በመከላከያ ሰራዊት የጭነት መኪና በህወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የምግብ ዘይት በኦሮሚያ ፖሊስ መወረሱ ታወቀ

 

BBN News December 20, 2017

በኦርላል የመከላከያ መኪና ከጋምቤላ ክልል ተጭኖ በኦሮሚያ ዉስጥ ያልፍ የነበረ ህገወጥ የዘይት ጭነት በቁጥጥር ስል መዋሉ ታወቀ።ታርጋዉና ንብረትነቱ የመከላከያ ሚኒስቴር የሆነ መኪና የጋምቤላን ክልል በማለፍ ኢሊባቡር ዞን ቡሬ ወረዳ ሲደርስ በፖሊስ ተገዶ መቆሙ ታዉቋል።የመከላከያ ሰራዊት አባል የሆነው ሾፌር ጭነቱ ምን እንደሆነ ለማሳየት ፍቃደኛ ባይሆኑም የቡሬ ከተማ ፖሊስ አስገድዶ ጭነቱን መፍታቱን እማኞች ያስረዳሉ።

በመከላከያ አርማ፣በመከላከያ መታወቂያና በመከላከያ የጭነት መኪና እቃዎችን በህገወጥ መንገድ ለማሳለፍ የሚደረገው ሙከራ ባለፉት ሶስት ወራቶች ተጠናክሮ መቀጥሉን መረጃዉን ለቢቢኤን ያደረሱት አካላት ይገልጻሉ። እቃው የህወሃት የጦር መኮንንኖች ሊሆን አንደሚችል የሚያስረዱት የቢቤኤን የኢሊባቡር ዞን ምንጮች በቁጥጥር ስር ከዋለዉ የመከላከያ ሰራዊት አባል ጋር ሁለት ክላሽ-ኢንኮቭ ጠመንጃዎች መያዛቸውን አሳዉቀዋል።ባጠቃላይ 328 ጀሪካን ዘይቶች ከኦራል የጭነት መኪናዉ ላይ የተራገፉ ሲሆን፤መኪናዉን ለመረከብ የመጡ ከፍተኛ የጦር መኮንን «ወታደሩ በግሉ የሰራዉ የኮንትሮባንድ ስራ ነው፣መከላከያዉ የሚያገባዉ ነገር የለም» ማለታቸውን የቡሬ ከተማ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

የመከላከያዉን የጭነት መኪና ይነዳ የነበረው ሾፌር ከቡሬ ከተማ ፖሊስ ጋር ለመታኮስ ሞክሯል።ሁኔታዉ የማያዋጣው መሆኑን ሲያዉቅ ወታደሩ እጅ እንደሰጠ ታዉቋል።ዘይቱን ለማራገፍ የቡሬ ከተማ ነዋሪ መሳተፉን የሚያስረዱት ምንጮች፤ ወታደሩም በኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ቁጥጥር ስር ዉሎ ፍርድ ቤት ከቀረበ በሗላ የሁለት አመት ጽኑ እስራትና ሐያ ሺ ብር ቅጣት እንደተፈረደበት አሳዉቀዋል።

በሀገወጥ መንገድ ኮንትሮ ባንድ ዘይትን በመከላከያ ሰራዊት መኪና ጭኖ ሲሔድ የተገኘው የመከላከያ አባል የቡሬ ከተማ ፖሊሶችን ጉቦ ለመስጠት ሞክሮ ነበር። ሐያ ሺ ብርና አመስት ጀሪካን ዘይት እንካቹ ቢሊም የፖሊስ አባላቱ በመቃወማቸውና ከህዝብ ጎን በመቆማቸው ዘይቱን ለመያዝ እንደተቻለ ታውቋል።

በተለያዩ የኦሮምያ ዞኖች የመከላከያ ሰራዊቶች ሲምንቶ፣ብረትና ሌሎችንም የግንባታ እቃዎች ጭነው ሲሔዱ በተደጋጋሚ መያዛቸው የሚዘነጋ አይደለም። ምግብና ሌሎችንም ሸቀጣ ሸቀጦችን በሰራዊቱ ስም በመጫን የህወሃት ጀነራሎች ከኦሮሚያና ከመሐል አገር ወደ ትግራይ በማሸሽ ያከማቻሉ የሚል ክስ ይቀርብባቸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.