ኮማንደር አማረ ጉዕሽ የወልዲያ ወጣቶችን ስም ማጉደፉ ቀጥሏል (ጌታቸው ሽፈራው)

ዜና ወልዲያ በአማራ ቴቪ

ዛሬ ጥር 21/2010 ዓም ከ3 ጀምሮ በወልዲያ ግርግር ነበር ሲል የአማራ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ችግሩ የተፈጠረው ጥር 12/2010 ዓም የተገደሉት ንፁሃንን ለማሰብ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ሊያደርጉ የነበሩትን የወልዲያ ነዋሪዎች ስነ ስርዓቱን እንዳያደርጉ ፖሊስ በመከልከሉ እንደሆነ ከዘገባው መረዳት ይቻላል።

በዚህም ምክንያት የወልዲያ መንገዶች በድንጋይና በኤሌክትሪክ እንጨቶች መዘጋታቸውን የአማራ ቴቪ ዘግቧል። የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴም ቆሟል ብሏል።

የ12 አመቱን ህፃን ጨምሮ ንፁሃን በግፍ በተገደሉ ቀን “የፀጥታ ኃይሉን እያሳደዱ በድንጋይ በመደብደባቸው ነው። ታግሰናቸው ነበር……” የሚል መግለጫ የሰጠው የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አማረ ጉዕሽ “ዜጎች ከጎናችን እንዲቆሙ” የሚል መልዕክት አስተላልፏል።

ኮማንደር አማረ ጉዕሽ “በችግሩ ሰበብ ስርቆት እየተስፋፋ ስለሆነ ህዝቡ ከጎናችን ሆኖ እንድንከላከል……” ሲል ሸቀጣሸቀጥ እያቀጠሉ ነው እያሉ የሚያወገወዟቸውን ወጣቶች ሌላ ስም ሰጥቷቸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.