ከአሜሪካን የሚመጣው ሲኖዶስ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግ እንጂ ቤተክርስቲያን ሊመራ አይደለም!!` በረከት ስምኦን

ሰበር ዜና`ከአሜሪካን የሚመጣው ሲኖዶስ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግ እንጂ ቤተክርስቲያን ሊመራ አይደለም!!` በረከት ስምኦንየወያኔው የህዝብ ግንኙነት ሰው ወይም ራሳቸዉን ምኒስትር ብለው የሚያስጠሩት አቶ በረከት ስምኦን ዛሬ ማምሻውን የኦርቶዶክስ ቤ/ክ አስመልክቶ ከወዳጆቻቸው ጋር ባደረጉት ዉይይት ቤተ ክርስቲያኒትዋን በመከፋፈል የጽንፈኛ ዲያስፖራዎችን ፖለቲካዊ አላማ በማንገብ አገር በት ከገቡ በሁዋላ ሽብር በመንዛት መንግስትን እና ህዝብን ለማጋጨት የተሸረበ ሴራ ነው ብለዋል:ሲሉ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገለጡ::

የአሜሪካው ሲኖዶስ ነኝ የሚለው የፖለቲካ ቡድን በኢትዮጵያ ዉስት መረጋጋት እንዲኖር የሚሰራ እና ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን የተረጋጋ መንግስት ለመገልበጥ የተዘጋጀ ቡድን ነው ሲሉ ወቅሰዋል::

አቶ በረከት እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ሰላም እና ዲሞክራሲ በልማት አውህዶ ማደግ እንጂ በበርገር የጠገቡ ጳጳሳትን አይደለም ብለው ተወያይ ወዳጆቻችውን  ፈገግ አሰኝተዋል:: እንደ አቶ በረከት አባባል ለእርቀ ሰላም ከመጡት ሰዎቻቸው አንደኛው (ሃይለስላሴ አለማየሁ) ከተቃዋሚ መሪዎች ጋር በተለያየ ጊዜ በመንግስት ደህንነቶች በመታየቱ የህን ጉዳይ ከአቡነ ናትናኤል ጋር ተወያይተንበት ከምታስሩት ከሃገር እንዲወጣ አድርጉት ..አለም አቀፍ ተቃውሞው እንዳይበረታ …የሚል ነገር ስለነገሩን ከሃገር አባረነዋል ሲሉ አቶ በረከት ተንፍሰዋል:እንደ ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች::

አቶ በረከት የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በተመለከተ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ መሆኑ ገልጠው አንዳንድ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ይረዱዋቸዋል እንዲሁም ወደ ፖለቲካ ሽብር ለመቀየር እየለፉ ነው ሲሉ የሚለፉትን ሰዎች ሲም ከመጥከስ ተቆጥበዋል…የሚረዱትንም እንዲሁ…ዲያስፖራው ጽንፈኝነትን ለማስፋፋት እየሮጠ እንደሆን ሳያወሩ አላለፉም::

አሕባሽ የተባለዉን ነገር አንስተው የህ የሃይማኖት ሴክት /ሃራጥቃ / ነው ያሉት አቶ በረከት በህገ መንግስቱ መሰረት መስራት ይችላል ሆኖም ዘየቤው ሽብርተኛ አይደለም እንደለላው ብለዋል::
አቶ በረከት ይህን ሁላ ሲያወሩ የተቀዳላቸው ሻይ በርዶ ነበር::እንደ ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ዘገባ::

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.