የኢሓዴግን መግለጫ አባል ፓርቲዎች ይቀበሊታል ብዬ አላምንም (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

ስለ መግለጫው

1 ኢህአዲግ የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባውን ሲጀምር “ወሳኝ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ብሎ ነበር።” በመግለጫው ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ ሊያረካ የሚችል ወሳኝ ውሳኔ የቱ ነው?

2 በመግለጫው ኢህአዲግ የተግባር እና የአመለካከት አንድነት ፈጥሯል ተብለናል።ኢህአዲግ የአመለካከት እና የተግባር አንድነት ከፈጠረ ይህንን መግለጫ ለመፃፍ ለምን ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኃላ 30 ሰዓት አከባቢ አስፈለገው?

3 የተከበሩ አቶ አባዱላ የህዝቤ እና የድርጅቴ ክብር ስለተነካ ስልጣኔን ለቅቅያለሁ ብለው ነበር።አሁን ወደ ስልጣናቸው መመለሳቸው ተገልፃል።በመግለጫው ውስጥ የህዝባቸውን እና የድርጅታቸውን ክብር የሚመልስ ውሳኔ ተካቷል?ስለዚህ ለክብራቸዉ ስሉ እሳቸው ይህንን መግለጫ በተመለከተ መግለጫ መስጠት ሳያስፈልጋቸው አይቀርም ።

4 የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብን ግንኙነት በተመለከተ በግምገማው ላይ እንደ አጀንዳ ተነስቶ ውይይት እንደተደረገበት ይታወቃል ።በመግለጫው ላይ መሪህ አልባ ግንኙነት በማለት በተደጋጋም የተገለፀ ነገር አለ።በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህ አረፍተ ነገር ከሁለቱ ህዝቦች ግንኝነት ጋር ተያይዞ በተደጋግሚ በብዙ ሰው እየቀረበ ነው። ይህ አረፍተ ነገር ከሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት ጋር የሚገናኝ ነገር አለው? በዚህ ላይ መግለጫውን የሰጠ አካል ሌላ መግለጫ መስጠት ያስፈልገዋል።የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በምንም መልኩ መሪህ አልባ ብሎ መቅርብ እብደት ነው። በተለይ ብአዴን እና ኦህዲድ በዚህ ጉዳይ ላይ አቋማቸውን በተለየ መልኩ ግልፅ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

5 በአጭሩ የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ 18 ቀን የተሰበሰበው ለዚሁ ነው? ለዚህ ለምን 18 ቀን መሰብሰብ ያስፈልጋል? ለምሳሌ በመግለጫው ላይ የተገለፁት ውሳኔዎች ላይ ለመድረስ 8 ሰዓት አይበቃም ወይ? ምን አዲስ ነገር አለው?

” ….መንገድ መዝጋት አይቻልም፣ የግል እና የመንግስት ሚዲያዎች ህዝብን የሚያጋጭ መልዕክት ማስተላለፍ አይችሉም፣ የተፈናቀሉትን መልሰን እናቋቁማለን፣ ከዚህ በኃላም መፈናቀል እንዳይኖር ጠንክረን እንሰራለን፣ -ለኢትዮጵያ ህዝብ የተፋጠነ አገልግሎት ለመስጠት መልሰን የሚናዋቅራቸው መስሪያ ቤቶች ይኖራሉ፣ እስከ አሁን ለበደልንህ በደል ኢህአዲግ ተጠያቅ ነው።ይቅርታም እንጠይቃለን…..” ለማለት ለማለት 18 ቀን ሳይሆን 18 ሰዓት ለምን ይባክናል? ሰዓት አይበዛበትም? እስት ይህ ምን አዲስ ነገር አለው?

ሳጠቃልል በኔ አመለካከት በመግለጫው ኢህአዲግ በሁለት ምክንያት እራሱን የማጥፋት ሙከራ አድርጓል።

ምክንያት 1 – ይህንን መግለጫ አባል ፓርቲዎች ዝም ብለው ይቀበሉታል ቢዬ ማሰብ ይከብደኛል። መነታረካቸው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ።ያ ማለት ኢህአዲግ ወደ ስብሰባው ሲገባ እንደ ነበረው መነታረኩን መቀጠሉ ነው። እኛም ሳሮቹ መረጋገጣችንን መቀጠላችን አይቀርም።

ምክንያት 2 – እኔ ከስብስበው ብዙ ነገር አልጠበኩም።ህዝቡ ግን ከስብሰባው ብዙ ነገር ጠብቋል።መግለጫው ውስጥ ግን ምንም የለም።ይህ ነገር ቁጣ እንዳይቀሰቅስ ፍራቻ አለኝ።

እናም ኢህአዲግ በቅርቡ ሌላ መግለጫ መስጠቱ አይቀርም። መስጠቱ ካልቀረ ደግሞ የውይይቱን ድባብ በሚያሳይ መልኩ ሌላ ያልተቀሸበ ፣ ተስፋ የሚሰጥ እና የሚጨበጥ ነገር ያለበት መግለጫ ቶሎ መስጠት እጅግ ወሳኝ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.