የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል፤ በሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ስም የተቀመጠውን ገንዘብ ወደ ራሱ አካውንት ለማስገባት ሲነጋገርበት የነበረው ኢሜይል በሃዱሽ ካሱ ይፋ ሆነ

ህብር ሬድዮ

የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሃዱሽ ካሱ የደብረጽዮንን ምስጢሮች “ፌስቡክ ገጼ” ሃክ ተደርጓል በማለት ለአደባባይ ማብቃታቸውን ቀጥለዋል:: የደብረጽዮንን የወሲብ ገመና አደባባይ ያወጡት አቶ ሃዱሽ ዛሬ ደግሞ “17 ዓመት ወደ ኋላ ልመልሳችሁ” በሚል አንድ ምስጢር የያዘ የኢሜይል ልውውጥ አደባባይ በማውጣት የአዲሱን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ምስጢሮችን ማጋለጣቸውን ዘሐበሻ ዘግቧል።

ኢሜይል ልውውጡ የተደረገው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2001 ዓ.ም ሲሆን የቀድሞው የደህንነት ሹም ባለስልጣን አቶ ክንፈ ገብረመድህን ከተገደሉ በኋላ በ እንግሊዝ ሃገር (National Westminister Bank, UK) ያላቸውን ገንዘብ ወደ ራሳቸው (ደብረጽዮን) አካውንት ለማዘዋወር ያደረጉትን እንስቃሴ ያሳያል:: ማሌዥያ ከሚገኘው አማካሪያቸው አንድሪው ጋር ያደረጉት ይኸው የኢሜይል ልውውጥ እንደሚያሳየው የማሌዢያው አማካሪ ደብረጽዮን ገንዘቡን ለማዘዋወር ከመሞከራቸው በፊት ስለክንፈ ገብረመድህን የሞት ሰርተፍኬትና ሌሎች ማስረጃዎችን እንዲያቀርቡና ዝውውሩን ሕጋዊ ለማስመስልና ችግር ውስጥ እንዳይወድቁ ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ ይመክራል::

ከክንፈ ገብረመድህን ልጅ ልዑል ክንፈ እውቅና ውጪ አቶ ደብረጽዮን ይህን በ እንግሊዝ የሚገኝ ገንዘብ ወደ ራሱ አካውንት ለመክተት ያደረገውን ሙከራ አቶ ሃዱሽ ሲገልጸው “ገንዘቡ የክንፈ ልጅም የደብረጽዮንም ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተዘረፈ ነው” ይለዋል::

በዚሁ ኢሜይል ልውውጥም አንድሪው ለደብረጽዮን ሚስት እንደሚፈልግለት የገለጸበት ይታያል::

የኢሜይል ልውውጡን ይመልከቱት::

በነገራችን ላይ: የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ ደገፉ በሃገር ቤት በሚያሳትማት መዲና ጋዜጣ ላይ ከደህነንቱ ሹም ክንፈ ገብረመድህን ግድያ በስተጀርባ የመለስ ዜናዊ እጅ አለበት በሚል አንድ የሕወሓት ሻለቃ የሰጡትን ቃለምልልስ ጠቅሶ በመዘገቡብ በማዕከላዊ እስር ቤት ስቃይ ተፈጽሞበታል::

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.