ወያኔ በአማራው ላይ የሚፈፀመው ኢ-ሠብዓዊ የዘር ማጥፋትና የዘር ማፅዳት እኩይ ዘመቻ ከጫካ ጀምሮ አስቦበትና በፕሮግራም ነድፎት የመጣው መሆኑ ይታወቃል፡፡በዚሁም ናዚያዊ የሆነውን ፀረ-አማራ እና ፀረ-ኦርቶዶክስ ተግባሩ በንፁሃን ላይ በወልዲያ ከተማ የጥምቀትን በዓል ለማክበር በወጡ የአማራ ወገኖቻችን ላይ ሆን ተብሎ በተካሄደው ጭፍጨፋ ድርጅታችን አዴኃን ጥልቅ ሀዘን እና ቁጣ ተሰምቶታል፡፡
በደረሰውም ጭፍጨፋ ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን እና ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው የአማራ ህዝብ ትልቅ መፅናናትን ይመኛል፡፡
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ህወሃት ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ ባደረሰው የዘመናት የዘር ማጥፋት ዘመቻ፣ጅምላ ስልታዊ የዘር ማፅዳት ሴራ፣የዘመናት ምርኮና ባርነት፣ዘረፋና ማሳደድ እንዲሁም አሰቃቂ ግፍና በደል በመንገፍገፍ አማራን እንደ ህዝብ ኢትዮጵያ ሀገራችንን እንደ ሀገር ከጥፋት ለማዳን ነፍጥ አንስተን ፀረ-ህወሃት ወያኔ ትግሉን ከተያያዝን አመታት ያስቆጠረ ሀቅ ነው፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ድርጅታችን አዴኃን የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ አመራሮቹ እና አባላቱ ግንባር ተገኝተው ከድርጅቱ ስራ አስፈፃሚዎችና ከሰራዊቱ አባላት ጋር የሀገር ቤቱን የትግል አካሄድና ወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ላይ በሚወያዩበት ወቅት ይህን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ መካሄዱን ሲሰማ በሠራዊቱ ላይ ወገናዊ መራራ ሀዘን እና ትልቅ ቁጣ አሳድሮበታል፡፡
አዴኃንም እንደ ድርጅት በአማራ ወገኑ ላይ የደረሰውን ኢ-ሰብዓዊ ጭፍጨፋ በሀዘን መግለፅ ብቻ ተወስኖ የሚያልፈው አለመሆኑንና በቆራጥ ትግሉና ልጆቹ አፀፋዊ ፀረ-ህወሃት ወያኔ ብትሩን የሚዘረጋ መሆኑን በጠንካራ አቋም ያሳውቃል፡፡
በመጨረሻም ለመላው የአማራ ህዝብ ባለፉት 27 ዓመታት እናም ከዛም በፊት በነበሩት የአማራው የእልቂት ዘመናት ወገኖቻችን ከመካከላችን ተነጥለው ሲያልቁ ከንፈር መምጠጣችንና ነብስ ይማር ማለታችን ከሞት አላዳነንም፡፡ ከእልቂት አላዳነንም፡፡ትላንትም አላደነንም ነገም አያድነንም፡፡እራሳችንን ከታወጀብን እልቂት ማትረፍ የምንችለው በአማራነታችን ተደራጅተን የመጣብንን ጠላት ፊት ለፊት መጋፈጥ ስንችል ብቻ ነው፡፡

የአለቅነው አልቀን ወያኔ ይደመሰሳል ፤አማራው ከታወጀበት የዘር ማጥፋትና ማፅዳት እራሱን ይታደጋል!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ(አዴኃን)
ጥር 13÷2010 ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.