ወሎ መርሳ ከፍተኛ ህዝባዊ ትንቅንቅ አለ! (አስናቀው አበበ)


የፖሊስ ጣብያና ፍርድቤቱ ተቃጥሏል!
የህወሃት ባለስልጣንና ነገረ ሰሪዎች ቤቶች እየተቃጠሉ ሲሆን ለማቃጠል ያልተመቹ ቤቶች እየፈረሱ ነው!

መርሳ ከተማ ከወልድያ አቅራቢያ 30ኪ.ሜ. እርቃ የምትገኝ ከተማ ናት። ሰሞኑን የወልድያው ጭፍጨፋ ከተፈጠረ በኋላ አጋዚና ፌደራል ማታ ማታ እየዞሩ ሰውን ሲያስፈራሩ ሲሰነብቱ ህዝቡን ይበልጥ አስቆጡት። ፀብ አጫሪዎቹም እነሱው መሆናቸውን ኗሪዎች ገልፀዋል። ትናትና ብዙ ኦራል የወታደር መኪና መርሳ ዙሪያ ተሰማርተው ህዝቡን ማሸበር ያዙ። ይህን የተቃወሙ በጣም ብዙ ወጣቶች ላይ የተኩስ እሩምታ በመክፈት ጉዳት አድርሰዋል። የሞቱ ሰዎች አሉ እየተባለ ነው ብዙ ሰው እንደቆሰለ ግን ታውቋል።

ህዝቡም በሁኔታው ተቆጥቶ አደባባይ ግልብጥ ብሎ ወጥቷል። በአሁኑ ሰአት የወያኔ ባለስልጣናትና ነገረ ሰሪዎች ቤቶች በእሳት እየተቃጠሉ ናቸው። ወጣቱ እጅግ ገንፍሎ የወያኔ ባለስልጣናትን ቤት እየመረጡ እያፈራረሱ ይገኛሉ። ለማቃጠል ያልተመቹ ተቀራርበው የተሰሩ ቤቶችን ሲያፈራርሱ ነጠል ብለው የሚገኙትን ጋዝ አርከፍክፈው በእሳት እያነደዷቸው ነው። ፓሊስ ጣቢያ እና ፍርድ ቤቱንም አቃጥለውታል። በመላ መርሳ ህዝባዊ አመፁ ቢቀጣጠልም አቧሬ የምትባለው ሰፈር አካባቢ በተለይ ሁኔታው የጠነከረ ነው።

ወልድያ የተነሳው ህዝባዊ አመፅ ቆቦን አካሎ አሁን መርሳንም አዳርሷል። ወሎ ላይ የተነሳው ህዝባዊ አመፅ በአማራ ክልል እየተካሄዱ ካሉት በፍጥነት እየተዛመተ ያለ ነው። ወደ ሌሎች ቦታዎችም እንደሚስፋፋ ከሚወጡት መረጃዎች መረዳት ይቻላል። ወያኔ አማራንና ኦርቶዶክስን ለማጥቃት ሆን ብሎ ወልድያ በጥምቀት በአል ላይ ህዝቡን በጅምላ በመፍጀቱ ከቁጥጥር ውጭ ለሆነው አዲስ ጠንካራ ህዝባዊ አመፅ መነሻ ሆኗል። የወሎ ወገናችን በመላ አማራ ክልል ብሎም በመላ ኢትዮጵያ ያለው ህዝብ በየ አለበት ትግሉን በማፋፋም የወያኔን ግብአት እውን እናድርግ እያለ ጩኸት እያሰማ ነው።
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው መረጃውን ላጋሩን ጀግኖች ምስጋናችን ይድረሳቸው።
ህዝብ ያሸንፋል©!

 \

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.