ቦሌ በወረቀት ላይ በተፃፈ መፈክር እና በግድግዳ ላይ ፅሁፎች አሸብርቃ አደረች፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ  እንደ ለሊት ወፍ ካልሆነ ከወያኔ እይታ ተሰውሮ መፈክሮችን በቀን ማሰማት የማይሞከር ነው። ስለሆነም የለሊቱ ግርማ ያላስፈራቸው የስርዐቱ ተቃዋሚዎች በቦሌ ፒኮክ, በ35 ቀበሌ,በ26,እና በተለያዩ ቦታዎች

1) የፍትህ እንጂ የትራንስፖርት ችግር የለብንም !
2) ለነጻነታችን ከዚህ የበለጠ መስዋዕት እንከፍላለን !
3) አሸባሪ አይደለንም !
4) ፍትህ !
   እና የመሳሰሉት መፈክሮች ተለጥፈው አድረዋል ። ይህም ብዙ ነገር የሚያንጸባርቅ ሲሆን ከሁሉም በላይ ነገሩን በለሊት ማድረጉ ምን ያህን ወያኔ አፋኝ መሆኑን እና በምንም አይነት መንገድ ይህ ገዢ በሚገዛበት ዘመን በነጻነት እንደዜጋ ድምጽን ማሰማት የማይሞከር እንደሆነ መረዳት ይቻላል።
           የወያኔ ከከፋ ባህሪው በኢትዮጵያ ላይ ያደረጋቸው ዘረኝነት፣ ስርቆት፣ ዝርፊያ፣ ጨለምተኝነት፣ አውዳሚነት፣ ራዕይ አልባነት፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባህሪይ፣ ቡድንተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጥላቻ፣ ቂም በቀል፣ ጥርጣሬ፣ አለመተማመን፣ጥሎ ማለፍ ወዘተ በትውልዱ ላይ ጥቁር ጥላቸውን እያጠሉ መሆኑ እና ለትውልዱ ተስፋን የሚተልም ሥርዓት ሙጥጥ ብሎ ከመጥፈቱ የተነሳ ጎመን በጤና የማይል ወገን እያስገመገም ነው።
           ሞዴል የሚሆን የፓለቲካ (የመንግሥት) አመራር ማግኘት ሕልም በሆነበት በወያኔ የቁማር ዘመን ለኢትዮጵያ ሉዐላዊነት የሚታገሉ ጀግነው በመነሳታቸው የወያኔ ታሪክ መቋጫ ላይ እንደሆነ ትልቅ ምልከታ አለው።
        ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

10978657_1546202058984325_5162985147593662143_n 1475841_1546202125650985_2431107026042397337_n 1509152_1546202162317648_5009699838496113588_n 1782084_1546202062317658_2434862860400927041_n  10954555_1546202032317661_1199538579719028328_n 10958704_1546202108984320_5548532869537314093_n 10959613_1546202095650988_2330058176076836165_n

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.