አንድ ቀን፣ ከአንድ ቀንም የተወሰነ ሰዓት እስረኞችን ብናስታውስ ምን ይመስላችኋል? (ጌታቸው ሽፈራው)

~ ብልቱ የተኮላሸውን

~ጥፍሩን የተነቀለውን

~ የሀሰት ምስክር የተሰማበትን

~ ቤተሰቡ የተበተነበትን

~ ህክምና የተከለከለውን

~ጨለማ ቤት ውስጥ የታሰረውን

~በማንነቱ፣ በፖለቲካ አስተሳሰቡ፣ በሙያው ( በጋዜጠኝነቱ፣ በጦማሪነቱ፣ በፖለቲከኝነቱ……) ምክንያት የታሰረውን

~ በግፍ ለአመታት የታሰረውን

~ ቤተሰብ እንዳይጠይቀው የተከለከለውን… … ብዙ ብዙ አለ።

እነዚህን እስረኞች አንድ ቀን በእኩል ሰዓት ብናስታውሳቸው መልካም ይመስለኛል። ለእስረኛ ትልቁ እና ዋናው ነገር ውጭ ባለው ህዝብ አለመረሳት ነው። ብዙዎቹ የታሰሩት ሲታገሉ ነው። እነሱን መርሳት ተገቢ አይመስለኝም። ምንም ባናደርግላቸው እንኳ በተመሳሳይ ሰዓት ማስታወስ አይከብደንም። እነሱን ለማስታወስ ማዕከላዊ፣ ቂሊንጦ፣ ቃሊቲ፣ ዝዋይና በእየ ጣቢያው መሄድ አያስፈልግም። እዚሁ ፌስቡክ ላይ የተፈፀመባቸውን ክፉ ነገር እና የፈፀሙትን መልካም ተግባር እያወሳን ማስታወስ እንችላለን።

ለእስረኛ እጅግ የከበረው ነገር አለመረሳት ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.