የትግራይ የበላይነት በኢትዮጵያ ስለመኖሩ ማረጋገጫ (ገረሱ ቱፋ)

አራቱ የኢህአደግ ሊቃነመናብርት ከ17 ቀናት ዝግ ጉባኤ በኋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፖለትካ እስረኞችን ለመፍታት መስማማታቸዉ ይታወቃል።

በዚሁ መሠረት በፌደራል መንግስት ደረጃ 643፣ከኦሮሚያ ክልል 2345 ፣ ከአማራ ክልል 2905 እና ከደቡብ ክልል 413 እስረኞች ሲፈቱ ከትግራይ ክልል እስካሁን ምንም የተፈታ እስረኛ የለም።
ይህ ማለት የትግራይ ክልልን የሚወክለዉ ህወሃት ከራሱ ክልል እስረኛ ከሌለዉ ከሌሎቹ ክልሎች የሳራቸዉን ሰዎች ለመፍታት ነዉ መግለጫ የሰጠው ወይስ በጋራ የገቡትን ቃል አፍርሰዉ ነዉ በራሱ ክልል የሚገኙትን እስረኞች አልፈታ ያለዉ? ወይም የትግራይ ሰው በፖለቲካ አይታሰርም? በፖለቲካ የሚታሰሩት ሌሎች ብቻ ናቸው ማለት ነው። ይህ የሚያሳይው ልክ እንደ አፍርካን አሜርካን የሰብባዓዊ ደ ን ህነታችን(human security) እጅግ በጣም የተለያየ መሆኑን ነው። በአንድ ሀገር እየኖርን አንዱ ክልል በፖለቲካ ምክንያት የመታሰር ወይም የመሞት ዕድሉ ከሌላው በተለየ መልክ ዜሮ ከሆነ አንድ የሚሰጠን መልዕክት አለ።እነሱ ለምን አልታሰሩም አይደለም ጥያቄው የሌላው የደህንነት(human security) ደረጃው ከትግራይ ብሔር አባላት ለምን አነሰ ነው።

ነገሩ የፖሊቲካ እስረኛ አልመኖር ብቻ አይደለም። የፖሊቲካ እሰረኞችን መፈታት ተቃውሞው ስፅፉ የነበሩትም የህወሃት አባላት ነበሩ። እንድይፈቱ ያደረገውንም ለማወውቅ ከፈለጋቹ ማን የደንህነት መሰሪያቤቱን እንደሚመራ ማወቅ በቅ ነው። ከዚህ በታች ያላውን የለጠፈው ዮሃቅንስ አብረሃ(Jhon Abraha) የሚባል ቤልጄይም ብራስልስ የሚገኝ ድፕሎማት እና የህወሃት አባል ነው።

የፖሊቲካእስረኛ አልመኖር አንድ ነገር ነው። እንዲፈቱ የተወሰኑትን የፖሊቲካ እሰረኛ ማጏተት እና መቃወም ሌላ ነግር ነው። ይህ የሚያሳየው የሚገደሉት እና የሚታሰሩት ሰዎች ለህወሃት የፖሊቲካ እና የኢኮኖሚ ጥቅም መሆኑ ያረጋግጣል። መቸም በቀለ ገርባን ለልጁ ለቦንቱ ፤እስክንድርን ለልጁ ለናፍቆት ጥቅም ነው ያሰርነው እንደማይሉ እርግጠኛ ነኝ። እነዚህ ነገሮች ነበራዊ እወነታ ናቸው።ይህንን እወነታ የሚክድ ካለ ከዚህ አትራፍ የሆነ ግብዝ ብቻ ነው።

መሰረታዊውን እወነታ ሳይረፍድ ተቀብሎ ስር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት መጣር ለሁሉም ህዝቦች የተሻለ ወደፍት ጠቃሚ ነው።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.