ሰበር_መረጃ መርሳ & ቆቦ 

1) በአማራ ክልል ስሜን ወሎ መርሳ ከተማ ዛሬ ቅዳሜ ረፋድ በተቀሰቀሰ ፀረ አገዛዝ ተቃውሞ አስር ሰዎች መገደላቸው ተሰማ። የጀርመን ድምፅ ራዲዮ እንደዘገበው በቅርቡ በወልዲያና ቆቦ የተፈፀመውን ግድያ ተቃውመው አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ተጋጭተዋል። የመንግስት ተቋማትና የሰርዓቱ አገልጋይ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች መኖሪያ ተቃጥሏል። አንድ የመንግስት ሹም በነዋሪዎች መገደሉም ተዘግቧል።

2) ሰበር_መረጃ መርሳ & ቆቦ
# የህወሓቱ ባንዳ የሆነው አለምነው መኮነን በቆቦ ሕዝብ ተዋረደ!
# መርሳ በህወሓት አመራሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ!
# በወልዲያ ከተማ የጦር መሳሪያና ተዛማች ዕቃዎችን የጫነ ተሽከርካሪ ላይ እርምጃ ተወሰደ!
# ዛሬ ጥር 19 ቀን 2010 ዓ/ም በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማ እና ዙሪያው የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ እንቢተኝነትና አመፅ ለማስቆም እና እንደለመደው ለህወሓት ባሪያ ሁኖ ሕዝቡንም ባሪያ ለማድረግ ተልዕኮ ተሸክሞ ሕዝብ በመሰብሰብ ለመስበክ ሲጀምር ሕዝቡ በአንድ ድምፅ “አንተ ማነህና እኛን የምትሰበስበን ? እየሞትን ያለነው እኛ እየተሰቃየን ያለነው እኛ አሰቃዩ እና ገዳዩ ደግሞ ህወሓት እሱን መቃወም እና ያስገባውን የህወሓት ገዳይ ሰራዊት እንዲወጣ ማድረግ ሲገባህ በአሁኑ ሳዓት ስለ ሰላማዊ ትግልና ጥያቂያቹሁን በሰላማዊ መንገድ ጠይቁ አሁን የተነሳው ነገር የፀረ ሕዝቦች እንቅስቃሴ እንጅ የሕዝብ አይደለም እያልክ ልትሰበክ መምጣትህ እጅግ አሳፋሪ እና አስነዋሪ ስራ ነው በመሆኑም አንተ አድርባይ ፡ ቆሻሻና የህወሓት ተላላኪ ነህ ውጣ ” በማለት ተዋርዶ ከአዳራሹ ወጥቷል ፡፡ ሕዝቡም በአንድ ድምፅ የጀመረውን ትግል እንደሚቀጥል እና ከአርበኞች ጎን እንደሚቆሙ በዚህ አጋጣሚ ቃላቸውን አድሰዋል ፡፡ በተያያዘ ዜና በሰሜን ወሎ ወደ ደሴ አቅጣጫ በምትገኘው ከተማ መርሳ ሕዝባዊ እንቅስቃሴው የቀጠለ እና አርበኞችም በህወሓት ደህንነቶችና ወታደራዊ አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል በዚህ እንቅስቃሴ ላይ የህወሓት ሰዎች ህወሓት ያስታጠቃቸውን መሳሪያ በማውጣት በሕዝብ ላይ በመተኮሳቸው በተለይም አንድ የህወሓት ዳኛ ተኩሶ አንድ አርበኛ ወጣት በመግደሉ በእሱ እና በመሰሎቹ ላይ የአፀፋ እርምጃ ተወስዶበታል ፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ በወልዲያ ከተማ ንብረትነቱ የህወሓት የሆነ የጦር መሳሪያ እና ሊሎች ነገሮችን የጫነ አሲይዙ ተሽከርካሪ በተወሰደበት እርምጃ ሙሉ በሙሉ ተቃጥላል ፡፡ በአሁኑ ሳዓት ሕዝባዊ አመፆች በተነሱባቸው ከተማዎች የህወሓት ወታደሮች እንደ ጊዜያዊ መጠለያ እና ማረፊያ እየተጠቀመባቸው ያሉ የስርዓቱ ተቋማት ላይ እርምጃዎች እየተወሰድ ይገኛል ፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ሳዓት ህወሓት መራሹ ዘረኛ ስርዓት ንፁሀንን እየገደለ መግዛት አይቻልም የነፃነት ጊዜው አሁን ስለሆነ በሁሉም አቅጣጫ እዲነሳ ጥሪ ማቅረብ እንወዳለን ፡፡ዝርዝር ነገሮችን እና መረጃዎችን እየተከታተልን ለሕዝብ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡ ድል ለሕዝብ


3)

ተደራዳሪ ፓርቲዎች ሁሉም ፖለቲከኞች እስኪፈቱ ለድርድር አንቀመጥም አሉ

መኢአድ እና ኢዴፓን ጨምሮ በጋራ ከገዥው ፓርቲ ጋር ለድርድር የቀረቡ 11 ፓርቲዎች፤ በድርድሩ ቀጣይነት ላይ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡ ሲሆን ኢራፓ በበኩሉ ከድርድሩ ሙሉ ለሙሉ ራሱን አግልሏል፡፡
አስራ አንዱ ፓርቲዎች ከፀረ ሽብር አዋጁ 4 አንቀፆች እንዲሻሻሉ፣ 6 አንቀፆች ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዙ እንዲሁም 5 የሰብአዊ መብት አያያዝ ድንጋጌዎችን የያዙ አንቀፆች እንዲጨመሩ ሃሳብ አቅርበው የነበረ ሲሆን ኢህአዴግ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን “ይታያሉ” በሚል መቀበሉንና ይጨመሩ ከተባሉትም በተለይ መርማሪዎች በተጠርጣሪዎች ላይ የመብት ጥሰት ሲፈፅሙ በህግ የሚጠየቁበት አንቀፅ እንዲካተት የቀረበውን ጥያቄ መቀበሉን የፓርቲዎቹ ዋና ተደራዳሪ አቶ ሙሉጌታ አበበ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡
“የሽብር ድርጊት ለመፈፀም የዛተ” የሚለውን የህጉን ድንጋጌ ጨምሮ የፋክስ፣ ስልክና ሌሎች የግል መልዕክት ልውውጦችን መጥለፍ የሚፈቅደውን አንቀፅ እንዲሰረዝ ከጠየቋቸው መካከል መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሙሉጌታ፤ ኢህአዴግ ሁሉንም እንዲሰረዙ የተጠየቁ አንቀፆች፣ አልቀበልም ማለቱን አስታውቀዋል፡፡
እንዲሰረዝ ከተጠየቁ አንቀፆች መካከልም ፖሊስ ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃ ተጠቅሞ የተለያዩ የምርመራ ናሙናዎችን (አሻራ፣ የሰውነት ፈሳሽ የመሳሰሉ) መውሰድ ይችላል የሚለው እንደሚገኝበት የጠቆሙት አቶ ሙሉጌታ፤ ይሄም በገዥው ፓርቲ ተቀባይነት አላገኘም ብለዋል፡፡
በቀረቡለት 16 ያህል የሚሻሻሉ፣ የሚቀነሱና የሚጨመሩ አንቀፆች ጉዳይ ላይ ኢህአዴግ ግልፅ አቋም አለመያዙን የጠቆሙት አቶ ሙሉጌታ፤ በግልፅ የተቀበሉት የሰብአዊ መብት የጣሰን መርማሪ ተጠያቂ የሚያደርግ ህግ ማዘጋጀት የሚለውን ነው ብለዋል፡፡ ኢህአዴግ ተጠያቂ የሚያደርገውን ህግ አዘጋጅቶ ለማቅረብ መስማማቱንም አቶ ሙሉጌታ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡
ተቃዋሚዎች ለድርድሩ ቀጣይነት ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸውን ያወሱት አቶ ሙሉጌታ፤ ኢህአዴግ አዋጁ በህግ ባለሙያዎች የሚሻሻለው ተሻሽሎ፣ የሚጨመረው ተጨምሮ ለድጋሚ ውይይት እስከሚቀርብ በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውይይቱን እንዲቀጥል ቢጠይቅም ይህ ሃሳብ በተቃዋሚዎች ተቀባይነት አለማግኘቱንና የፀረ ሽብር አዋጁ ሳይሻሻልና አጠቃላይ መግባባት ሳይደረስበት ወደ ሌላ አጀንዳ ማለፍ እንደማይፈልጉ ግልፅ አቋም ማንፀባረቃቸውን አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲ አባል እስረኞች ሳይፈቱ ድርድሩን መቀጠል እንደማይችሉ መግለፃቸውንም አቶ ሙሉጌታ አስታውቀዋል፡፡
ከመኢአድ፣ ከመድረክ፣ ከሰማያዊና ከሌሎች ፓርቲዎች 512 ያህል ፖለቲከኞች መታሰራቸውን የሚጠቁም መረጃ እንዳላቸው የገለፁት አቶ ሙሉጌታ፤ ከእነዚህ መካከል እስካሁን የተፈታ አለመኖሩንና ከመኢአድ ብቻ ከታሰሩ 120 አመራሮችና አባላት መካከል አንድ ሰው ብቻ መፈታቱን አስታውቀዋል፡፡
ኢህአዴግም የፀረ ሽብር አዋጁን በህግ ባለሙያዎች አሰርቶ በድጋሚ ለውይይት እንደሚጠራቸው ቃል መግባቱን አቶ ሙሉጌታ ጠቁመዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ “ኢትዮጵያውያንን ዒላማ ያደረገ የፀረ ሽብር አዋጅ አያስፈልግም፣ ኢትዮጵያ ለአለማቀፍ ሽብርተኝነት የተጋለጠች እንደመሆኑ አለማቀፍ ደረጃ ያለው ህግ ነው መዘጋጀት ያለበት፤ በሽብርተኝነት የተፈረጁ የትጥቅ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ድርጅቶች ጉዳይ በወንጀል ህጉ ቢታይ በቂ ነው” የሚሉ የመደራደሪያ ሃሳቦችን አቅርቦ እንደነበር የገለፀው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) በበኩሉ፤ ሃሳቦቹ ተቀባይነት ባለማግኘታቸውና አካሄዱ ውጤት የማያመጣ መሆኑን በመረዳቱ፣ ሙሉ ለሙሉ ከድርድሩ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡

ምንጭ አዲስ አድማስ

4)

አሁን በዚህ ሰዓት ስለ 7… ቤት ወሎ አመፅ አጠቃላይ #መረጃ ስለመስጠት ።

— የመርሳ ከተማ ዳኛ አቶ ከፈለኝ ወደ ህዝብ ተኩሶ 2 ሰዉ በመግደሉ በተወስዶበት እርምጃ ተገድሏል።
— የሀብሩ ወረዳ ፍርድ ቤት ተቃጥሏል።
— በርካታ ቤቶች (የሥርዓቱ ደጋፊዎች ቢሆኑም) እየወደሙ ነው።
— አሮጌዉ ገበያ አካባቢ ሁሉንም ጽ/ቤቶች የያዘዉን የብአዴን አስተዳደር ህንፃ እና ፖሊስ ጣቢያ ወድሟል።
— ንብረትነቱ የግል የሆነ የወያኔ ወታደሮችንና መሳሪያዎችን ጭኖ ወልዲያ የገባ FSR አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ህዝብ እርምጃ ወስዶበት ሙሉ በሙሉ ወደመ።
— ወልዲያ ላይ የሥርዓቱ ደጋፊ ትግሬዎች ሌሊት ላይ ያልታወቀ በርካታ ነገር በመኪና ጪነው ሲወጡ ሕዝቡ ቀምቶ አቃጥሎታል።
— ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቆቦ በከፍተኛ ሁኔታ በአጋዚ ቆስለው ወደ ወልዲያ የሔዱ ወጣቶች ሕክምና ማግኘት አልቻሉም፡።
— ሌሊት ላይ የተለቀሙ ወጣቶች ወደ ሐራ በኩል ሆራ የተባለ የማሰቃያ ቦታ እንደተወሰዱ ነው የተገለጠው።
— በቆቦ ከተማ ህዝብ በስታዲዩም ገዱ ይመጣል ብሎ ሊወያይ ሲጠብቅ ያልተጠበቀው ትልቁ ባንዳ አለምነው መኮነን በመምጣቱ ከፍተኛ ውርደት ተከናንቦ ተሸኝቷል፡፡

ቀድመን ተናግረን ነበር በራያ ፣ የጁ ፣ ሳይንት ፣ ዋድላ ደላንታ ፣ ከላስታም ፣ ከአገዉ ፣ ጃማ ፣ ከሚሴ ፣ ቦረና ይሁን የትኛዉም የወሎ ታሪካዊ ግዛት ላይ ህዉሀት ጥቃት ቢፈፅም አፀፋዉ ከባድ እንደሆነ ተናግረን ነበር።

?ለማይቀረዉ የመላዉ ወሎ አመፅ

ደሴ ፣ ኮምቦልቻ ፣ አጅባር ፣ ደብረሲና ፣ ሸዋሮቢት ፣ ሰንበቴ ፣ አጣዬ ፣ ካራቆሬ ፣ ከሚሴ ፣ ባቲ ፣ ጨፋ ፣ አንቻሮ ፣ ገርባ ፣ ደጋን ወዘተ …ተዘጋጁ ብለዋል ።

“ከፋኖና, ከጎበዝ አለቃ” የተሰጠ መግለጫ ።

5) ESAT News  መረጃ ወልቂጤ
ባለፈው ረቡዕ የወልቂጤ ከተማ ህዝብ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ለዛሬ የተቀጠሩት በህዝብ የተመረጡ የኮሚቴ አባላት ከጉራጌ ዞንና ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል። ባለስልጣናቱ የአንድ ሳምንት ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የኮሚቴው አባላት እስከዓርብ ድረስ ምላሽ ካላገኙ ለህዝቡ እንደሚያሳውቁ አስጠንቅቀዋል። ለኢሳት በደረሰ መረጃ ባለስልጣናቱ የኮሚቴውን አባላት በገንዘብ በመደለል ህዝቡን ዝም እንዲያሰኙ እየተንቀሳቀሱ ነው። የኮሚቴው አባላት መደለያውን አንፈልግም ብለዋል። ህዝቡ ነቅቶ እንዲከታተል ተጠይቋል

6) መረጃ አርባምንጭ
ሃይማኖትን መነሻ ያደረገው የአርባምንጩ ተቃውሞ የህወሀትን አገዛዝ በማወገዝ እየተካሄደ ነው። የከተማዋ ባላስልጣናት ድጋፍ በሰጧቸው ግለሰቦች ተንኳሽነት የኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውውን የጽላት ስርቆት ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ አርባምንጭ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኗ ታውቋል። የፌደራልና ልዩ ሃይል ፈሷል። ህዝቡ የህወሀት አገዛዝ እንዲያበቃ በሚጠይቁ መፈክሮች አደባባይ ተቃውሞውን ቀጥሏል። የዞኑ ሀገርስብከት ጳጳስ ህዝቡ ለማረጋጋት እየሞከሩ ነው።

7) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የሚገኘው የታንታለም ማምረቻ መዘጋቱ ውዝግብ ፈጠረ

የኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የሚገኘውንና የፌዴራል መንግሥት ተቋም የሆነውን የቂንጢቻ ታንታለም ማዕድን ማምረቻ መዝጋቱ በክልሉና በፌዴራል መንግሥት መካከል ውዝግብ ፈጠረ፡፡

የማዕድን ማምረቻው እንዲዘጋ የተወሰነው በአካባቢውና በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው በሚል ምክንያት ቢሆንም፣ ዋና ምክንያቱ ግን የማዕድን ይዞታውን ለአካባቢው ወጣቶች ተሰጥቷቸው ራሳቸው አምርተው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታስቦ መሆኑን ከሁለቱም ወገኖች ሪፖርተር ያሰባሰባቸውመረጃዎች ያመለክታሉ።

የማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን ላለፋት 28 ዓመታት ማዕድኑን በማምረት ለውጭ ገበያ ሲቀርብ የነበረ ሲሆን፣ ማዕድኑን እዚሁ በማቀነባበርና እሴት በመጨመር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኝ የፌዴራል መንግሥት መወሰኑ ይታወቃል። በውሳኔው መሠረትም ኮርፖሬሽኑን የሚቆጣጠረው የመንግሥትልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የቂንጢቻ ታንታለም ማምረቻን በከፊል ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ አውጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም በክልሉና በኮርፖሬሽኑ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ይህ ጨረታ በወጣበት ወቅት ነው፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በየዓመቱ ሦስት ሚሊዮን ብር በጀት እንደሚመድብ ያቀረበው የአማራጭ ሐሳብም በዞኑ አስተዳደር ተቀባይነት አላገኘም። ይህንን አጣብቂኝ ሁኔታ ለመፍታትና የቂንጢቻ ታንታለም ማዕድን ማምረቻን ለውጭ አልሚዎች በከፊል ለማዘዋወር የወጣውጨረታና የተጀመረው ጥረት እንዳይስተጓጎል ለማድረግ የኮርፖሬሽኑ ተቆጣጣሪ የሆነው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር አቶ ግርማ አመንቴ የሚመራ ኮሚቴ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳን ለማነጋገር መወሰኑን ያገኘናቸው መረጃዎች አመልክተዋል።

Esat News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.