የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ልዩ ጥቅም አስመልክቶ ተጠርቶ የነበረው ስበሰባ

“እስካሁን በምንሄድበት መንገድ መሄድ አንችልም። ህዝቡ የሚፈልገውን ለውጥ እኛ መስጠት ካልቻልን የሁላችንንም መቃብር እራሳችን እየቆፈርን መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል”
ዶር አብይ አህመድ የኦህዴን ከፍተኛ አመራር አባል

 

የሕወሃት ዉሳኔዎችን በፓርላማው እንዲጸድቅ የሚያደርገውና ፓርላማዉን የሚያሽከረክረው አቶ አስመላሽ ፣ ከአባ ዱላ ገመዳ ጋር በመሆን ፣ ወቅታዊ ባልሆኑ፣ የኦሮሞውን ማህብረሰብ አባላት ከሌላው ጋር የጀመሩትን የመቀራረብ መንፈስ ሊያደፈርስ በሚችልና በአዲስ አበባ የኦሮሞን ጥቅም ለማስጠበቅ በሚል፣ በሕወሃቶች በቀረበው አጀንዳ ላይ የፓርላማ አባላት እንዲወያዩ ለማግባባት ሲሞክሩ

———————-///—————————–

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ልዩ ጥቅም አስመልክቶ ተጠርቶ የነበረው ስበሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል

ባህርዳር ፡ታህሳስ 13/2010 ዓ/ም(አብመድ)የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ህገ-መንግስታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ህዝባዊ ውይይት ለማካሄድና አስተያየት ለመሰብሰብ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጠራው ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት (አዲስ ዘመን ጋዜጣ) አስነበበ ፡፡

Image may contain: 26 people, people sitting

ምክር ቤቱ ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለህግና ፍትህ እንዲሁም ለከተማ ልማትና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመራው መሰረት፤ ቋሚ ኮሚቴው ዛሬ የህዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ የጠራው ስብሰባ በረቂቅ አዋጁ ላይ ምንም አስተያየት ሳይሰጥበት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት፤ ቋሚ ኮሚቴው ስብሰባውን የጠራው በረቂቅ አዋጁ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል፣ ረቂቅ አዋጁን የሚያዳብሩ ግብአት ለመሰብሰብና ወጥነትን የተለባሰ ለማድረግ በመሆኑ ተሳታፊዎች ረቂቁን ለማዳበር የሚረዱ ገንቢ አስተያየቶችን እንዲሰነዝሩ ጠይቀዋል፡፡Image may contain: 13 people, people sitting and indoor

በዕለቱ በምክር ቤቱ የተገኙ ተሳታፊዎቹ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት ይልቅ የኦሮሞ ህዝብ በረቂቅ አዋጁ በተገቢው ሁኔታ ባልተወያየበት፣ ከሁሉም አካባቢ ያሉ ተወካዮች ባልተገኙበትና ወቅታዊ ችግሮች ባልተፈቱበት ሁኔታ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ መወያየት ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤው አቶ አባዱላ ገመዳ፤ በክልሉ ውስጥ ችግር ቢኖርም ምክር ቤቱ ስራውን መስራት ስለሚጠበቅበትና ጉዳዩም የተለያየ በመሆኑ ውይይቱ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

“እስካሁን የህዝብ ውይይት አለመደረጉ ስህተት ነው፡፡ በመሆኑም አሁን የባለድርሻ አካላት የተካተቱበት ጭምር በመሆኑ ቢቀጥል የተሻለ ነው፡፡ሃሳቦች ማንሳት፣ መከራከርና ማዳበር ተገቢ ሲሆን፤ ቀጣይ የሚነሱ ሃሳቦችን በመያዝ ምክር ቤቱ የሚወስንበት ጉዳይ ይሆናል” ብለዋል፡፡

የሚያሳይ

http://amma.gov.et/am/content/የኦሮሚያ-ክልል-በአዲስ-አበባ-ከተማ-ያለውን-ልዩ-ጥቅም-አስመልክቶ-ተጠርቶ-የነበረው-ስበሰባ-ላልተወሰነ-ጊዜ-ተራዝሟል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.