የትግራይ ህዝብ ሆይ …ተነስተህ ከህዝብህ ጎን የምትቆምበት ስዓቱ አሁን ነው!!! (አገር ሰላም)

ወያኔ የዘር ግጭት እንዳይቀሰቀስ እያለ ይሄው ወጣቱን በስናይፓር ግንባር ግንባሩን እያለ ጨረሰ።
የትኛው ዘር ከየትኛው ዘር ጋር እንድሚጋጭም አናውቅም ። 27 ዓመት በሙሉ ጥላቻንና ዘረኝነትን ሲሰብክ ኖረ ይሄው ዛሬ የዘራው በቅሎ ውጤቱን እየተመለከትን ነው። ለዘመናት ተከባብሮና ተቻችሎ የኖረን የትግራይ ህዝብ በሌላው ብሄር ዘንድ እጅጉን እንዲጠላ አደረገ።
“እኔ ከሌለሁ(ወያኔ) ሌላው ዘር አጋድሞ ያርድሃል” በሚል አጉል ፍልስፍና ህዝቡን(የትግራይን) በፍራቻ ሌላ አማራጭ የለለው እስኪመስል ድረስ ከሌላው ዘር ጋር እየደጋገመ ያጋጨዋል፣ያስጠላዋል ወ..ዘ.ተ…………
የኢትዮጵያ ህዝብ በባህሉም በወጉም ጨዋ ህዝብ ነው!!! ፍርሃ እግዝአብሄር ያለው። አይደለም ሰውን አጋድሞ ሊያርድ የሚመገበውን እንስሳ እንኳን በስንት ፀሎት ባርኮና ቀድሶ ነው የሚያርድ… እንዴት ይህን ነገር ወያኔ ለፖለቲካው ፍጆታ እንደሚያውለው የትግራይ ህዝብ መገንዘብ አቃተው? እየፈሰሰ ያለው ደም የወንድሞቹ ደም አይደለም ወይ? ይህ ህዝብ ነገ ይህ አስከፊ ስርዓት ሲወድቅ ለበቀል እማይነሳ ይመስላቹሃል ? በየትኛውም የሂሳብ ቀመር ለማሰብ ሞክሩ ይህ ህዝብ ቻይ እና ታጋሽ ነው ትግስቱ ግን እየተሟጠጠ ብሶቱ ገንፍሎ እየወጣ ሰደድ እሳት እየሆነ መድረሻ ሳያሳጣችሁ ቆም ብላችሁ ትንሽ ሰክናችሁ ወደ ኋላ ብትመለከቱ ተግቢ ይመስለኛል።
አገር ሰላም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.