የአዲስ አበባ ወጣቶች የተቃዉሞ ወረቀቶችን ሲለጥፉና ሲበትኑ አደሩ (ቢቢኤን)

(ቢቢኤን) — በህወሃት አገዛዝ ተንገፈገፍን ያሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች የተቃዎሞ ወረቀቶችን ሲለጥፉና ሲበትኑ ማደራቸው ታወቀ። በዘር በሐማኖት ሳንለያይ ለተቃዉሞ ወጥተናል ያሉት ወጣቶች የአንድ ብሔር የበላይነት ያለበት አገዛዝ ህዝባዊ በሆነ ስርዓት እንዲቀየር ተግተን እንሰራለን ብለዋል።

አገሪቷ ዉስጥ የተንሰራፋው ጭቆና እንዲያበቃ መልእክታቸውን ያስተላለፉት ወጣቶች ለነጻነት መጠማታቸውንና በጽኑ ለዉጥን ፈላጊ መሆናቸውን አሳውቀዋል።ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ያደረጉትን ትግል በእስርና በግድያ ማፈን አይቻልም፣የህዝብ ዉክልናን ተቀብለው እስር ቤት ከሚሰቃዩት ወኪሎች ጎን እንቆማለን፣ ለነጻነት ለእኩልነት የሚደረግ ትግል ምርጫችን ሳይሆን ግዴታችንም ነው፣ ኢትዮጵያ ወይም ሞት! ሲሉ ጠንከር ያለ መልእክት ለህወሃት መራሹ መንግስት ልከዋል።

የፌዴራል ፖሊስ የቄሮን ንቅናቄ አፍናለሁ ማለቱን አንቀብለም ያሉት የአዲስ አበባ ወጣቶች «የአዲስ አበባ ቄሮዎች መልእክት…በቅርብ ቀን አራት ኪሎ እንገናኝ» በማለት ገልጸዋል።መልእክታቸውንም በማስፋት «አዲስ አበባዎች ከተበደሉት የአማራና የኦሮሞ ወንድሞቻችን ጎን እንቆማለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ቢቢኤን ተጨማሪ የቪዲዮና የምስል መረጃዎችን ከሰዓታት በሗላ ያቀርባል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች መልእክት፡
• በማሰር በመግደል የሙስሊሙን ጥያቄ ማዳፈን አይቻልም!
• የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አሁንም ለረጅም ትግል ተዘጋጅተናል!
• የትግል መርሃችንና አንድነታችን ምንጊዜም የማንነታችን ጽኑ መሰረቶቻችን ናቸው!
• ግዙፍ ህዝባዊ ንቅናቄያችን በሓይል እርምጃ አይገታም!
• ውድ ኮሚቴዎቻችን ሆይ፡ ዛሬ በእስር ብትሆኑም ደማቅ ታሪካችሁ ዝንተአለም ደምቆ ይኖራል!
• ህዝበ ሙስሊሙ ትንኮሳ እንደማያደናቅፈው ሁሉ ሽንገላም አያማልለውም!
• ለነጻነት ለእኩልነት የሚደረግ ትግል ምርጫችን ሳይሆን ግዴታችንም ነው!
• የአንድ ብሄር የበላይነት ያለባት ሃገር ማየት አንፈልግም!
• የአዲስ አበባ ቄሬዎች መልእክት በቅርብ ቀን አራት ኪሎ እንገናኝ!
• ድፍን ሀገር እስር ቤት ሆና እያለ እስር ቤቶች ዘግተናል ማለት ፌዝ ነው!
• አዲስ አበባዎች ከተበደሉት የአማራና የኦሮሞ ወንድሞቻችን ጎን እንቆማለን!
• ኢትዮጵያዊነት በኢትዮጵያዊነታችን ያገኘነው ነው!
• ኢትዮጵያ ወይም ሞት
• ዘረኝነት ይውደም!ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
• ከወያኔ ነጻ መውጫ ቀን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው!

Protest pamphlet distributed in Addis Ababa, Ethiopia.

Protest pamphlet distributed in Addis Ababa, Ethiopia.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.