ ሆኑ ከምል ጮርቃ ህሊናቸው ተቀጠቀጠ በመዶሻ ማለት ውስጤን ይገልጸዋል።  ቤተሰቡም ብቁ ዜጋ በማፍራት እረገድ የጎበጠ ሁኔታ ይገጥመዋል። አሁን ትግራይ ውስጥ የሚያድግ ልጅ በዚህም መስፈርት ስንሄድ ሰቆቃው አይነካቸውም። ሳቂተኞች ናቸው። እንደ ልጅ ይጫወታሉ፤ ይደሰታሉ። የልጅነት ጊዜ ታሪክም ይኖራቸዋል፤ በትምህርት ውጤታቸውም ከፍተኛ ይሆናል፤ 40 ዓመት ሙሉ ጦርነት እስከ አሁን ባልቆመባቸው በወሎ እና በስሜን ጎንደር፤ ከወያኔ ሥልጣን ማግስት ጀምሮ ደግሞ ባልተቋረጠ ሁኔታ ጋንቤላ፤ አሁን የሚታዬው በኢትዮጵያ ሱማሌ እና በኦሮምያ ድባቡ የመከራ ነው። ህፃናት የት/ ክ/ ጊዜያቸውን ሁሉ የድንኳን ሃዘንተኞች ሆነው ነው የሚያሳልፉት። ሳቅ አይኖራቸውም፤ ደስታ የራቃቸው ነው የሚሆኑት። ተስፋቸውም ጥውልግ ነው ጥንዙል። የትምህርት አቀባበላቸውም ተዛነፍ ይሆናል። ውጤታቸውም እንዲሁ ዝቅተኛ ይሆናል።… ሌላም ይህን መጠራቅቅ አልፈው ቢወጡ እንኳን በዬትምህርት ተቋሙ ሌላ የህሊና ካቴና ይጠብቃቸዋል። ት/ ሚር ለዚህ የተዛባ የአያያዝ እና የአዲሱ ትውልድ ኢ – ፍትሃዊ ቤተሰባዊ ሰቆቃ፤ ሚዛኑ ጠናና የሆነ የክት እና የዘወትር ልጅነት አበጅቷል። ሃላፊነቱን ጠንቅቆ ያልተወጣ ስልብ ድርጅት ነው። ወላጆች በሚደርስባቸው አፈና እና ወከባ ልጆች የመከራው ዓውራ ቤተሰብ ስለመሆናቸው አጀንዳው አድርጎት አያውቅም ት/ሚር። ሌላው ቀርቶ አሁን ዘንድሮ የአማራ ተማሪዎችን ትግራይ መላክ አልነበረበትም። ልክ እንደ ኦሮምያ ወጣቶች ወደ ኢትዮጵያ ሱማሊያ ክልል እንዳልሄዱት ሁሉ። በግዴለሽነት ላከ፤ አስገደለ። ጥበቃ ማስደረግ ለፈለገውም አደረገ። አማራ ከእሳር ወይንም ከእንጨት ነው የተፈጠረው።
 • አምስተኛው — ከቀዬው የሚፈናቀል ማህበረሰብ ትግራይ ውስጥ አለመኖር ሌላው ለልጆች የሥነ – ልቦና ጥበቃ የሚያደርግ መሰረታዊ ዋልታ ጉዳይ ነው። ተከታታይ የሆነ የሥነ – ልቦና አቅም ይፈጥርላቸዋል። በሌሎች የደረሰው መፈናቅል፤ ከመፈናቀሉ በኋዋላ የሚኖረው ህይወት ያልተረጋጋ እና በፍርሃት የተናጠ ስለመሆን ለዘላቂ ተስፋ ንጥረ ነገር ይጎድለዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን በነበሩበት ቀዬ የለመዱትን አዬር ስለሚነፈጉ የህሊና መጨናነቅ ሊደርስባቸውም ይችላሉ። ምናልባትም የጭንቀት በሽተኝነት።
 • ስድስተኛው — ሰፋፊ ለም መሬታቸው፤ ከጎንደር ከወሎ መወሰድ ይህ በራሱ የኤኮኖሚ አቅሙን ጉልበታም በማድረግ በመማር ማስተማሩ ሂደት ዘመናዊ እንዲሆን ከማድረጉ በላይ የጀግንነት ስሜትን ይፈጥራል፤ በተጨማሪም የዓለም አቀፍ ወሰን ደንበር ባለቤት መሆናቸው በድርብ ኩራት እንዲኮፈሱ ይረዳቸዋል። እንዲሁም ይህ መሬት የተወሰደባቸው ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ አርማጭሆ፤ ራያ ላይ የሚያድጉት ደግሞ በስጋት የተወጠረ ነፍስን ገና በጮርቃነታቸው እንዲያስተናግዱ መገደዳቸው ብቻም ሳይሆን በዬትም ሁኔታ በበታችነት ስሜት እና በባይታዋርነት መገረፋቸው፤ እንደ ራሳቸው ሆነው ለመኖር ፈቃድ ማጣታቸው፤ በመኖር ውስጥ ጎብጠው፤ ደንግጠውበት እንዲያድጉ የደርጋቸዋል። ከፍ ሰሉም ለእስር ይዳረጋሉ። በቀጣይ ህይወታቸውም በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ህይወት እንደ መጤ መታዬት፤ መገለል ስለሚገጥማቸው በጠሉት መኖር ውስጥ ራሳቸውን ቀብረው እንዲኖሩ ይገደዳሉ። መኖርን አጥብቀው ይፈሩታል። ይህ በራሱ ሌላም አስቸጋሪ ውጥረትን ይፈጥራል። እንደምንም ብለው ለአቅመ አዳም የመድረስ ዕድሉ ቢገጥማቸው ትዳር ለመመስረት የመንፈስ ድፍረት ያነሳቸዋል፤ በሥራም አካባቢ አቅማቸውን የሚፈታተኑ ረቂቅ የድፍረት ግብግብ ይገጥማቸዋል። ጠቅላላ ህይወታቸው በጭንቅ የተናጠ እና በድቀት የተወጠረ፤ የመከፋት አንባ ይሆናል።
 • ሰባተኛው — የቤተ ተጋሩ ልጆች ሀገር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ማግኘቱ የበለጠውን እጁ እንዲገኙ ያደርጋቸዋል። አዬሩ እራሱ ትግራይ ላይ በራሱ የተማመነ፣ ልበ ሙሉ የሆነ ሰብዕና ስለሆነ ይህ በልጆች ህይወት ላይ „አደርጋለሁ! እችላለሁ!“ የሚል ልዩ አቅም ስለሚፈጥር ብርታት እና ጥንካሬ ይሰጣቸዋል። ለዚህም ጥበቃ የሚያደርግላቸው የእኛ የሚሉት የትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት የትም ቦታ በተጠንቀቅ ዘባቸው መሆኑን በሚገባ እዬተነገራቸው ነው የሚያድጉት። ለእያያንዳንዱ ተማሪ የመንፈስ ዘበኛ ቁሞለታል። አሁን ባህርዳር ላይ፤ ወልድያ ላይ ጎንደር ላይ ፈጥኖ ነው የደረሰላቸው መንግሥታቸው። እዛ ያሉት የክልል ሃላፊዎች ደግሞ ክትትላቸው፤ ጥበቃ የሚያደርጉት ለባለ ጊዜዎች የመንግሥት ሠራዊት በሙሉ ሃይሉ ጥበቃ ለሚያድርገላቸው በተጨማሪነት፤ እንጂ ሜዳ ላይ ለወደቁት ኢትዮጵውያን ወታቶች አይደለም። ይህ በራሱ በወጣቶቹ ላይ የሚያሳድረው የሥነ -ልቦና ጥልቅ ተጽዕኖ ማግስትን እንዲጠሉት፤ መኖርን እንዲሸሸጉት ያደርጋቸዋል።
 • ስምንተኛው — ለቤተ ተጋሩ፣ ለባለ ዘመኖች የውጭ ዕድሉም ያን ያህል የበራ ዕጣ ፈንታ ነው ያላቸው። መስፈርቱን ባያሟሉ እንኳን ተደግፈው በእድሉ ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያድርጋቸዋል ዞጋቸው። የትምህርት ጊዜያቸው ያለፈባቸው ሳይቀር 12ኛ ክፍልን እኮ በሦስት ዓመት ዶክትሬት በ5 ዓመት የሚያገኙ እኮ ናቸው የትግራይ ልጆች። ይሄ እኮ በዓለም የትምህርት ሥርዓት ፈጽሞ ታስቦም የማያውቅ የጉድ ጉድጓድ ነው። ፊላንድ ያልሰማቸው ጉድ።
 • ዘጠንኛው — በዬትም የሚኖሩት የማህበረ ተጋሩ የባለቀኖች ልጆች ከተማ ላይ የተሻለ ይኖራሉ። የዲታ ልጆችም ከሆኑ ተከፍሎላቸው ውጪ መማራቸው ብቻ ሳይሆን እረፍት ጊዜያቸውን ሁሉ የሚያስልፉት እንደ ውሃ መንገድ በአውሮፕላን አገር ቤት በመመላለስ ነው። የትኛው ይናፍቃችኋዋል ሲባሉ እፍረት ስላልሰራለቸው „ሰቲት ሁመራ“ ይላሉ። ስለምን? መግደል የሚፈልጉት መንፈስ ስላለ። ሰቲት ለሥራ እንኳን የሚሄዱት ባለርስቶች ደግሞ ይታሳራሉ።
 • አስረኛው — የወርቅ ዘሮች እነ ቅምጥልጥል የሌላ ሀገር ዜግነትን ለማግኘት ነፍሰጡር እናቶቻቸው ጥቂት የማይባሉ የሥርዓቱ ብልጫ ተጠቃሚዎች የሚወልዱት ውጪ አገር ሄደው ነው። ስለሆነም አስተማማኝ የነገ ቀንም አላቸው። ማግሥት በመዳፋቸው ነው። የፈለገ አይነት ለውጥ ቢመጣ ኑሮን በታቀደ ሁኔታ ተጠብበውበታል። እንብልጣለን ቢሉ ይገባቸዋል። ተኝቶ በለኝ የሚለው የኢትዮጵያ የነፃነት ፖለቲካ ነው።
 • አስረአንደኛው — የኢትዮጵያ ዲያመንዶች የነተጋሩ ሽሙንሙኖች ከተማሩ፤ ከተመረቁ በኋዋላ የተሻለ የሥራ ዕድል ያገኛሉ። አዬር መንግድ በሙሉ እነሱ ናቸው። እንኳንስ የተማሩት ያልተማሩት አዛውንቶች አሁን በፊልም ኢንደስትሪ የተወረረ እስኪመስል ድረስ እነሱው ናቸው። ኤቲክሱ የሙያው ሥነ-ምግባር ሳይሆን ዞጋቸው ከበቂ በላይ መስፈርቱን ያሟላል። ይሄ የፊልም ዳይሬክትር፤ የፕሮዳክሽን ሠራተኛ ሁሉ እንደ ኦክስጅን ማህበረ ተጋሩን ካለቀሰሰ አይሞቅም፤ አይደምቅም። ቅድሚያ ነው። ጸጋው ያላቸው ቢሆኑ የሀገር ልጆች ናቸው፤ ግን ሂደቱ ልክ እንደ ትምህርት ዘርፍ ላሽቋል ልበለው። አስቲ ጊዜው ከኖረ „አሜን“ አዲስ ተከታታይ ፊልም ነው እዬት እና ለኩት።
 • አስራሁለተኛው —- በሥነ ጥበብ ዘርፍ፤ በሚዲያ፤ በፊልም ሥራ ከላይ እንደጠቃቀስኩት የተጠና ተግባር ይከውናሉ። ፊልምን ውሰዱት አራስ ልጅ ሲያስፈልግ የትግሬ ልጅ ነው፤ ህጻንም ሲያስፈልግ የትግሬ ልጅ ነው። እግረ ተከልም ሲያስፈልግ ተጋሩ ነው፤ ታዳጊም ወጣትም እንዲሁ ቤተ ተጋሩ ነው። ወጣቱ ሙሉ ለሙሉ ማለት እስኪያስችል ድረስ ያው የምርጥ ዘር ማህበር ነው። ሌላው ቀርቶ ለአንድ የማሟሟቂያ አፍታዊ ፕሮዳክሽን ሙሉው ተጋሩ ነው። ይህን ስታዩት ምን ያህል ሁሉንም ቦታ በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉት ማዬት ይቻላል። ይሄም ብቻ አይደለም የዕድሜ ተከታታይነቱን በውርስ እንዲቀጥል መሰረት አስይዘው ነው የጀመሩት። እኔ ፊልም አያለሁ – ስለመወድም። በተጨማሪም ኑሮ በኢትዮጵያን ለማዬት ልዩ መስታውት ነው። መረጃም አገኛለሁ። ወንጀል ላይ ጭካኔያቸውን ታዩት አላችሁ፤ በዬፊልሙ ሁሉ እነሱን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶውን ከነ ሙሉ ቁመናው ማስተዋል ይቻላል። አሁን „ዘመን“ ላይ ሴት ልጅ በምስማር እጇ ሲነደል /ማስመስልም/ ቢሆን መንፈሱ የሚልከው መልዕክት አለው። ፊልም የዕውነተኛውም ዓለም ግልባጭ ነው። ሥነ ጥበብ የህይወት መስተዋት ነው። የሆነ ሆኖ በሥነ – ጥበብ ዘርፍ አብሶ ትወና ላይ ትውልዱን መሰረት ባለው ሁኔታ እየገነቡት ነው። ተዉ ባይም የለም። የእነሱ ሂደት በብልህነት እዬከወኑት ያለውን ኢትዮጵያን አክስሞ ወይንም፤ አልሞ የታላቋ ትግራይ የምስረታ ጉዞ በጸና መሰረት መገንባት ነው። እርግጥ ኢንደስትሪው ጎጥ አምላኪ ብቻ ሳይሆን ጣዕምና ለዛ አሳጥተውታል። ኪነ – ጥበብ ተስጥዖ ነው። የሰማይ ስጦታ። የድምጹ ቃና እራሱ አንዳንድ ጊዜ አይደለም ለሰው ልጅ ጆሮ ድንጋይ እራሱ አታደንቁረኝ እንዲል ያሰኘዋል። እንጨት ነው። ወዙ የተመጠጠ ነው። የአሮጌ ቆርቆሮ ጩኸት፤ የጎረይና ቃና ነው የሚደመጠው። እንደስትሪውን እራሱ በቁሙ ገድሎታል – ዞግ ስለሚመራው። እርግጥ አጋጣሚውን ካገኙ በኋዋላ በጥረታቸው ጠረናቸው ሳቢ መሆን የቻሉ አሉ ድንቆች አሉ። እኔ ራሴ የምወዳቸው – የማደንቃቸውም። ገጠርኛውም ሆነ በከተሜው ሲሰሩ ውበት ያላቸው አሉ። ግን ዞጉ የታጨቅበት መሆኑ ግን በእውነቱ የሙያው ክህሎት ዲያሪክተር ያለህ ያሰኛል። ኪነ-ጥበብ ጎጣዊ ሲሆን መስፈርቱ ከፈጣሪ ጋርም መጣላት ይመስለኛል። የኪነ – ጥበብ ውበቱ ሰማያዊነቱን እራሱ አማኑኤል በኪናዊ ጥበቡ ሠርቷታል። ያ ነው የተሰረዘው፤ ያ ነው የተደለዘው። ሃጢያት ይመስለኛል። ክህሎተ – እግዚአብሄርንም የተዳፈረ እርምጃ ነው። አንዲት ወጣኒት የቅኔውን ልዑል የብላቴን የቅኔ እጬጌ አውርዳ ከፎቅ ላይ ትፈጠፍጠዋለች፤ እንዳሻት ታንከረባብሰዋለች። ከመጠን ያለፈው በራስ የመተማማን ስሜት የፈጠረው አቅም አግዝፎ የማየት ችግር ይመስለኛል። አልተገሩም። አሁን የብላቴ ሥን – ግጥሞች ቃለ ወንጌል ናቸው። እኔ አመልክባቸውአለሁ። አንዳንድ ጊዜም አማርኛው እራሱ ከሌላ ቋንቋ የመጣ ነው ይመስላል፤ ከመጠበቡ ከመርቀቁ የተነሳ ተፈጥሮው። ከልጅነቴ ጀምሮ አነበዋለሁ፤ ግን ሁልጊዜም አዲስ እጅግም ፈተኝ፤ በተጫማሪም ከባድ ነው። የቅኔው ልቅና የታቦት ያህል ነው። ይህን ነው ካለልክ የሚዳፈሩት። ሌላውንም ሙያ እንዲሁ። መብት በገፍ ነው ግዴታ ደግሞ በመቁንን። የራስ መተማመኑ ደግሞ ጣሪያ ነክ።
 • እስራሦስተኛው —- ፋሽን ኢንደስትሪም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚዩው። የውበት መግለጫ የሆኑ ደሞች አሉ፤ እነዛ ዞጋዊ ሆነው ነው በመዛኙ የሚታየው። ደመ – ገብ፤ ዓይነ ገብ፤ ካሜራ የሚወዳቸው፤ ካሜራ የሚሳሳላቸው፤ ካሜራ የማይጠግባቸው፤ ለካሜራ ብዙ ጊዜ የማይፈጅበት ተፈጥሮ እያለ፤ ግን በዚህ መንገድ ኢንደስትሪው የታደለ አይደለም ተጋሩ መሆን ብቻ ይበቃል … እርግጥ በውድድር የተጀመረው ጥረት ያበረታታል፤ ከዚህ ውጪ ያለው ግን መንፈሱ ዞጋዊ ነው።
 • አስረአራተኛው —- የማስታወቂያ ዕድልም ከነገስታቱ ዘር ውጪ አይደፈርም። ምክንያቱም ብዙውን የባላሃብት ቦታ የያዙት እነሱ መሆናቸው ብቻ እድሉን የሚሰጡት ለራሳቸው ዞግ ነው። ሌላውም ማሸብሸብ ስለሚፈልግ፤ የታይታ ነገር ስለሚወድ፤ ከንቱ ውዳሴም ስለሚገዛው ዓይኑ የሚያርፈው ከትግራይ ላይ ነው። ጉቦ ነዋ። በስተቀር ሰበብ ተፈልጎ ይከረቸምበታል። ወይ ደግሞ ከገቢያ ውጭ ይሆናል።
 • አስራምስተኛው ማናቸውም ውድድሮች እንደምንም ብለው ትግራይን ማስገባት አለባቸው። በስተቀር ስፖንሰር አያገኙም። ሲወድቁ እንኳን አንዱ ዲታ ብድግ ብሎ ምክንያት ፈልጎ ሌላውን ቅስም በሚሰብር መልኩ በሺ የሚቆጠር ገንዘብ መድረክ ላይ ወጥቶ ይሸልማል። ያልተሸለሙት ግን እኩል የወደቁት ለዘለዓለም በህሊናቸው ጠበሳ ተሸክመው እንዲኖር ይገዳደሉ ዘረኝነቱን የሚገልጽ ቃል የለኝም፤ በተለይ ይሄ ለወጣት ሴት ተዋንይ እጅግ ፈታኝ ነው። የኢትዮጵያ ልጆች ተንከባካቢ የላቸውም፤ ከለላ የላቸውም። ጠበቂ የላቸውም – ቢያንስ ለሥነ ልቦናቸው እኔ ሳያቸው ልክ እንደ እኔ በሀገራቸው ስደተኛ መሆናቸው ያቃጥለኛል። እነ ተጋሩ ደግሞ ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ ናቸው። ቀብረር ብለው፤ ኮራ ደልድል ብለው ለዛውም ተለመንው በሁሉም ቦታ ይንጎራደዳሉ።
 • አስራስድስተኛው — በተስጥዖ መስክ፤ ተስጥዖ ዛሬ ጎሳ ነው። በሚደያ መስራት ዛሬ ማህያውም ከፍ ያለ ነው። የሚገርመው ፕሮግራሙ መሪዎች ተጋሩ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፤ ተጋባዦችም ተጋሮዎች ናቸው፤ ተወዳድረው ሲያሸንፉም ሲሸለሙም እነሱው ናቸው። ይሄ ሂደት የተጋሩን ተናጠላዊ ብቻ ሳይሆን ወላዊ የሆነ የውስጥ መስምር በመዘርጋት እረገድ ዘመን የማሽረው ሃዲድ ገንብቷል።
 • ከዚህ ጋር አያይዘው ተጽዕኖ ፈጣሪ ማህበረሰብ በመፍጠርም ተግተው እየሠሩ ነው። አሁን ባለፈው አንዲት አርቲስት ሄለን በርሄ ክሊፕ በተባባሩት መንግሥታት የሴቶች ጉዳይ „ከጣይቱ“ ልቆ ዕውቅና ማግኘቱን አንብቤያለሁ። በሴቶችም ጉዳይ ዓለም ዓቀፍ ሁነቶችን ስለመክተታል። እነሱ ደክሞናል እረፍት እንውሰድ ያሉበት ጊዜ የለም። ሂደቶችን በጥሞና የማንከታትል ስለሚመስላቸው ነው ሊሂቃኑ እና በተጫማሪም አሽቃባጩ የሆኑ ወገኖች ትግራይ ምን ተጠቅማ? ደሃው ገበሬ እንደ ሌላው ነው? የሚሉን በ26 ዓመት ከዚህ ከተደረሰ በቀጣይ በመንገድ ያሉም የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በውጭም በሀገር ውስጥም አሉ፤ ወደ ዩንቨርስቲ ሊገቡ የተሰናዱትን ጨምሮ የት ሊደረስ እንደሚችል ይህ ጣሪያ የነካ፤ የሚጥለቀልቅ ነው የሚሆነው አስተውሉ ከ5%። ሁሉን ያለሳተፈ፤ ሚዛኑን ይልጠበቀ ጉዞ ወደፊትም ከዚህ በእጥፍ ድርብ ሊገጥም እንደሚችል ግምት ውስጥ ማስገባት ይገባል። ምክንያቱም ሂደቱ ገና አላለቀም። አንድ ዘርፍ ወይንም ሁለት ዘርፍ አይደለም በጠቅላላ ነው፤ የቀረ መሬት የለም። የቀረ የህሊና መሬት ሳይቀር ተወሯል። ተዘርፏል።
 • አስራሰባተኛው — እራሱ በስፖርት ዘርፍ ሙሉ አቅም ያለው ትውልድ ለመገንባት ጥረቱ አንቱ ነው። ከትግራይ እኮ ሴት አትሌቶችን ሳይቀር እያዬን ነው። ሌላው ደግሞ ማትሪክ እዬተጠበቀ በጥይት ይነዳል – ጎንደር።
 • አስራስምንተኛው —- አሁን በግላጭ የምናያቸውን ቅንጣት ክስተቶች ናቸው፤ ያውም ዩቱብ ላይ የተቀረጸ፤ የማናውቀው፤ በረጅሙ የተጀመሩ ውጥኖች ደግሞ አፍሪካንም የሚያድርስ ነው 5%። በዬዓመቱ ምርጥ ልጆች ብቅ ይላሉ። አብሶ የትምህርት ሂደት አሁን ያለውን ብቻ ሳይሆን ትምህርት የረጅም ጊዜ ሂደት ውጤት ስለሆነ ነገም መንገዱ በእጥፍ ድርብርብ የቀና፤ አትራፊ አስተማማኝም አድርገው ገንብተውታል። ስለሆነም ምርጥ ደምን በእውቀት ላይ የተገነባ እንዲሆን ማደረጋቸው የተነሱበት መሰረታዊ ዓላማ ነው። ቢመኩም ይገባቸዋል። ሌት ተቀን ነው ሳይታክቱ የሚተጉት። ዓላማቸውን ለማስፈጸም ደግሞ ይህ ሂደት ተደናቅፎ ተፎካካሪ ጥያቄዎች እንዳያስነሳ የተጠቀሙበት ወሳኝ ስልት አላቸው። መነሻቸውም ሆነ መድረሻቸውን ሽዋን መተካት ነው። በሽዋ ውስጥ ጉራጌ እና ኦሮሞ አለ። ይህቺ ግን ተከድና የኖረች አሁን የፈነዳች ገመናቸው ናት። ሽዋ አማራው ብቻ ሳይሆን ሽዌው ማዕከላዊ መንግሥት ስለነበረበት በሁሉም ቦታ ቀዳሚ ሥፍራ ነበረው በቀደመው ጊዜ ብለው ያምናሉ። ስለዚህ ኩርኩሙ አማራ ላይ ይሁን እንጂ ሳያስጠጡ ኦሮሞውም፤ ጉራጌውም ተመስጥሮ ተደቁሷል በጥቂቱም ቢሆን።

የተፈጥሮ ጀሶ ያነሳቸው ዕሳቤዎች።

የወያኔ ሃርነት ትግራይ የታላቋን ትግራይን ህልም ይዞ ሲነሳ መሰረታዊ ዓላማው „በአማራ መቃብር ላይ ታላቋን የትግራይ ሪፓብሊክን እመሰርታለሁ“ ብሎ ነው። በ2008 እ.አ.አ የወጣው የሚስጢር ሰነድ እንደሚያሰረዳው „የሽዋ አማራን“ ዒላማ ያደረገ ነው። ይህም ሽዋ የትግራይን ሥርዕዎ መንግሥት ተቀናቃኝ ነው ከሚል ዕሳቤ የፈለቀ ነው። ለእኛ ሊሆን የሚገባውን የሥርዕዎ መንግሥት ቦታ ወስዷል ነው የተጋሩ ዶግማ። ከወሰደም በሀዋላ እኛን ጨቁኗል፤ አግልሎናል ነው የበቀሉ ዋንጫ። የመጨቆኛ መሳሪያው ደግሞ ሽዋ ለቤተ-መንግሥቱ ቅርብ መሆን ነው። የሽዋ ተወላጆች ሲሉ አማራውን ነጥለው በማውጣት ነበር። ጉራጌውና ኦሮሞውን አንስተውት አያውቁም። የፖለቲካ ሊቁም የሽዋ አማራ ሲባል ሽንፍንፍኑን ፈልፍሎ ማዬት አልፈቀደም። ስህተትቱ ከዚህ ላይ ነው። በፈረቃ ነው የወያኔ የጦርነት ግንብር ነጋሪት የሚጎስመው። ይህ ስለተባለ ኦሮሞን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጎኑ ማሰለፍ ቻለ። ፍተሻ የለም። ጥርጣሬ እንኳን። አይደለም ትናንት አሁን በዚህ ሙግት ሲገጥሙ ይገርመኛል።

ስለሆነም አይዋ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከድሉ እርከን እስኪደርስ ድረስ የመንፈስ ጥሪት ማዳበሪያ ያስፈልገው ስለነበረ፤ ኦሮሞን  በአማራ ላይ አስነሳ። ይህን ለማድረግ ሻብያም ከዚህ መንፈስ ስለሚነሳ ጠረኑን ተጋራ። ለአፈጻጻሙም ተጋ። ይህን ለመጠቀም ጥርጊውን የሚያመቻችለት ብሂል አጠና። ቋንቋውን ለዬ። ትግራይ ላይ አማርኛ አንድ የእውቀት ዘርፍ ነው። ኦሮሞ ላይ ግን የጥላቻ ግንብ ተገነባ። ኤርትራዊ ጸሐፊም ተዘጋጀ። „ኦሮሞ ኢትዮጵያ የአንተ አልነበረችም፤ የተሰዋህው፤ ታሪክ የሰራኸው ለአማራ ንግሥና ብቻ ነው። እንዲያውም አማራ ማንነትህን ድጦ፤ ውጦም ግፍ ፈጽሞብሃል፤ አንተ የእኔ የምትለው ምን አለህ ባህልህ ቋነቋህን፤ ወግህን ልማድህ አምንትህን ተነጥቀሃል?“ ልብ የሚነካ ነው። እኔ ደግሞ በቋንቋህ እንድትማር የፈለግከውን ታደርግ ዘንድ እፈቅድልሃለሁ፤ ወረቀት ላይ ቢሆን መገንጠልን ዓውጄልሃለሁ፤ ፍሬም ውስጥ ዓዋጁን ካስቀመጥከው ይበቃሃል“ በኢህዴግም ውስጥ አንተም 11 ወንበር እኔም በለ 5% ከአንተ እኩል ተሰልፌያለሁ“ ሳያቅማማ፤ ሳይከራከር አምኖ ተቀበለ። አብሮ አህዱ አለ።  አሁን ሰፊ የሆነ የህሊና መሬት ከላ ሊዝ አገኘ በኦሮሞ ሊሂቃኑ ዘንድ ሐሤት ሆነ። ሊሂቃኑም ጫካ እያሉ ባልተመቸ ሁኔታ የሠሩበትን በህጋዊ መድርክ ሠሩበት። ትውልዱን በዚህ ዶክትሪን ኮትኩተው አሳደጉ። ይሄ ልዕለ መሠረት የሆነ አምክንዮ ከአድዋ ድል በላይ ለታላቁ ትግራይ ጸጥ ባለ መስመር መርሃ ግብሩን ለመከወን ያስቻለው ልባም ስትራቴጂው ነው። ይህን ማህረሰብ ኦሮሞን ከራሱ ልቅና፤ ከራሱ የፈጠራ አቅም፤ ከራሱ ውረሰ ጽናት፤ ከራሱ አኩሪ ዝልቅ የማድረግ አቅም አውጥቶ ለእሱ ስውር ፍላጎት ማስፈጸም እንዲችል በሥሩ ጠቅልሎ አልጋ ስር ሰወረው። ጦርነቱ በአማራ እና በኦሮሞ ሲቀልጥ እሱ ቃላት ሊገልጻቸው የማይችሉ በፍጹም ሁኔታ ረቂቅ የሆኑ ዲል ያሉ ተግባሮችን በበላይነት፤ ካለ አንዳች ከልካይ ሙሉ 26 ዓመት ከጊዜ ጋር እዬተጣደፈ ፈጸመ፤ ከወነ። ለዚህ በአጋፋሪነት ጸሐፍትን አሰለፈ፤ ባለታሪኮችን አሰለፈ፤ በዩንቨርስቱ የነበሩ ሙሁራን መቅኖ አሳጣ፤ የታሪክ መምሪያውን የጥቃቱ ሁሉ ሰላባ አደረገ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሰላምና መረጋጋት፤ ልማት እና ግንባታ ፓስተሩን ኢትዮጵያ ላይ፤ ተግባሩን ትግራይ ላይ በብልጽግና ተገነባ።

የወያኔ ሃርነት ትግራይ ባለሟሎችም ተቃውመውት የወጡትም ቢሆኑ ይህቺ ቀይ መስምርን ማለፍ አይፈልጉም። ምክንያቱም የፍልጎታቸውን ሆድዕቃ ስለሚያነቃንቀው፤ እንደ ጉርና ርጎ ስለሚንጠው። ባድመ ላይ ችግር ሲገጥመው ደግሞ አዲስ ብሄራዊ አጀንዳ ይዞ ከች ሲል በኢትዮጵያ ጉዳይ ሆደ ቡቡው ዜጋ ሆ! ብሎ ዘመተ። ያን ጊዜ እንኳን የኦሮሞ ሊሂቃን አብረው በአንድ መቃብር አማራና ኦሮሞ መቀበሩን እንዲያስተውሉት ፈቃደ እግዚአብሄር አልፈቀደም። መፈተሽ አልቻሉ። አሁንም አካላቸው እንጂ ህሊናዊ ማሳቸው እዛው ወያኔ ከኦሮሞ ሊሂቅ በቅቶ ከፈጠረላቸው ትውናዊ ሴራ መውጣትን አልፈቀዱም። በባድመ ጦርነት በዛ ማን እሳት ውስጥ አንደገባ፤ ማን የግንባር ሥጋ እንደሆነ ታሪክ በራሱ ጊዜ ይጽፈዋል። ከተኮስ አቁሙ በኋዋላ አሁንም የተረጋጋ መስሎ የነበረው ሾተላዩ ቀስ እያለ እያሟሟቀ አለስልስ እያለ ቀጠለ። ኦሮሞ የተቀበለውን ዶክተሪን ሌሎችም ብሄሬሰቦች ሊሂቃን ይህንኑ መርዝ አጋራ። ሌሎችም የዚህ ሰላባ እንደሆኑ ቀጠሉ። ባድመ ታላቅ ተቋም ነበር። በዚህ የአፈጻጻም ሂደት እንኳን የነቃው ህሊናቸው እውነት እንዲያንኳኳ አልፈቀዱም። ለማን ሲባል? ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ለታላቋ ትግራይ ተደላድሎ መግዛት ሲባል። 2.5 ሚሊዮን አማራ ሲጠፋ ለኦሮሞ ሊሂቃን ከመጤፍ ያልተቆጠረ የታሪክ ዕዳ ነበር። ሺህዎችን አፈናቅሎ፤ አስሮ፤ አምክኖ፤ ተወላጆዎችን ከቦታ አባሮ እራሱ አካባቢውን ወሮ፤ የመስፋፋት ፖሊሲውን ሲያራምድ ጉዳያቸው አይደለም። በዚህ የጭካኔ ሂደት ሁሉም በመንፈሱ ተባባሪ ነበር። „ጨቋኞ“ አማራ ዘሩ ሲጠፋ፤ ሲፈናቀል፤ ሲመክን፤ ሲወረር የእጁን ነው ዓይነት። በዚህ ሂደት ለሱ ጸጥ ያለ ሰላም አገኘ። ሰለምና መረጋጋት የሚባለው እኮ የታላቋ ትግራይ ህልም ለማሳካት ግድግዳው መቆሙን፤ ማገር መማገሩን፤ ጣሪያው ቆርቆሮ መልበሱን፤ በስሚንቶ መለሰኑን፤ ህንጻው መገንባቱ፤ በጠንካራ መሰረት ላይ ፎቅና ምድር ቤት መገንባቱን ነው። ይህን ነው ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ ጽናት! ክብር! የማድረግ አቅም! የቅርስ የበላይነት! የሥነ – ልቦና የበላይነት! የሚሉን። ዕድሉ ተሰጣቸው ተጠቀሙበት። ምን አጠፉ? ኢትዮጵያን ጠቅልለው ቢሸጧትስ ማን ከልካይ አላባቸው?

የሽዋ ልጆች በመማራቸው የሀገር ውስጥም የውጭም ዕድል የትምህርት እድል በማግኘታቸው፤ የበለጠውን የመንፈስ ቦታ ተጠቃሚ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ፖለቲካውን፤ ኢኮኖሚውን፤ ማህበራዊውን፤ ባህላዊውን፤ ታሪካዊውን፤ ወጋዊውን፤ ልማዳዊውን ሁሉ የመቆጠጠር፤ የመምራት ዕድል አግኝተዋል። ስለዚህም ተራዬ ነው አሁን ይገባኛል ባይ ነው ወያኔ። በዚህ ውስጥ ሽዋ ውስጥ የነበሩ ጉራጌው፤ ኦሮሞው ተጠቃሚዎች ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንዲነሳበት አይፈልግም። ስለምን ሰላሙን ያጣል? ስለዚህ አለ ወያኔ የመጀመሪያው ተግባራችን በዕውቀት ላይ የተገነባ ማህበረሰብ መፍጠር አለብን አለ። ወሰነ። አደረገው። ታዲያ እኛ ስናቀለፋ እና ለሽ ብለን ስንተኛለት ስለምን ዕድሉን አይጠቀም? በዕድሉ በሚገባ ተጠቀመ። እኛ አሁንም በታሪክ ላይ ሙግት ነው ቀን ከሌት። እያለቅን በማለቅ ውስጥ መሳቅ። እዬሞትን በሞታችን ውስጥ ምላሽና ግጥግጥ ማድረግ። እኛ እንዲህ ነን። „ጽኑዎች“ ደግሞ የተነሱበትን ዓላማ በዬደረሱበት ከግብ እያደረሱ፤ እያዘናጉ አድበተው እየገዘገዙ፤ እዬሰነጠቁ፤ እዬተረተሩ ይሄው ቀጥለዋል። የሥነ – ልቦና አቅማችን ሙሉዑ ነው ይገባቸዋል። አንድ ሀገራዊ ስብስብ ህጉ በማይፈቅድ መልክ ያልተወከሉትን እንዳሻው አስገብቶ ማሰተፍ ይችላል። ማን ሲጠይቀው? ከዚህ በላይ ብልህነት ምን ይምጣ? ልክ ናቸው። 95 ሚሊዮን ለ5 ሚሊዮን ወንዱም ቀበቶውን ለላ፤ ሴቷም መቀነቷን ሸብርክ አድርጋ በለኝ ስትለው ምን ይሁን? የማድረግ አቅም ከዚህ በላይ ምን ይግለጸው። 5%>95. እነሱ ያሉበት ደረጃ እና ሌለው ዜጋ ያለበት የመንፈስ አቅም እኮ የት ይገናኛል? በሴራቸው ውስጥ አንበርክከው እዬገዙ … እዬነዱ ነው። ጥልቅ ተሃድሶ ሲከለስ፤ ሲከለስ፤ ሲከለስ አሁን አረከሰ።

 • ተያያዥ ነገሮች።

  ከሱዳን ትግራይ፤ ከጁቡቲ ትግራይ፤ ከቅማንት ትግራይ፤ ከቤንሻጉል ጉምዝን የፈጠረበት ምክንያት ሲፈጥረው ገና ድርጅቱን ሲጠነስስ ያሰበው ነው። አባይን። አባይን ከአናቱ ለመቆጣጠር ሲያስብ መሸጋጋሪያ ቤንሻጉል ጉምዝን በምናቡ ፈጠረ። እዛ ላይ ህዳሴ ግድብ አለው። ከጣና በቀጥታ ትግራይ ላይ ኤሌትሪክ ወሰደ። ጋንቤላ ላይ ባለሃብቶች ፈጠረ የራሱን ሰዎች። እግረ መንገዱንም ጋንቤላ በሚያድረሰው መስምር ለመድረስ ቅማንትን ከጎንደር መነጠል ዋንኛ መስመሩ ነው። የወልቃይት የጠገዴ መሬት ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ደንበር ባለድርሻ ትግራይን አደርጓታል። ከዚህ በላይ ብልህነት ምን ይምጣ? የሆኑበትን እኮ ነው የሚናገሩት። ድምት አይጥ ገድላ እንደምትጫወትበት ነፍስን ገብሮ ለዛውም ተሸማቆ 27 ዓመት በጉድጓድ።

አሁን ሰሞኑን አቶ አዲሱ አረጋ በኦሮምያ የጻፉትን በአማራኝ ተተርጉሞ ቀርቧል። ለእኔ ስህተት ሆኖ አልታዬኝም። ይህንን ብቸኛው የሞራል ፖለቲከኛ አቦ በቀለ ገርባ በዛች በመጠራቅቅ በታሰረች የካቴና የሚዲያ ቆይታቸው ላይ „መሬት ዛሬ የማን ነው?“ የሚል በህሊና መሬት ላይ መጸሐፍ የጻፉት ያለምክንያት አይደለም። ከተሞች ሲሰፉ ገጠሬውን ማፈናቀላቸው ብቻ ሳይሆን፤ ከከተማ መምጣት ጋር የሚመጡ ባህልን፤ ወግን፤ ልማድን የሚፈታታኑ፤ ለመቆጣጠሪያ መንገድ ያልተበጀላቸው ሰፊ የማህበራዊ ቀውሶች ሁሉ አብረው ይመጣሉ። የገጠሩን ለዛ፣ ጣዕም፣ ወዝ የሚደርቁ። ይህን ለመከላከል ቅደመ ዝግጅት ቀርቶ በሃሳብ ደረጃ ውጥን የለም። ምን አገባው ወያኔ። ለራሱ ብቻ ነው ማዬትን የሚፈቅድ። በተመሳሳይ ሁኔታ የዋልድባ ገዳምንም በዚህው ማዕቀፍ ማዬት እንችላልን። ነገ ማህበረ – ሥላሴም ዕዳው አይቀሬለት ነው። ገዳም የሚፈለገው ከገሃዱ ዓለም ለመገለል ነው። ገዳም መግባታቸው ቅድስናው ፋይዳው ጸጥታው እና ከገሃዱ ዓለም ጋር ንክክኪ የሌለው ለጸሎት፤ ለሰጊድ፤ ለሱባኤ፤ ሃሳብን ለመሰብሰብ ከዱር አራዊት፤ እንሳሰት ወፎች በስተቀር የማይሰማበት የቀኖኖ ቦታ፤ የህሊና መሬት ስለ አስፈለጋቸው ነው። ገዳማት ሩቅ ናቸው። አብዛኞቹ መንገድም የላቸውም። ስለምን? አባቶቻችን ፈተና መቀበል ጸጋቸው ስለሆነ። አሁን ዋልድባ የስኳር እርሻ ሲኖረው ያ ቅርስ፤ ያ ትውፉት ይጠፋል፤ ስለምን ኦርቶዶክሰ ሃይማኖትም ኢትዮጵያን የሚገልጽ ንጥረ ነገር ስላለው በጣላትነት የተፈረጀ ነው። አሁን ይሄን ምዕመኑ አልገባውም። ይህ ሲሆን ጸጥ ብሏል። ትግራይ እንኳን። ስለምን ዋልድባ የትግራይ መሆኑ፤ መሬቱ የትግራይ እንዲሆን መፈለግ እንጂ በሃይማኖታቸው፤ በማተባቸው ላይ ላይ የተቃጣውን፤ የተሴረውን ነገር ልብ አላሉትም። መሬት ነው እነሱ የሚፈልጉት። መሰፋፋት። ገዳሙ እንደዛ መርከሱም አይጎረብጣቸውም እንደ ሃይማኖት ጽናታቸው።

ወደ አዲስ አባባ ስንመጣ የሚመሩት ባለሃብቶች የትግራይ ሰዎች ናቸው። እሰቡት አባይ ግድብ፤ ጣና ኤሌትሪክ፤ አዲስ አባባ ማሰተር ፕላን፤ ከጅቡቲ ትግራይ፤ ከሱዳን ትግርይ፤ ከጭልጋ ትግራይ፤ ጋንባሌ ላይ ሰፊ የእርሻ ልማት፤ ቤንሻጉል ላይ ህዳሴ ግድብ እነኝህ ሁሉ የትግራይን ልዕልና የሚያስከብሩ የተያያዙ፤ የተወራራሱ፤ በጥልቅ ልቦና የታቀዱ በመተግበር ላይ ያሉ መሰረታዊ አማክንዮች ናቸው። ትግራይ ባራሷ እምትገነባው አመዛኙ በእርዳታ ገንዘብ ነው። ሌላ ቦታ ደግሞ በዓለም ባንክ ብድር ነው የጎንደሩን የአዘዞውን ቁሞቀር መናህሪያ ማዬት ይቻላል። ሥራው ቆሟል፤ ግን የባንክ ወለዱ ዕዳው ይጨመራል። ከፋዮዋ ደግሞ ሰቲትን ያህል የነጭ ወርቅ መሬት የተወሰደባት ጎንደር፤ አቧራ ላይ ያለች ከተማ ነው እዳው የሚቆለለው። ልግጫ።

ሌለው አዲስ አበባ ያላት ጥሪታዊ ተቋማት ዋነኛ የሚባሉ ሀገራዊ ተቋሟት፤ ተቀማጭ የሚሆኑት ትግራይ ላይ ነው። ለምን ብሎ ደፍሮ የሚጠይቅ ቀርቶ የሚያስበውም የለም። ጥሬ እቃው መጥቶ የሚመረትብት ትግራይ ነው። ሌላ ቦታ ምርት የሚመረትብት ዳሽን ቢራ ጎንደር ይመረታል፤ ገቢው ለትግራይ ነው።  በኢትዮጵያ  አንቱ በተባሉ ማናቸውም መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ በልሆኑ ተቆሞች የተማሩም ያልተማሩም የትግራይ ሰዎች ቁልፍ ቦታዎችን ይዘዋል። በትናንሽ ከተሞች ባለው መረጃም ቢሆንም ማናቸውም ቦታዎች ትግራይ ኮረሪማ ናት። የድህንነቱን ሥራም ቀጥ አድርገው ይሰራሉ። ሰላም እና ጸጥታው፤ ልማቱና ግንባታው ይሄው ነው። እነ ኢፈርትንም ሌሎችንም ሲታሰቡ ምን ቃል ይችለዋል።

ሌላው ደግሞ ባታሪክ እሰጣ እገባ ሲሞገት፤ ሲፋተግ፤ ሲጋደል የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ መስራቾች ይሰቃሉ – በጅልነቱ።

https://www.youtube.com/watch?v=AjQC9sO-3jU የአማራና ኦሮሞ ምሁራን መድረክ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲበስዩም ተሾመ የቀረበ መነሻ ሀሳብና የምሁራንና ተሳታፊዎች አስተያየት“ አሁን ያሳበደቸው ይሄ ነው። አንድ የዩንቨርስቱ ሙሁር ወጣት „መርዝ በልተን ነው ያደግነው“ በማለት የመፍትሄ መንገድም ጠቁሟል። ይሄው ታሪካችን የእኛ ሆኖ፤ ለታሪካችን  ባዕድንት ይሰማናል። ስለሆነም የታሪካችን የክፉም የደጉም ባለድርሻነታችን በሚመለከት በተከታታይ እንዲሰራበት ከሁለቱም ክልላዊ መንግስት ባጀት ተመድቦ የሚሰራ ህጋዊ አካል ይፈጠርልን ይላል አንድ ወጣት ሊቅ። ሊቁ በመቀጠልም ዩንቨረስቲ ውስጥ በፍጹም ሁኔታ ወጣቶች ልንግባባ አንችልም ነው የሚለው። አልዛር ብለው ይሻለኛል፤ መዳህኒቷአለም አባቴ እጅግ ይወደው የነበረ ጻድቅ ከሞት የተነሳ። „መርዝ ተመግብን ነው ያደግነው የዛ መሻሪያ የህሊና ሥራ ብቻ ነው ይላል አላዛር ሊቁ።“ በዚህ መሰረት በፊት ጊዜ ወጣቶች ዳር ድረስ ሄደው ሲናገሩ ያመኝ ነበር። ለካናስ ጥፋቱ የእነሱ አይደለም። እንደ እህል በልተው፤ እንደ ውሃ ጠጥተው፤ እንደ አዬር ተነፍሰውት ነው ያደጉት። አሁን ግን በጥልቀት እንደገባኝ፤ በሽታው የት ላይ እንደሆነ ወጣቶቹ የፈለጉትን ነገር ቢናገሩ የተመገቡትን ነው። የኦነግ መሥራች ሊሂቃኑም መጣን የሚሉት አካላቸው ብቻ ነው የምለውም በዚህ ነው። እኔ እንጃ አሁን እንኳን መማር የሚፈልጉ አይመስለኝም። አማራ የሚባለውን ዘውግ መንፈሱን ለመቅረብ የቆረጡ አይደሉም። በዚህ ሂደት መፍትሄ ማፍለቅ አይቻልም። እጅግ የገረመኝ፤ ሳድግ ነገሩ የማይገባኝ ነገር የግንቦት ልደታ ጉዳይ እዚህ ሙሁራን ስብሰባ ላይ ተነስቷል። አሁንም አለጎንደር ከተማ የእመቤቴ ባዕል ነው። ግን ንፍሮ ይቀቀላል፤ ቡና ይፈላል፤ ሰፈረው በጋራ ያሳልፋል፤ ሲጠናቀቅ በእጃችን ይሰጠናል፤ ወንዝ ዳር ሄደን ረጭተን ዙረን ሳናዬው እንመለሳለን። ካዬነው በሽታ አብሮ ይመጣል ይባላል። የጳጉሜ ሰሞናትም ሄደን ወንዝ ስንጠመቅ ስንመለስ 5ቀኑን ሙሉ አድዮ ይዘን ነው። ይህ ለካ የገዳ ሥርዓት እንደሆነ ነው አንድ ሙሁር ሲገልጡ የሰማሁት። ጭልጋ የታቦት ያህል እንክብካቤ የሚደረግላት እሜቴ አይከል ቅቤው፤ ማሩ፤ በጉ፤ ዶሮው ይጎርፍላታል። ይሄ መሰረት ነው የተናጋው። ይህ የለማ በፍጹም ሁኔታ እርስ በርሱ በውስጥነት በረቂቅ መንፈስ የተገነባ፤ የታነጸ የህሊና መሬት ነው በጥላቻ እና በበቀል የከሰለው። ምክንያቱም ቤተሰቦቼ የተዋህዶ አራት ዓይናማ ሊቃናት ናቸው። ግን ይሄንን ይፈቅዳሉ። ይገርማል።

ይህን መልክ ለማያስያዝ ጥረት ሲጀመር ወያኔ ሃርነት ትግረይ የኢትዮጵያ ሱማሌን የኦሮሞ ጠላት እንዲሆን አስነሳው። እንጥሽት ውሃው ነው የፈሰሰው። ልክ አማራን ጠላትህ ነው ብሎ 26 ዓመት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰላሙን እንዳገኘ ሁሉ አሁንም ሁለቱ ሲዋቁለት እሱ ቀጣይ ተግባሩን በሰላም እና መረጋጋት ስም የጀመራቸውን ያጠናቅቃል። ይህም ብቻ አይደለም አማራ ጠላትህ ነው ማለቱ ብቻ ሳይሆን፤ እሰኪበቃው ህዝባዊ ፍቅር እንዳይሰማው፤ ርህራሄ እንዳይኖረው በመድረግ፤ ተበቀልኩልህ፤ ደምህን መለስኩልህ እያለ የሚፈልገውን በአሻው መንገድ አድርጓል። በታወቅ ቁጥር 2.5 ሚሊዮን አማራ ሲጠፋ ጉዳዩ አልነበረም ለሌላው ወገኑ። ነገም ይሄው ነው የኦሮሞ ማህረሰብ ዕጣ ፋንታው። ከዚህ በባሰ ሁኔታ ተመሳሳይ የዘር ማጥፋት ያካሂዳል። ኢትዮጵያን ሱማሌ ከጎኑ አሰልፎ ጥቃትህን ለእኔ ተዎው፤ እኔው አለሁልህ እያለ ያሻውን ባሻው ጊዜ ያሰፈጽማል። ለማን ሲባል ለታላቋ ትግራይ የማንፌሰቶ መሰረታዊ ዓላማ ሰላም እና መረጋጋት ሲባል። ከነገ ወዲያ ደግሞ ኦሮሞ ድቅቅ ሲልለት ወደ ኢትዮጵያ ሱማሌ መዶሻውን ይዞ ኮተት ይላል። ይህን ነው በህሊና ተመርምሮ የውስጥ አብዮት ማካሄድ የሚያስፈልገው። ለዚህ የሚተጉት ለእኔ መንፈሴ ናቸው። ከፍቅር በላይ ምን ሐሤት አለና።

 • የህሊና መሬት ወረራ።

ወያኔ ሃርነት ትግራይ የተነሳባት ዓላማ ሁሉንም ውጦ ኢትዮጵያን አጥፍቶ ታላቋን ትግራይን መፍጠር ነው። ቤተ መጸሐፍት ሄዳችሁ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመጣ የውጭ ዜጎች የጻፉትን መጸሐፍ ብታነቡት ፎቶው የሄሮድስ መለስ ዜናዊ፤ የአባ ጳውሎስ ነው። የሚገርመው አራስነት፤ ሰርግ፤ ሥራ – ወዳድነት፤ ቡና ሥርዓት፤ አልባሳት፤ ውበት፤ ዕምነት፤ ሃይማኖት፤ ሥልጣኔ ሁሉም ነገር ተወሮ የትግራይ ሆኖ ታገኙታላችሁ። እኔ ይሄን በ2004 ነበር ያነበብኩት። ትግራይ የራሷ የሆነ ድንቅ ባህል፤ ወግ፤ ልማድ፤ የሥነ – ጥበባት ቅርስ፤ እምነት አላት፤ በዚህ ደማቅ ባህሏ ብቻ ሳይሆን የሌላውም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ባህል የእኔ ብላ ብትቀብል መልካም ሲሆን፤ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ የሚያደርገው ግን ይህን አይደለም። ሌሎችን ከኢትዮጵያዊነት ወላዊ ዕሴት እያወጣ እሱ የወላዊ ዕሴት ባለቤት ለመሆን ነው የሚጥረው፤ ስለሆነም የወላዊ ዕሴት የህሊና መሬትም በወያኔ ሃርነት ትግራይ የሴራ ድር ተወሯል። ስለምን? ህልሙ ትግራዊነትን በመላ ኢትዮጵያ ማስፈን ነው። የወያኔ ማንፌስቶ በኢትዮጵያ ሊገለጽ በማይችለው ህብረ ቀላማት መንፈሷ አጅግ ነው የሚቀናው። ለዚህም ነው አብዛኛው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመጣ የጋብቻው፤ የአኗኗር ዘይቤው፤ በሽሚያ በወረራ የያዘው። ይህን በጥልቀት ሲታይ ትምክህታቸው መሰረት የለውም ማለት አይቻልም። እኛ አኮ በፍርፋሪ ወይንም በቅርጥምጣሚ ሥጋ ነው እምንባላው። እነሱ ደግሞ ዲል ባለ፤ በደላው ኮረቻ የሥን – ልቦና ግንባታ ላይ ናቸው። በታቀደ፤ ተከታታይነት ባለው። ውጤቱ በ አጭር፤ በመከከለኛ እና በረጅም ቢመታይ የተግባር መስኖ እዬለሙ ነው። በማን ሃብትና ጥሪት፤ በማን የመንፈስ አቅም ዛሬን፤ ነገን ተነገ ወዲያ እዬገነቡ ነው? መልሱት …

 • ማንአህሎኝነትና ግዛቱ።

ከወልድያ ስፖርት በተፈጠረው ችግር ምሽቱን ቀውጢ ያደረጉት ወጣቶች ምን ሲባል ከትግራይ አንድ ወጣት ይሰዋል ነው? ማንህሎኝነት። ንጉሥ አይሞትም አይከሰሰስም አይነት። በራሳቸው በጥጋባቸው በተፈጠረ ችግር ለተፈጸም ግድፈት ማረን አማላካችን፤ ወደ ልቦናችን መልሰን፤ ማለት ሲገባ ሌላ በቀል አዲግራት ዩንቨርስቲ አስተናገደ፤ ሰሞኑን አንድ ቃለ ምልለስ ላይ ስልክ አዳምጬ አቶ ማህሪ መሰለኝ ስማቸው ኢ.ኤንኤን የሚባል ድርጅት ነበር። ከጎንደር ስለተፈናቀሉት የትግራይ ሰዎች የአማራ ክልል ተጥሶ በግለሰብ ቤት ተኩስ ተከፍቶ፤ ህጻናት መፈጀታቸው፤ ከትግራይ የተነሱ የወንበዴ ቡድኖች ቤንዚን እና ክብሪት ይዘው ቅዳሜ ገብያን ማቀጠላቸው ብቻ ሳይሆን እጅ ከፍንጅ መያዛቸው አያሰፍርቻውም፤ አይሰቀጥጣቸውም እነሱ ስለምን እኛ ተነካን ነው። እሱም ቢሆን ለፖለቲካ ትርፍ የግድፈት ማረሚያ ትውና ጻፉ፤ ከትወና በኋዋላ ደግሞ ተጎጂው ሄዶ በራሳቸው መንደር ተገኝቶ የግፍ ድርብ  ይቅርታ ተገኖብሶ አፈር ልሶ እንዲጠይቅ አስደረጉ፤ ግጨውም ካሳ ተሰጠ፤ ይሄ አይነሳም፤ በቃ … አንዴት አድርጎ አማኑኤል አባቴ ቢፈጥራቸው እንደሆን አላውቅም። እንዲህ ዓይነት ተፈጥሮ ነው የሚታዬው። የተላጨ ምናብ። በሚታይ በሚጨበጥ ወላዊ ግድፈት ነገር አንኳን መታበይ፤ መንጠራራት፤ ስለዚህ እንዲህ ቢሉም፤ ቢሆንም አይደንቅም። ማዕት ፈጣሪ ያመጣል። መታበይ ላምንም ለምንም አይሆንም።

 • ባለሳምንት።

አሁን ደኢህዴን የጎላ ችግር የሌለበት ስለመሰለው ጸጥ ብሏል። ያው የትግራይ ያህል ባይሆንም ጸጥታው እንዳይተወክ ብቻ ሳይሆን ጥርጣሬ እንዳይገባው የወያኔ ሃርነት በጭቃ እሾኽ ተፈጥሮው የቤት ቃጋነቱን ሸፍን አድርጎ አልጋ ሆኖለታል። ነገር ግን ኢትዮጵያን በትግራዊነት የመተካት ህልሙን ሳያሳካ አያንቀላፋም። ለዛሬ እንደ መሳሪያ ይጠቀምበታል። ነገ ወርውሮ መጣል ብቻ ሳይሆን፤እየተከታታል አመድ ያስግጠዋል እራሱን ደኢህዴን። ለዛውም ኢትዮጵያዊነት ላይ ድርድር የሌለው ማህብረሰብ ነው። ጽኑ እና የጠራ አቋም ያለው እንደ አፋር፤ እንደ ጋንቤላ። ጋንቤላ የፈተናው ግማድ ተሸካሚ የሆነው እኮ በህገ መንግስቱ ላይ በነበረው የጠራና የጸዳ አቋም በተቋጠረበት ቂም በቀል ነው። ደቡብ ሱዳን ስለሚያዘርፋቸው ደም እና -ሥጋዎቻችን የሱዳን ንድፍ አይደለም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ንድፍ ነው። ከደቡብ ሱዳን ጋር አብሮ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ይሰራል። የኢትዮጵያን ዘር እዬነቀለ ደቡብ ሱዳን ላይ እንዲበቅል ያደርጋል። በሌላ በኩል ከተቀናቃኙም ጋር ሸሪካ ነው። ከደቡብ ሱዳን የሚመጡትን ስደተኞች ተቀባይ ሆኖ ደግሞ ከዲታ ሀገሮች ዶላር ይዘንብለታል። ሳናውቀው መኖራችን ብቻ ሳይሆን አሁንም ለማወቅ አለመፍቀዳችን ነው አንጀትን የሚያቆስለው ነገር። ከችግራችን ሳይሆን የምንነሳው ከ4ኪሎ ወንበር ነው፤ በቃ። ለ4ኪሎ ወንበር የህሊና መሬት ያስፈልጋል። የህሊናው መሬት በወያኔ ሃርነት የሴራ ማሳ ሆኗል። በዛ ላይ የሚጀመር ትንሽ ነገር ሲኖር የወያኔው እግር ብረት አለብቃ ብሎ እኛ ደግሞ አቃቂር እንወጣለን። እንራቀቃለን። ከመርዝ በላይ የሆነ መከራ ተሸከመን ቅልጣን ያሰኘናል። እናማርጣለን፤ በሌለን፣ የእኛ የምንለው የህሊና መሬት ላይ መዘባነን። አሁን እኛ ጸዕዳ መንፈስ አለን? እንፈትሸው? እምንፈልገው መሞጋጋስ ብቻ ነው። ምን አጎደልን ብሎ ሊሂቁም አይጠይቅም እኛም ውስጧችን ሸሽግን በቅብ ላይ መጪ ነው። ለዛውም ወያኔን የሚያክል ሥሩ የት ላይ ተነስቶ የት እንደሆነ መዳረሻውን የማናውቅ አውሬ አስቀምጠን።

ዘረፋው፤ ወረራው፤ ማፈናቀሉ የርስት ጉልት የመሬት፤ የሃብት፤ የባህል፤ የቅርስ፤ የትውፊት  ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው ቀጥ አድርጎ የያዘነን የህሊና መሬትንም ጭምር ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ በቁማችን የወረረን። ስለሆነም ነው በተለያዬ ጊዜ እነሱ አፋቸውን ሞልተው ገና ቀትቅጠን እንገዛሃለን የሚሉት። እነሱ እኮ ምርጥ ደም ያላቸው ስለመሆኑ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ እራሳቸው እኮ ተናግረውታል። የናዚ መንፈስ እኮ ነው አንሱ ዘንድ ያለው። እኔ እሰከ ወልድያው ክስተት ድረስ ሙሉ ለሙሉ እንዲህ ተሳክቶላቸዋል ትግራይ ውስጥ ብዬ አላስብ ነበር። አሁን ግን ህሊናዬን አሳምኘዋለሁ ዘር አንዳልተረፈ። የሚያሳዝኑኝ አሁንም ገና ወደፊት የሚፈጠሩት ህፃናት ብቻ ናቸው። በማያውቁት ዓለም የበቀል ተጠያቂ ወይንም ተጥቂ መሆናቸው። ትውልድ ሂደት ነው …

 • ስልበት።

የሰው ልጅ የተሰጠው ተፈጥሮ አለ። በተፈጥሮው የሰው ልጅ ከእንሰሳቱ ዓለም የተለዬበት ስሜት ነው። ስሜት ውስጥ ደስታ፤ ቁጣ፤ ሃዘን፤ ብስጭት፤ ሳቅ፤ ርህርና፤ ንዴት ወዘተ ሃብታችን ነው። አሁን የወያኔ ሃርነት ትግራይ በፈጠረው የህሊና መሬት ወረራ ተፈጥሮ ውስጥ ድልድዩን የመሰበር ሁኔታ አለ። ሃዘን እንኳን የራስ ደምና ሥጋ „ሰው“ በሚለው መሥፈርት እራሱ የማንገፋው የተፈጥሮ ጸጋችን ሆኖ ሳለ ይህን እንኳን ተፈታትኖታል። ስሜታችን ሳይቀር ወረራ ተካሂዶበታል። እስራቱ፤ መፈናቀሉ፤ ሞቱ፤ መሳደዱ፤ እኩል አይሰማንም። ሁለት ወጣቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ቢሰዉ ጎሳቸው ሳይሆን „ሰው“ መሆናቸው ብቻ ቅርባችን ሊሆን አልቻለም። ስለምን አድሎው ስለገለማ። የተዳላለትም „ሰው“ የሚለውን ፍጡር ማዬት ተስኖታል። ቤተ – እግዚአብሄር ይሄዳል፤ ሥርዐቱን ይፈጽማል፤ መስኪድ ይሄዳል፤ ሥርዐቱን ይከውናል። ሃይማኖት እኮ የተፈጠረው ለሰው ነው። ሰው የተፈጠረውም እግዚአብሄርን እንዲያመሰግን። ይህችን ብቻ ነው ፈጣሪ ከእኛ የሚፈልገው። ለሰው የተፈጠረውን ሃይማኖት አክብረን፤ ሃይማኖትን እንዲያከብር የተፈጠረውን ሰውን እኩል ማክበር አልቻለም። ሞቱን እንኳን። በጎጂም በተጎጂም አትራፊው የወያኔ ሃርነተ ትግራይ ማንፌስቶ ነው። ሰውነታችን ነው የቆመው እንጂ ሌላው ቀርቶ ስሜታችን ውስጥ ያሉት ተፈጥሮዎች ጌታ ልንሆን በፍጹም አለስቻለንም። አናዝንም። ይህ የሆነበት ግፉ መመጣጠን አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ገፊዎችም ከተገፊው በላይ ተሰላፊ ነን ብለው ስለሚያላግጡ። አሁን ባለፈው ሀገር ቀውጢ በሆነ ሁኔታ ብለው ዘረዘሩ ዶር. አረጋይ በርሄ „የሰቆቃው ማዕከል“ የሆነውን አማራን ዘለው። አማራ ሰው አይደለንም? ከእንጨት ነው የተፈጠረውን? አንድ ሊሂቅ። ለመሪነት ራሱን ያጨ። በእውቀቱ የመጨረሻ ደረጃ የደረሰ። ለቀለሃ ቀለብ፤ ለእንባ ስንቅንት አማራ ቢውል ጉዳያቸው አይደለም። ለነገሩ የተነሱበት ዓላማ ስለሆነ በሂደት በአፈጸጸም የተጎዱት እንጂ አማራ ሞቱም፤ ስደቱም፤ መፈናቀሉም እስራቱ ይገባዋል ባይ ናቸው። ወሸኔ የኔ ጀግኖች እያሉ ነው። ይሄን የሚያነቡ ወጣቶች እንዴት ወደ ሰውነት ሊመጡ ይችላሉ? በፍጹም። መርዙን መንቀል የሚችሉት መርዙን የተከሉት ሰዎች ከመርዝ አስተሳሰባቸው በፍጹም ሁኔታ ሲነጹ ብቻ ነው። ከሳጥናላዊ ተግባራቸው ወጥተው እንደ ሰው እጃቸውን ከደሙ ለማጽዳት በሰባዕዊነት ጠበል ሲጠመቁ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ትውልዱ አይድንም። ነገም ዕድሉን ቢያገኙ ይህ መከራ፤ ይህ ሰቀቀን አልጎርበጣቸውም፤ አላሳዘናቸውም እና ይቀጥላሉ። ስለምን? በህሊናቸው መሬት ውስጥ አማራን ጠላት ብለው መዝግበውታል። ስለዚህ በአንድም በሌላም መጥፋት አለበት ይህ የህሊናቸው ፖሊሲ ነው። ይሄው ነው። እንኳንስ ከስልጣን ላይ የሆኑት ከሥልጣን የለቀቁትም ወደ ተፈጥሯዊነት ለመቅረብ አልፈቀዱም። ነፃነት በዚህ ኢ- ሰብዕዊ ማዕበል ውስጥ ነው ተጠርንፎ ያለው። ወጣቶችም የሚማሩበት አብነት ሊያገኙ አልቻሉም። ከአንድ ቅዱስ ሰው ከክቡር አቶ ገ/ መድህን አርያ በስተቀር።

ትዕቢቱንም እንደዛ ነው የሚቀበሉት። ትምክህቱንም እንደዛ። ከስሩ እንዲነቀል መርዙ አይፈልጉም። ውስጣቸው ከማንፌሰቶው አስኳል ጋር ፍች መፈጸም አይችልም። ማንፌስቶውን በልተው ከደማቸው ጋር አዋህደውታል እና። ትውልዱም በዚህ መልክ እንዲቀጥል ይሻሉ። ተዉ አይሉም! የትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት ቢወድቅ እንኳን ከላይ አስከታች በዬትኛውም ሁኔታ መዋቅራቸውን አሳምረው ዘርግተውታል። ገንብተውታል። በጸና መሰረት አዋቅረውታል። ይህ የውስጥ ሐሤታቸው ነው። የሚያረካቸው። የሚያፍነከንካቸው።

አሁን ሁለተኛው ፈረቀኛ ኦሮሞ ላይ  ቀጥሏል፤ በሌሎችም ላይ እያሰገረ ይቀጥላልም። ጥቃቱን እንዲፈጽም የሚያደርጉት ደግሞ  የአማራን ልጅ አስገድደው ኦሮሞን እንዲገድል፤ ኦሮሞውን ደግሞ አማራውን እንዲገድል ነው። ስለምን? የኢትዮጵያ መዳኛ ስለሆነ። አሁን እኮ ማሰብ ያልቻልነው ሳይሆን ሌሎችም ሦስተኛ ትውልድ እኮ ነው እያለቀ ነው፤ መስናዶውም አራተኛውን ለመፍጀት ነው ስንዱነቱ። ስለሆነም መሬት ላይ ትውልድ ሊድንበት የሚችሉ የመፍትሄ ቁልፍ ስለተገኘ፤ አሁን በውጥረት ማዋከቡ ቀጥሏል በውጪም በሀገር ውስጥም። እስከ አሁን ድካሙ፤ በሽታው እንዳለ እንጂ የበሽታው መንስኤ ምን እንደሆነ ከጥቂቶች በስተቀር ሌላው አያውቀውም። ለዚህ ነው ሊሂቃኑ በድፍረት ወጥተው ዕውነቱን ሲነግሩን እምንደነግጠው። እነሱ የኖሩበት፤ ነገም እንዲኖሩበት ያቀዱት፤ በግብር ይውጣ ሳይሆን የወያኔ ሃርነት ትግራይ እጅግ በሰለጠነ አመራር ነጮችን በምክር አገልግሎት ቀጥረው ሳይቀር የሚሰሩበት ጥልቅ የመርዝ፤ ውስብስብ የሸር ተልዕኮና ግብ ያለው መሰሪ ወንዝ መሆኑን መቀበል ተስኖናል።

 • አቅም ማዋጣት።

አሁን ያ የፍቅር መንደር ሀረር ጦርነት ላይ ነው። ጦርነቱ ሞት ነው። ሞቱ ትርፉ አመድ እና ዕንባ ነው። በታቀደ ሁኔታ ነው ጥቃቱም፤ በቀሉም እዬተከወነ ያለው በመጠነ ሰፊ ሁኔታ ነው። ቢያንስ የኦሮሞ ልጆች አቅም ማዋጣት ሲጋባቸው ከሞት ጋር እተጋፈጡ ላሉት ወጣቶች ቅድመ ሁኔታ ይደረድራሉ። ይሄ ለእኔ  በፍጹም ሁኔታ ዘመናይነት ነው። አሁን የምንፈላሰፍበት ወቅት አይደለም እኮ። 40 አመት ተደራጅቶ ኦነግ ምን አደረገ? ሥልጣን ላይም ነበር። 40 ዓመት ያልተሳካ አሁን በጥቂት ጊዜያት ችግር ሁሉ ብን ብሎ እንዲጠፋ እንመኛለን። ውጪ ሀገር ሆኖ እኮ አይደለም አቶ ለማ መገርሳም ሆኑ ዶር. አብይ አህመድ የሚታገሉት። እሳት ረመጥ ውስጥ ተጥደው ነው። ወያኔ ገዢ መሬት ሆኖ እነኝህ ምስኪኖች ሙት መሬት ሆነው ነው እዬተጋፈጡ ያሉት። እነኝህን የአጥቢያ ኮከቦችን ሃሳብ እያዋጡ አይዛችሁ ማለት ነው ግዴታው ነፃነት ከተፈለገ። የእነሱ አይደለም ጠቅላላ የቤተሰቦቻቸው ህይወት ሁሉ አደጋ ላይ ነው። እያንዳንዷ ሰከንድ የውጪ ነፍስ/ የግቢ ነፍስ የጭንቅ አዬር ነው ያለው። ሙሉዑ የመንፈስ አቅሙን፤ ሙሉ የደህንነት ተቋማትን፤ ሙሉ የጸጥታ ሃይሉን፤ ሙሉ የኢኮኖሚ አቅሙን ለሎቢ አውጥቶ ስውር መረብ ዘርግቶ እዬተፋለማቸው፤ የእኛ ድምጽ ግን የነፃነት ቃና ያነስዋል። ያለ ህዝብ ፖለቲካ ቀርቶ የእምነት ተቋም በቀጣይ ይኖራልን? ጎንደር ሲሪያ ከሆነች ቆዬች። አሁንም ኢትዮጵያ ሱማሊ እና ኦሮምያ ሲሪያ ሆነዋል። የቱ ይቅደም? አቅም ማዋጣት ወይንስ ቅልጣን?  ቢታሠሩ ወይንም በህይወታቸው ላይ አንድ ነገር ቢደርስ ወይንም የቀናበትን የመንፈስ ህሊናው ብቃት እና ልቅና በመርዝ በመበከል ሌላ ሰው አድርጎ ቢፈጥራቸው ወይንም አካላቸውን አጉድሎ መንፈሳቸውን እንዲስቱ ቢያደርጋቸው ፎቶ ተይዞ ይወጣል ወግ አይቀርምና። ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይመለከታል። በጠቅላላ መንገዱ ጠፍቶብናል። ምን ይሆን አዚሙ?

 • ከውና።

ቀደም ብዬ የገለጽኩትን ስጋቴ አጠንክሬ መከወኛ ላድርገው። ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባው ቁምነገር አሁን ለሴራ የሚያሰማሯቸው የራሱን ዞግ አይደለም። አማራውን ወደ ኦሮሞ ኦሮሞውን ወደ አማራ ሪስፕሮካል ስልት ነው የሚጠቀመው ወያኔ። ይህ ቢሆን ተመልሰን ደግሞ ሌላ የሊሂቃን፤ የአክቲቢስት ጦርነት እንገባለን። አዲስ ሙግት እንጀምራለን። በዚህ ጊዜ ለታላቋ ትግራይ ህልም የልማት፤ የደህነነት፤ የሰላም ጊዜ አዋጅ ፈቅደን ሸለምነው ማለት ይሆናል። ከሴራው ጋር ኑረን አሁንም መማር አለመቻላችን የጤናችን አይደለም? ቀድሞ ነገር ወያኔ ሃርነትን እኮ የኢትዮጵያ መሬት በፍጹም ሁኔታ ያለበቀለችው የምድር እንባይ እኮ ነው። እንደሌሎች የተቃዋሚ ድርጅቶች መሰላችሁን? በፍጹም ሁኔታ „ሰው ሰው“ ጠረን የሌላው እርግማን እኮ ነው ወያኔ ሃርነት ማለት። ቀን ሲክብ ይውላል። ማታ ሲንድ ያድራል። የሆነ ሆኖ ለወያኔ ሴራ ከራሱ ዞግ ውጪ ሌሎች ቢጠዬቁ እንዳይተባበሩ፤ የማህበራዊ ሚደያ ታታሪዎች ልትመክሯቸው፤ ልታስጠነቅቋቸው ይገባል። ቢፈጠር እንኳን ከታሰበው ዘላቂ ግብ ጋር ስለማይመጣጥን በላቀ የመቻቻል ጥበብ ይህን የገዘፈ የግማድ አቀበት መሻገር ይኖርብናል። ልብ ይስጠን ፈጣሪ አምላክ። እምንታገለውም እንወቅ። ለሩቅ መንገድ መነሻ እርሾ ያስፈልጋዋል። ለመነሻው ሆነ ለእርሾ ክብር እንስጥ። አሁን መግለጫውን አዳምጫለሁ። አዘናግቶ ወያኔ ምን እንደሚያደርግ አይታወቅም። ትእግስት፤ ርጋታ፤ ጥንቃቄ፤ ያሰፈልጋል። እንዲህ ሚዲያ ላይ እኛ እንደምጽፈው ወይንም እንደምንናገረው፤ እንደምናጣጥለው፤ ወይንም ይበናል ብለን እንደምናሟራተው አይደለም። ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ መርዝ ከተበከሉት ጋር አብሮ መብላት፤ መጠጣት፤ መዝናናት፤ ጎን ለጎን አልጋ ይዞ መተኛት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ የሴራ አቅም ማለት፤ የተቆለፈ ምድር ማለት ነው። ተከፍቶ የማይታይ፤ ተከድኖም የማይምር። በዚኸው ላብቃ …

„የተሰወረ ጥበብ እንደ ተሰወረ ወርቅ ነው። የሁለቱስ ጥቅማቸው ምንድን ነው? ጥበቡን ከሚሰውር አዋቂ ሰው፤ ስንፍናውን የሚሰውር ሰነፍ ሰው ይሻላል።“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፴ እስከ ፴፩)

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.