ኢትዮጵያ ከምትበታተን ዝሆን በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል! (ልዑል አለሜ)

ባደግኩበት ሰፈራችን አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ከተለያየ ብሄር ብሄረሰብ የተዉጣጡ ድብልቆች ነበርን የሁላችንም ቤተሰቦች በተለያየ ብሄር ብሄረሰብ ባህልና ስነ ስረአት የታነጸ ስነ አምግባር አላቸዉ ይከባበራሉ ይዋደዳሉ ይጣላሉ ይቅር ይባባላሉ በአንድ እድር ዉስጥ በሀይማኖትና በዘር ሳይነጣጠሉ በፍቅር ኖረዋል ልጆቻቸዉ ሁላችን አብረን መረሬ ጭቃ አቡክተን ድፍርስ ዉሃ አምቦጫርቀን ደረቅ ጸሃይ ሞቀን እርጥብ አየር ምገን አንድም ቀን ሳንነጣጠል አብረን ኖረናል።

ስንወለድ ተከበን ስንታመም ድንገተኛ፣ ፌጦ፣ ጤና አዳም ተበዳድረን… ከአንዱ ቤት አንዱ ቤት ዞረን.. የድስት ቂጥ ፍቀን በፍቅር ኖረን ነበር።
አንድ ቀን በመንደራችን መተላለፊያ መንገድ ላይ በጨርቅ ካልሲ በተሰራ ኳስ እየተጫወትን ሳለ እጅግ የምናከብራቸዉና የምንወዳቸዉ የመንደራችን አባት አቶ አጋፋሪ መጡ ሁላችን አባባ አጋፋሪ ሲመጡ እሮጠን እንከባቸዋለን እያንዳንዳችንን የአናት ጸጉራችንን እያሻሹ ይመርቁን ነበር…. አባ አጋፋሪዉ የሰፈሩ ህጻናት የማእድ ትሪ ነበሩ… እሳቸዉ ቤት ያለዉ መሶብ የኛ ነበር…. ልጆች ብሉ! ይሉናል የሚገርመዉ አባባ አጋፋሪ ከአብራካቸዉ የተወለዱ የ 4 ልጆች አባትም ነበሩ…. ነገር ግን እርሳቸዉ እኛንም ለይተዉ አይመለከቱንም ነበር።
ዛሬ አባባ አጋፋሪ ሲመጡ ከሩቅ ተመልክተን ወደሳቸዉ እሮጠን አባባ አባባ ስንላቸዉ እንደልማዳቸዉ በተራ በተራ አናታችን እየነካኩ ጥያቄ ይጠይቁን ጀመር።

” ልጆች ዜግነታችሁ ምንድን ነዉ አሉ ?
በህይወቴ ለመጀመሪያ ግዜ ነበር ስለ ዜግነት ያሰብኩት… እናም ሁላችንም ዝም አልን አባባ አጋፋሪ በድጋሚ ጠየቁን
” ልጆች ዜግነታችሁ ምንድን ነዉ ?
አሉን ከመሃላችን መሃመድ የሚባለዉ ልጅ ” ኢትይኦጵያ ” አለ ጎበዝ ልጅ አሉት . . .
ከዚያ ቀጠሉ፡፡ ልጆች ማንም ሰዉ ኢትዮጵያ የት ነች ቢሏችሁ እንብርታችሁን አሳዩ ማንም ሰዉ ዘራችሁ የት ነዉ ቢሏችሁ ሆዳችን ዉስጥ በሏቸዉ ልጆች ከእንብርት ጀርባ ባለዉ ሆድ ዉስጥ ብዙ አካል አለ ግን አንዱ ከአንዱ የተለያየ ስራ አለዉ አንዳቸዉም ስራ ካቆሙ ሁሉም ይሞታሉ አሉ።
ማናችንም አልገባንም አባባ አጋፋሪ ሄዱ እኔ ይህንን ቃል ጻፍኩት እስከ ዛሬ አለ በዉስጤ።

ማናችንም በዘር ላይ ከተመረኮዘ ንትርክ እንዉጣ አማራም ኦሮሞም ከንባታ ወይም ጉራጌ ብለን አንነጣጠል በተለይ የመጣንበት መሃበረሰብን እንወክላለን ብለን ስናወራ የስድብ ቃላትን ማስወገድ አለብን አንድ በትልቁ ልናስብበት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር እዚህ መሐበራዊ ሚዲያ ላይ እራስችን እንሞነጭራለን እንጂ የትኛዉም መሃበረሰብ አልወከለንም!
በተለይም ሀውሃት መርህ አልባ ብሎ እስኪሰይመን ድረስ ደርሷል ከዚህ ቀደም በንቀት አከርካሪዉን ከእነ እምነቱ ሰበርነዉ ሲል ሰድቦናል ሌላ ግዜ ደግሞ ጠባብ በማለት ዘልፎናል ህወሃት ሲያሻዉ ትምክህተኛ እያለ ያዋረደን ህዝቦች መሆናችንን እናስታዉስ…… አሁን መርህ አልባ ነን ምክንያቱም እነርሱ የገነቡት የጥሉ ግርግዳ መደርመስ ጀምሯል ይህ ይህ የመደርመስ አደጋ ለህወሃት አስደንጋጭ መሆኑን ተገንዝበናል በመሆኑም መርህ አዘል ትግል ለማድረግ መርህ ሊኖረን ይገባል መርህ የሌለዉ ትዉልድ ሁሌም ሲረገጥ ይኖራል።

መርህ ያለዉን ትግል ለማካሄድ ተደራጁ አንድ ሁኑ ተጠናከሩ ህወሃትን የሚታገሉ ሃይሎችን አግዙ የሃሳብ ልዩነትና ስህተቶች እንዲታረሙ በሃሳብ ተሟገቱ አትሳደቡ የጠላት መሳቂያ ከመሆን ያልዘለለ ትግል ይሰልቻችሁ ይህ ባይሆን ግን እዉነቱ ኢትዮጵያ ከምትበታተን ዝሆን በርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ እንደሚሻለዉ እወቁ።
ዛሬ ተመልከቱ ህወሃት የፖለቲከኛ እስረኞችን እፈታለዉ እያለ ነዉ ይህንን እንደሚያደርግ ቀድመን ተናግረናል ግን እወቁ እኛን መርህ አልባ ባለበት ማግስት ይህን ማለቱ ለምን እንደሆነ እንገነዝብ ተጨማሪ የረገጣ አመታት ከፊታችን ለመዘርጋት ብቻ ነዉ እኛ ግን ከንትርክ የዘለለ ስራ ባለመስራት አንማማል።

ትባንን እንደሆን ባንን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ልዑል አለሜ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.