ሰበር መረጃ …..እስረኞች ይፈቱ ከሚለዉ ስሌት ጀርባ የጨዋታዉ አቀናባሪ የህወሃት ብሐራዊ መረጃ ሐይለማርያም ላይ ቀልዶበታል

ልዑል አለሜ

ህወሃት እየመከረ ነዉ።
ጥር 5/2010
በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ቆንጮ ላይ የተቀመጠዉ ግለሰብ የተሰጠዉን ወረቀት ካነበበ ወዲህ የፍቺዉን ሂሳብ ባለማወራረድ አለም አቀፋዊ ታሪካዊ ጥፋት ሰርቷል!
የህወሃት ፈላጭ ቆራጮች ዉስጣዊ ስብሰባ ላይ ሐይለማርያም ህዝብን እንድዋሽ አድርጋችሁኛል ብሎ መጠየቅ ሲገባዉ ምን ይሻላል ? የሚል የተማጥኖ አረፍተ ቃል ሰንዝሯል።
የህወሃት ብሄራዊ መረጃ መግለጫዉ ጥናት ያልተደረገበት እና ሆን ተብሎ የተቀናበረ ዉስጣዊ ደባ ነዉ በሚል አጣሪ ኦፕሬሽን መድቦ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ከዉስጥ ያፈተለከ መረጃ ጠቁሟል።
ህዝብን፣ አለማቀፍ ሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን፣ እንዲሁም የተለያዩ የዉጭ ሐይሎችን በተለይም ታላላቅ የዜና አዉታሮችን ሁሉ በገሓድ መዋሸቱን ከምንም ያልቆጠረዉ የህወሃት ብሄራዊ መረጃ ሙሉ በሙሉ በህወሃት ባለስልጣናት ድጋፍ አግኝቶ በመፎከር ተጠምዷል።
ከህዝባዊ እንቢተኝነቱ ተንፈስ ብለናል ይህንን የመሳሰሉ መግለጫዎች የህዝብን የልብ ትርታ እንድናዳምጥም እረድቶናል ስለዚህ የተወሰኑ እስረኞችን በመፍታት ሂደቶችን ማዝገም እንችላለን የሚል ትልቅ ተንኮልም በምጣዱ ስር በተለኮሰዉ እሳት ዉሃ እያርከፈከፍን ነዉ የሚል ቃና ያለዉ ንግግር ያቀረቡት የህወሃት ባለስልጣን ዳጎስ ያለ ጭብጨባ እንደተለገሳቸዉ ምንጩ ጠቁመዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.