ሰበር መረጃ….በወልድያ ከተማ ሳምንታዊው የማክሰኞ ገባያ እንዲበተን ተደርጓል


በወልድያ ከተማ ሳምንታዊው የማክሰኞ ገባያ እንዲበተን ተደርጓል። ወጣቶች “ የወገኖቻችን ደም ሳይደርቅ ግብይት ማድረግ አይቻልም” በሚል ምክንያት እንዲበተን አድርገዋል።
ከወልድያ 20 ኪሜ አካባቢ በምትርቀው ጎብዬ ከተማ ላይ መኪኖች ወደ ሰሜን እንዳይጓዙ ተከልክለዋል። መከላከያ የወጣቶችን ተቃውሞ ለመስበር ወደ አካባቢው መጓዙ ታውቋል፡
ሃራ ላይ ትናንት ምሽት 2 ሞተር ሳይክሎችና አንድ ተሽከርካሪ ተቃጥሎ አድሯል።
የመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይል እና አድማ በታኞች ከከተማ እንዲወጡ ተደርገዋል።
ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለና ወጣቶች በሂደት ስለሚወስዱት እርምጃ እየተነጋገሩ ነው።

ESAT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.