የታሰሩት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በቤተሰብ እንዳይጠየቁ ተከልክለዋል

ትናንት አራዳ አካባቢ የታሰሩት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ፒያሳ ጣይቱ ፖሊስ ጣቢያ፣ ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ እና ራስ ደስታ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ። ማታ ጣይቱ ታስረው ከነበሩት መካከል የተወሰኑት ወደ ራስ ደስታና ወረዳ 9 ተዛውረዋል።

ወይንሸት ሞላ፣ አዲሱ ጌታነህ እና ይድነቃቸው አዲስ ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ። አምባሳደርና ሌሎች አካባቢዎች የተያዙት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የት እንደታሰሩ አልታወቀም።

አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ ተከልክለዋል። በቤተሰብ እንዳይጠየቁ የተከለከሉ 22 የሚሆኑ እስረኞች ስም ዝርዝር በፖሊስ እጅ ለማየት ችለናል። ቤተሰብ የእስረኛ ስም ሲያስመዘግብ ፖሊስ እስረኛው ከተከለከሉት ስም ዝርዝር ውስጥ አለመካተቱን በማረጋገጥ ይመዘግባል። እንዳይጠየቁ የተከለከሉት ምግብ ብቻ ይገባላቸዋል።

አዲሱ ጌታነህ እና ይድነቃቸው አዲስ እንዳይጠየቁ በመከልከላቸው ምክንያት ማስመዝገብ አልተቻለም። ወይንሸት ሞላን አስመዝግቤ ገብቼ የነበር ቢሆንም አንድ የፖሊስ አዛዥ እንድወጣ ካደረገ በኋላ ከነባር እስረኛ ውጭ በቤተሰብ እንዳይጠየቅ ለመዝጋቢው ፖሊስ ትዕዛዝ ሰጥቶ ተመልሷል። ወይንሸትን ጨምሮ ሌሎች ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው ከተባሉት ስም ዝርዝር ያልተካተቱ ቢሆንም እነሱም እንዳይጠየቁ ተከልክለዋል።

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.