ጥፊዎ ወደ ቦክሥ አደገች! (በእስማኤል ዳውድ)

ማዕከላዊ እሥር ቤት ውስጥ፣ አንድ መርማሪ ቃሌን ይቀበላል። ይጠይቀኛል እመልሳለሁ ። በክፍሉ ውስጥ መርማሪ ፖሊሱና እኔ ብቻ ነበርን ።…በመሃል አንድ ሲቪል የለበሰ ሠው በሩን ከፍቶ ገባ ።….ክፍሉ ውስጥ( ቃል የምሰጥበት) ትንሽ ጎርደድ ፣ ጎርደድ ካለ በኅላ ፣ ሳላስበው በጥፊ መታኝ ።…ይቺ ጥፊ አደገችና በንጋታው ወደ ቦክስ ተቀየረች።

በዚያው ቀን ለሊት ላይ የታሰርኩበት ክፍል ተከፈተ። በክፍሉ ምንም ዓይነት ብርሃን ሥላልነበረ፣ በሩን የከፈተውን ሰው መለየት አልቻልኩም ።….ወዲያው፣ ረጅም የባትሪ ብርሃን ዓይኔ ላይ በራብኝ ። ማንነታቸውን ያለየኋቸው ሰዎች ክፍሌ ውስጥ ዘለቁ ። ….” ተነስ” ተባልኩ ።…ተነሳሁ ።…ዓይኔን በጨርቅ ግጥም አድርገው አሰሩት ።……..በእነሱ መሪነት፣ ( ክንዴን ይዘው) ክፍሌን ለቅቄ ወጣሁ ። ወዴት እንደሚወስዱኝ አላውቅም ።…ግን፣ ኮረኮንች ላይ እንዳለሁ ይታወቀኛል ።…ጫማ ስላላደረኩ፣ እግሬን ጠጠር ይወጋኝ ነበር ።…ከዚያም ደረጃ መውጣቴን አስታውሳለሁ ። ደረጃውን እንደጨረስኩ አንድ ቤት ውስጥ አስገቡኝ ።….(ቤት ውስጥ መግባቴን ያወኩት፣በሩን ሲከፍቱ ስለሰማሁ ነው) ወዲያው በጠረባ መትተው ጣሉኝ ከዚያም.. የሚችሉትን አደረጉ ።…እስኪደክማቸው።
………በዚያም አላቆሙም አንስተው ገለበጡኝ ። ……( ቶርች)….ሲጨርሱ ተሸክመው ክፍሌ ውስጥ ጥለውኝ ሄዱ ።

ይህ ከላይ የተፃፈው ታላቁ እና ጀግናው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የደረሰው በደል ነው ። እስክንድር ነጋ ይህን ሁሉ መከራ የተቀበለው እና እየተቀበለ ያለው በኢትዮጵያዊነቱ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል ፤ ፍትህ ፣ ነፃነት እና እኩልነት ይገባኛል ብሎ ነፍጥ አንስቶ ሳይሆን ብዕር ጨብጦ ሃሳቡን በወረቀት ስለገለፀ ነው ።

እስኪ እናንተ እውነት ለሰው ልጅ ክብር ካላችሁ ፤ ስለ ኢትዮጵያ ያገባናል ካላችሁ እና እንደ እስክንድር ነጋ ፍትህ ፣ ነፃነት እና እኩልነት ይገባናል ምትሉ ከሆነ ይህ ዓይነት ግፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ሲፈፀም እንዴት ዝም ትላላችሁ ? እኛስ እንደዜጋ መች ነው ይሄን መንግስት ልክ የምናስገባው ?
ጋዜጠኛ እስክንድር እንደብዙሐኑ እነሱ የሚፈልጉትን ፈጽሞ ከባለቤቱ ከስርካለም ፋሲል ጋር ልጃቸው ናፍቆት እስክንድርን ት/ቤት እያመላለሰ ( በነገራችን ላይ እስክንድር ነጋ በመጨረሻ እስር ቤት ሲገባ ልጁን ናፍቆትን ከት/ቤት በሚያመጣበት ሰዓት ነበር እና ደህንነቶች ሲጎትቱት እና ሲያዋክቡት ይህ ህፃን ልጅ ተመልካች ሆንዋል ። እስኪ አስቡት ይህ የሆነው እናንተ ላይ ቢሆን እና ልጃችሁ ተመልካች ቢሆን ? ) ትዳሩን እያሞቀ እና ስራውን በስደትም ይሁን በአገር ውስጥ መኖር ይችል ነበር ። እስክንድር ግን ከልጁ ከናፍቆት እና ከባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል ይልቅ በፍትህ ፤ በነፃነት እና በእኩልነት የተገነባችን ኢትዮጵያ ለልጁም ሆነ ለወገኖቹ ተፈጥራ ማየትን መረጠ ። ነፃነት ፣ ፍትህ እና እኩልነት እያለ እነሆ በቃልቲ ከታሰረ ከስድስት አመት በላይ ሆነው ።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ይህን ግፍ ለባለቤቱ ለሰርካለም ፋሲል ሲነግራት ምን እንደተስማት ለማወቅ በሷ ጫማ ውስጥ መቆም አይጠበቅም ። እንዲህ ዓይነት ግፍ እና መከራ በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም እነሆ 26 ዓመት አለፈ ።

በአንተ ላይ በሆነውና በሚደረገው ነገር ሁሉ “የትግሬው አፓርታይድ ህዉሓት” ዋጋ ይከፍላል ።
——–

በእስማኤል ዳውድ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.