መቅደላ –  የዐኅኢአድ ልሣን የዐማራው ኅልውና መጠበቅ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው!

ሁለት ሺ አሥር የትግሬ-ወያኔ ከፋፋይ አገዛዝ ማክተሚያው ወይስ እንዳለፉት ሁሉ ሞቶ መነሻው?

ከመነሻው ወያኔ አንግቦት የተነሳበት ዓላማው የተሳሳተ፣ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህም የተሳሳተ ዓላማ በተለያዩ ወቅቶች ፣ዓላማውን ያልደገፉ ቡድኖች ባነሷቸው ጥያቄዎች የመከፋፈል እና የመፈራረስ አደጋዎች በከፍተኛ ደረጃ እየጋረጡበት እንደ እባብ ሞቶ አፈር እየላሰ ከዚህ የደረሰ መሆኑ ይታወቃል። የትግሬ-ወያኔን ለመበታተንና ለማፍረስ የሚችሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ተሟልተው እያለ፣ ገፍቶ የሚጥል ጠናካራ አገራዊ ዕራይ ያነገበ ድርጅት አለመኖር፣ላለፉት 43 ዓመታት አገርና ትውልድ የሚያጠፋ ሥራ እንዲሠራ ሠፊ ዕድል አገኘ። በራሱ ውስጥ የተፈጠሩትን ችግሮች በመጠቀም ገፍቶ መጣል ባለመሞከሩ፣ ወያኔ ድክመቶቹን የጥንካሬውና የመታደሻው መገለጫዎች እያደረገ ሕዝብን ለማተለል ተጠቀመበት። የ1969 እና 1970 ዎቹ «የሕንፍሽ ሕንፍሽ» የትግራይ አውራጃዎች ልዩነት እንቅስቃሴ፣ የድርጅቱን መሥራቾችና መሪዎች የነበሩት አረጋዊ በርሃና ግደይ ደብረጽዮን ከድርጅቱ የማባረር ሂደት፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ማግሥት በነተወልደና መለስ የተፈጠረው ክፍፍል የትግሬ-ወያኔ ወደ መቃብር አፋፍ ያደረሱት ክስተቶች ነበሩ። ለነዚህ ችግሮች ያበቁትም ጠንካራ ተቃዋሚ ኖሮና በርሱ ተገፍቶ ሳይሆን፣ ዓላማቸው ስሕተት በመሆኑ፤ኢትዮጵያዊነት በመንፈስ፣ ዐማራው በፀሎት፣ በትዕግሥትና ትዕግሥቱን እንደፍራት ሲቆጥሩት ደግሞ ከ2008 ዓም ጀምሮ በመጡበትና ሊገባቸው በሚችለው ቋንቋ ማነጋገር መጀመር ለሌላ ዙር የትግሬ-ወያኔ ክፍፍልና መፈራረስ ሠፊ በር እንደከፈተ እያየን ነው።

በሌላ በኩል ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በመካከለኛው የአገሪቱ ክፍለ-ሀገሮች፣ አውራጃዎችና ወረዳዎች የተቀጣጠለው የኦሮሞ ወጣቶች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተከታታይነት፣ ከዐማራው የጎበዝ አለቆች እንቅስቃሴ ጋር ጎን ለጎን መፋፋም፤ «ከየትኛውም ጊዜ ከነበሩት አገዛዞች በበለጠ የሕዝቡን አንድነት አረጋግጫለሁ፣ ሰላም አስፍኛለሁ፣ ከፍተኛ የሆነና በያመቱ 11% ዕድገት አስመዝግቤአለሁ፤ዲሞክራሲያዊ አሠራርና ባሕል እየገነባሁ ነው፣ የዚህም መሠረቱ ሕዝቡ ወዶ ያጸደቀው ሕገ-መንግሥት የአገዛዙ መመሪያ በመሆኑ ነው» እያለ፣ በሚለፍፍበት ጊዜ፣ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ በመላ አገሪቱ ዳር እስከ ዳር መቀጣጠል ያሳደረበት ከፍተኛ ጫና ፣የሰላምና የብልጽግናዬ መስተዋት ነው የሚለውን «ሕገ-መንግሥት» አግዶ ወታደራዊ አገዛዝ ለ10 ወሮች አስፍኖ ሕዝቡን በገፍና በግፍ መግደሉ፣ ማሰሩና ማሰቃየቱ ይታወቃል። …

GDE Error: Unable to load requested profile.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.