አርበኞች ግንቦት ሰባት የተሰኘው ድርጅት በዐማራ ሕዝብ ቁስል ላይ ጨው ነሰነሰ! ውግዝ ከማርዮስ! ከግንቦት ሰባት ጋር ያበረ ዐማራ ጥቁር ውሻ ይውለድ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሰኞ ጥር ፳፰ቀን ፪ሺህ፲ዓ.ም. ቅጽ ፮ቁጥር ፭

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ግንቦት 7 የተሰኘው ድርጅት ከትግሬ-ወያኔ የከፋ የዐማራ ሕዝብ ጠላት  መሆኑን ከሚያራምደው ዓላማና ከሚፈጽማቸው ፀረ-ዐማራ ተግባሮች ተነስተን «ለጥቃታችን መከታ ያልሆነን ድርጅት፣ለመሞቻችን ምክንያት አይሁን» በሚል ርዕስ መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል። ይህን መግለጫ ያዩ የድርጅቱ አባላት፣ ደጋፊዎችና ጀሌዎች «እንዴት ሆኖ፣ ግንቦት 7 የዐማራ ጠላት ይሆናል? ድርጅቱ ካሉት አባላት ከመቶ ሰማኒያ ምናምኑ ያህል ዐማራዎች ናቸው» በማለት ቡራ ከረዩ ማለታቸውን እናስታውሳለን። «ዕውነትና ንጋት እያደር ይፈካል» እንዲሉ፣ እኛ ያልነው ዕውነት፣ ደጋፊዎቹ የጮThበት ውሸት መሆኑን ሰሞኑን ድርጅቱ፣ «ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» ጋር በመሆን፣«ከአርበኞች ግንቦት ሰባትና ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ» በሚል ርዕስ ባወጣው ሀተታ ፀረ-ዐማራነቱን ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል። ከዚህ ፀረ-ዐማራና የትግሬ-ወያኔ ዓላማ አራማጅ ከሆነ ድርጅት ጋር የቆመ የዐማራ ልጅ፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የክሕነት ሥልጣን ባይኖረውም ፣እንደባህላችን፣ ወግድ ይሁዳ! ውግዝ ከማርዮስ፣ ጥቁር ውሻ ውለድ እንድንል፣ በዕውቀታችሁ፣ በጊዜአችሁና በገንዘባችሁ  ያሳደጋችሁት  ድርጅት  በዐማራው  ቁስል  ላይ  የነሰነሰው  ጨው  አስገድዶናል።

«ቀጣፊን ሲረቱ፣ በወንድሙ በእህቱ» እንዲሉ፣ የግንቦት 7 ቃል አቀባይ የሆኑት የኢሣት ሠራቶች ጭምር መግለጫው ተገቢና ትክክል አለመሆኑን በየገጸመጽሐፋቸው ገልጸዋል።የድርጅቱን የሕዝብ ግንኙነት ተግባርም አውግዘዋል።

የትግራይ ሕዝብ  ዴሞክራሲያዊ  ንቅናቄ  (ትሕዴን)  አመሠራረትና  ተልዕኮ  በሚገባ  የተከታተሉ ወገኖች የሚያምኑትና የሚገባቸው፣ ትሕዴን፣ ወያኔ በሕዝብ ግፊት ከሥልጣን ቢወገድ፣ አሁን ግንቦት 7 እንደሚለን በሰው ደም ፣ከሁሉም በላይ በዐማራ ደም የተጨማለቁ የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች የሆኑ ምንም ዓይነት ተጠየቅ እንዳይደርስባቸው ዘብ እንዲሆን፣ ከቻለም የሥልጣን ባለቤት እንዲሆን፣ በሻዕቢያና በትግሬ-ወያኔ ትብብር የተመሠረተ ድርጅት መሆኑን ያውቃሉ። ይህን ለመረዳት ከማንም የተሻለ የግንቦት 7 አመራር ከነመለስ ጋር በነበረው ጥብቅ ግንኙነትና አሁንም ከሻዕቢያ ጋር ባለው ግንኙነት ከማንም የተሻለው ዕውቀቱም ሆነ ግንዛቤው ሊኖረው እንደሚችል ይታመናል። ሞላ አስገዶም የትሕዴን መሪ፣ ብርሃኑ ምክትል አድርጎ፣ የመድው ሰው ፣የሁለቱ ድርጅቶች የስምምነት ሰነድ የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ፣ ከነሠራዊቱ ከድቶ አዲስ አበባ መግባትና፣ በግንቦት 7 አባላትና አካላት ላይ ያሳደረው የኅሊና ስብራት የቱን ያህል እንደሆነ የሚያውቁ ያውቁታል። ግንቦት 7 እና አመራሩ ይህን መራራ ሐቅ ወደ ጎን ገፍውና አራሙቻ ጭነው፣ዛሬም አንድ ነን በማለት በዐማራው ቁስል ላይ ጨው መነስነሱን ሥራዬ ብለው ይዘውታል። ሁለቱን ድርጅቶች እንዲህ አንድም ሁለትም ያደረጋቸው መሠረታዊ ምክንያቱ ፀረ- ዐማራ አቋማቸውና አመለካከታቸው እንደሆነ ተግባራቸው በግልጽ ያሳያል።

ማንም የትግሬ-ወያኔን እንቅስቃሴ የሚከታተል ሰው እንደሚረዳው፤ ወያኔ ተቃዋሚዎቸ ናቸው ያላቸውን ድርጅቶች፣ ግንቦት 7ን ጨምሮ፣ «አሸባሪዎች» በማለት ፈርጆ ከነርሱ ጋር ንክኪነት ያላቸውንም ሆነ «የዓይናቸው ቀለም አላማረኝም» የሚላቸውን በአሸባሪነት ስም እያሳበበ መግደሉ፣ ማሰሩና ማሰቃየቱ ይታወቃል። ትሕዴን ግን ከዚህ ፍረጃ ውስጥ የለም። ለምን? መልሱ በነርሱ የተቋቋመና የነርሱን ዓላማ የሚያስፈጽም መሆኑ ነው። ለዚህ የሞላ አስገዶም መክዳትና ወደ አለቆቹ መቀላቀል ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 የሚባለው ድርጅት፣ በትሕዴን ተማምኖ ያሰማው የነበረው ፉከራና ቀረርቶ፣«እሳት እንደገባ ጅማት ወደ ኋላ ተኮማትሮ» ወደ በረዶነት መለወጥ የጀመረው፣ ከሞላ አስገዶም ክዳት ተከትሎ እንደሆነ ግልጽ ነው።

እንቅስቃሴው ወደ በረዶነት የተለወጠው ደግሞ፣ አዘዞ ላይ ፊሽካው ተነፋ በተባለ፣ አጭር ጊዜ ውስጥ፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በተኮሳት አብሪ ጥይት አማካኝነት የጎንደርና የጎጃም ሕዝብ ነቅሎ በመውጣት የሕዝባዊ እንቢተኝነቱን እንቅስቃሴ በመቀላቀል፣ ለግንቦት 7 «ካላችሁ ሠራዊት ላኩልን፣ ከሌላችሁ መሣሪያ አቀብሉን» የሚለው ጥያቄ ከየአቅጣጫው ሲሰማ፣ሠራዊት ቀርቶ አንድ ጥይት ማቀበል ሳይችል በቀረበት ወቅት እንደሆነ ልብ ያለው ልብ ይለዋል።

በግንቦት 7 ስም የሞቱት፣ የታሠሩት፣ የተሰቃዩት በሙሉ ዐማሮች ናቸው። ኤርትራ በርሃ ሂደው በሻዕቢያና ቀጥሎም በዘመቻ ስም የተገደሉት ዐማራዎች ናቸው። እነ ሻለቃ መሣፍንት(ገብርዬ» እነ ተስፋሁን፣ወዘተ ዐማራዎች ናቸው፣። ካማራም ጎንደሬዎች ናቸው። በመፈንቅለ መንግሥት ስም የታሰሩትና የተገረፉት በሙሉ ዐማራዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ የዕድሜ ልክ እስረኛዋ  እማዋይሽ  ተጠቃሽ ናት። ይህ ሁሉ ሲሆን የግንቦት 7 ማኅበራዊ መሠረት ከሆኑት ነገዶች የሞተም ሆነ የታሠረ አለመኖሩን ስናስተውል፣ ግንቦት 7 ከወያኔ በምን ይለያል? ብለን ብንጠይቅ ነውሩም ሆነ ክፋቱ ምንድ ነው?

ሕዝባችን ይህን ሁሉ ሐቅ እየተመለከተ፣ግማሹ በየዋህነት፣ ግማሹ መረጃ ባለማገላበጥ፣ ግማሹ ወያኔ ይውደቅ ብቻ በማለት፣ ለግንቦት 7 ድጋፉን መስጠቱ ይታወሳል። ዐማራው ጠላቴ ነው ብሎ ሥንቅ ሰንቆ፣ ነገዱን አደራጅቶና መርቶ ለሥልጣን የበቃው የትግሬ-ወያኔም ዐማራውን ለማጥፋት ቆርጦ መነሳቱ እየታወቀ፣ እርሱንም ለማጥፋት ጥቃቅን ምክንያቶችን ለሚፈልገው ወያኔ፤ «ሲሻኝ ጢስ ወጋኝ» ሆኖለት፣ የሌለውን አለኝ እያለ ጧት ማታ በሚያሰራጨው ፕሮፓጋንዳ ለዐማራው መጨፍጨፍ ምክንያት ከመሆን አልፎ፣ እሱ ራሱም በቁስሉ ላይ ጨው እየነሰነሰ ይገኛል። ግፍ የበዛበት ዐማራ በራሱ አነሳሽነት በገዳዮቹና በአፋኞቹ ላይ ካለፉት 3 ዓመታት ወዲህ፣ በጎንደር፤ በጎጃምና ሰሞኑን ደግሞ በወሎ ተቀጣጥሎ የዘለቀውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ፀረ-ትግሬ ነው በማለት፣ ከትሕዴን ጋር አብሮ ትግሉን ጥላሸት ሊቀባው ሞክሯል። የዐማራውንም የኅልውና ትግል ፀረ-ትግሬ እንደሆነ ከወያኔ በላይ ሆኖ፣ የአዞ እንባውና ማንባት ጀምሯል። ይህ የወሎ ሕዝብ በ27 ዓመታት ውስጥ በትግሬ ወያኔ የተፈጸመበት ግፍ አንገሽግሾት የተቀጣጠለው አመጽ፣ በፀረ-ትግሬነት መፈረጅ የድርጅቱን ፀረ-ዐማራነት ያረጋግጣል።

በሌላ በኩል፣ ግንቦት 7 የወሎ ሕዝብ በ27 ዓመታት በትግሬ ወያኔ የተፈጸመበት የግፍ ቁና ሞልቶ መፍሰስ በመጀመሩ፣

«መምረር ነው፣ መምረር ነው,፣ መምረርነው እንደቅል፣ ባይመር አይደለም ወይ ዱባ የሚቀቀል።»

በሚለው የአባቶቹ ይትባህል በቁጣና በእልክ ተነሳስቶ የወሰዳቸውን እርማጃዎች የግንቦት 7 የሰሜን ዕዝ ጥቃት አደረሰ በማለት በፕሮፓጋንዳ አውታሩ ኢሣት ሲነግረን መክረሙ ይታወሳል። ይህ ከሆነ ወያኔን ከትግሬ ሳይለይ ጉዳት ያደረሰው ራሱ ግንቦት 7 እንደሆን ያሳያል። ነገሩ ግን ወዲህ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ግንቦት 7 እንኳን መሀል ወሎ የሚደርስ ዕዝ ቀርቶ፣አንድ አባል የለውም። የግንቦት 7 ን የሰሜን ዕዝ ወሬ ለሰማ ሰው ብልኅ ሴት አለችው የሚባለውን ነገር ያስታውሳል። «ከብት ያለው ያግባሽ፣ ወይስ አፍ ያለው? ቢሏት፣ አፍ ያለው ያግባኝ፤ አፍ ካለው፣ ከብቱን ያመጣዋል» ያለችው ዓይነት ሆኖ፣ የዐማራው ጀግና የሠራውን ሥራ በኢሣት አፉ አማካኝነት ሁሉም የኔ ነው ይላል። በኢሣት በተሰራጩት ዜናዎች ትክክለኛነት ካመነ፣ ትግሬን ከወያኔ ሳይለይ ጉዳት ያደረሰ እሱ ነውና ተጠያቂው ራሱ ግንቦት 7 ነው። ልብ አድርጉ «ጀግነቱን» የኔ ነው ብሎ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የማጣላቱን ግን የዐማራው ሕዝብ ነው ይላል። «ባንድ ራስ ሁለት ምላስ» የሚባለው ይህ ዓይነቱ ድርጊት ነው።

በጥቅሉ ግንቦት 7 የሕዝቡን ትግል ውጤቶች የእኔ ናቸው እያለ፣ ወደ ውጤቶቹ በተደረገ ጉዞ፣ ሕዝቡ ጠላቱን ከወዳጁ ለይቶ የወሰደውን ተገቢ እርማጃ፣ ራሱም በመግለጫው፣ ወያኔ «የትግራይን ተወላጆች በማስገደድና በማባበል አባል ካደረገ በኋላ፣ በሕዝብ ላይ ለሚፈጽማቸው ጥቃቶች መረጃ  አቀባይ፣  ጉዳይ  አስፈፃሚና  ያካባቢው  የሥርዓቱ  የድጋፍ  ኃይል  አድርጎ ተጠቅሞበታል። በዚህም የተነሳ ለዓመታት ተፋቅሮና ተከባብሮ ከሚኖረው ህዝብ ጋር እንዲጋጭና በጠላትነት እንዲታይ አድርጎታል» ይለናል። አያይዞም « ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተነሱ የጸረ ወያኔ እንቅስቃሴዎች የበቀል እርምጃ እየተወሰደባቸው ካሉ የህወሃት ካድሬዎች በተጨማሪ ከህወሃት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ያልነበራቸው ሰዎችም የጥቃቱ ሰላባ እንደሆኑ መስማት እየተለመደ መጥቷል።»

 

በማለት በገለጻቸው የወያኔ ተላላኪዎችና አፋኞች ላይ የወሰደውን እርምጃ፣ ከወያኔ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች ተጠቅተዋል በማለት ራሱን በራሱ እዚያው በዚያው ሲቃረን ይታያል። ግንቦት 7 ከወያኔ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች ጥቃት ተፈጸመባቸው ሲል፣ እነዚህ ሰዎች እነማን እንደሆኑ፣ የተጸመባቸው ጥቃት ምን ዓይነት መሆኑን በመግለጫው ይኸነው ያለን ነገር የለም። ይህ በሌለበት ሁኔታ በምን ተዓመር ነው፣ የትግሬ-ወያኔ ተባባሪዎችና ደጋፊዎች ያልሆኑ ሰዎች ጥቃት ሊደርስባቸው እንደቻለ በምን ሁኔታ እንዳጣራ የሚያሳይበት ማስረጃ የለም።

ከሁሉም በላይ ስብሓት ነጋ፣ ሥዩም መሥፍን፣ ሣሞራ የኑስ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ዐባይ ወልዱ፣ ወዘተ ወዘተ ሁሉም ወያኔዎችና ትግሬዎች ናቸው። እነርሱ ሲነኩ ትግሬ መነካቱ ግልጽ ነው። ትግሬ ናቸውና። ከሁሉም በላይ በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ የትግሬ ወያኔ አባል ያልሆነ ትግሬ፣ በግልጽ በሚያሰሙት ተቃውሞ ከምናውቃቸው ጌታቸው ረዳና ገብረመድኅን ውጭ አለወይ? በየቤታቸው አድፍጠው ድምፅ የማያሰሙ የወያኔ ተቃዋሚዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ግን ወያኔን ተቃወሙ ማለት አይደለም። ለምሳሌ አረና እንደ ድርጅት የወያኔ ተቃዋሚ መስሎ የሚታይ ነው። አረና ግን ከወያኔ ጋር የአካሄድ እንጂ፣ የዓላማ ተቃውሞ የለውም። ለምሳሌ እንደወያኔ ሁሉ ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠላምት የትግራይ እንደሆነ ያምናል። ወያኔ በዐማራ ላይ የፈጸመውን የዘር ማጥፋትና የዘር ምጽዳት ወንጀል አያምንም። የወልቃይትን ጠገዴ ሕዝብም ትግሬ ነው ብለው ያምናሉ። ሁሉም የቆሙት ለትግሬ ነው። ወያኔ በተጠቃ ቁጥር ሁሉም ትግሬ ተጠቃ በማለት ይጮኻሉ። ትግሬና ወያኔን እንዴት መለየት እንዳለበት የሚያውቀው ማንም ሳይሆን የትግራይ ሕዝብ ነው። እነርሱ ማለትም ትግሬዎቹ «ትግሬና ወያኔ አይለያዩም፣ አንድ ነን»፣ እያሉን፣ ግንቦት 7፣ ከወያኔ አባሎች (ትሕዴን) ጋር ሆኖ ከወያኔ ምልምሎችና ትግሬዎች ጋር ሆኖ፣ ከወያኔ ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ የሌላቸው ትግሬዎች ተጠቁ ብሎ ሲቆጭ፣ የወሎ ሕዝብ በድፍን ከሁሉም በላይ፣የዐማራ ሕፃናት ፣ አዛውንቶችና እናቶች በኤሊኮፕተር በታገዘ የአጋዚ ሠራዊት ሲጨፈጨፉ አላሳዘኑትም። ጎንደር፣ ጎጃም፣ ቤንሻንጉል፣ ከፋ፣ ሐገርጌ ወለጋ ከነነፍሳቸው ገደል  የተወረወሩ  ዐማሮች፣  ወያኔ  በጠላትነት  ፈርጆ እንዲጠፉ የፈረደባቸው ስለሆኑ አያሳዝኑም። ይህም ለግንቦት 7 አይገደውም።

ከላይ ከተጠቀሱት ሰዎች በቀር የትግሬ-ወያኔ ደጋፊ ያልሆነ ትግሬ፣ወይም የወያኔ ዓላማ አራማጅ ያልሆነ ትግሬ ፈልጎ ማግኘት ይቻላል የሚሉን ካሉ፣ «ተጨፈኑ ላሞኛችሁ» የሚሉን ብቻ ናቸው። ከተባለም መባል ያለበት፣ ሕዝብን እንደሕዝብ በጠላትነት መፈረጅ ተገቢ አይደለም የሚለው ነው። እናም ዐማራው የትግሬን ሕዝብ በጠላትነት አያይም። በተቃራኒው የትግራይ ሕዝብ ልጆቸ ናቸው ብሎ በአሸናፊት ስሜት ተውጦ ፣ ለወያኔ ዓይንና ጆሮ ሆነው፣ለጨበጡት ሥልጣን ያበቃቸው እንደሆነ በእያደባባዩ በኩራት የሚነግሩን ትግሬዎች ናቸው። ዐማራ ሲገደልና ሲፈናቀል ይህ ጥሩ አይደለም ብሎ ድምፁን ያሰማ ትግሬ ከሁለት  ሰው  በቀር  አልተሰማም።  በዓለም  ዙሪያ  የሚገኘው  ኢትዮጵያዊ በወገኖቹ ላይ የትግሬ ወያኔ የሚፈጽመውን ግፍ ለመቃወም ባለፉት 27 ዓመታት በየዓለምአቀፍ ድርጅቶች በር በበረዶ በፀሐዩ ሲንቃቃ አንድም ትግሬ አደባባይ አለመውጣት ትርጉም ምን ሊባል ይችላል? በእኛ እምነት ሁሉም የትግሬ ወያኔ የሚሠራው ሁሉ ትክክል ነው ብሎ በማመኑ እንደሆነ ጥርጥር የለንም።

በጎንደር፣ በጎጃምና በወሎ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ጥቃት የተፈጸመባቸው ግለሰቦች ትግሬዎች ብቻ    ካለመሆናቸውም በላይ፣ ሁሉም የወያኔ ሰላዮችና የአፈና መዋቅሩ ሠራተኞች ለመሆናቸው አንዳች ጥርጥር የለም። በዚህም ጥቃት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል በርካታዎቹ ዐማራዎች ናቸው። ይህን የዐማራው ክክል ተብየ ዝርዝሩን ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ተጠቂዎቹ ዐማራዎች ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸውን አሳውቋል። ወሎም የሆነው ይኸው ነው። የሚገርመው ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣  ደብረዘይት፣  አምቦ፤  ወዘተ  ዐማራውና  ኦሮሞው  በግፍ  ሲጨፈጨፉ  አንዳችም  መግለጫ  እንዳላወጣ ይታወሳል። የወሎውም ከዚያ የተለየ ነገር አልተፈጠረም። ጎንደርና ጎጃም በወያኔ ሰላዮችና አፋኞች ላይ ሕዝቡ ዘር ሳይለይ፣ እርማጃ ወስዷል። በዚህም ትግሬዎች እንዴት ተደፈርን ብለው አገር ይያዝልን ማለታቸውና ከውጭ እስከ ውስጥ ያለው የወያኔ አባል ሕዝቡ በወሰደው ነጥሎ የማጥቃት እርምጃ ቆፈን ውስጥ በመግባት «የአባዬን ወደ እማዬ ልክክ» ይሉት ዓይነት፣ የዘር ጥቃት ደረሰብን በማለት ሲያለቅሱ በመስማታችን እጅግ ተደንቀናል።

 

የእኛ ወገኖች በግፍና በገፍ ከነሕይዎታቸው ገደል ሲጣሉ ትግሬዎች ፈንድሻ እየነሰነሱ ዳንኪራ ይመቱ ነበር። መከራና ሐዘን፣ መጠቃትና መደፈር ምን እንደሆን ይወቁት።

ከእንግዲህ ለሚያደርጉት ሁሉ ምን ሊከተላቸው እንደሚችል በትንሿም ቢሆን ትምህርት አገኝተዋል። ይህ ትምህርት ግንቦት 7ን አንገሽግሾት ዐማራውን ሲያማርር፣ የፊቱን ያስተዋለ አይመስልም። በዚህ ድርጊቱ ቀለብ አቅራቢው የዐማራ ልጅ ለካ ብሎ የእንግሊላ ጥሎት ሲሸሸው፣ ያን ጊዜ ስሕተቱን እየመረረው ይረዳል። ይህ ጥቃትና መደፈር ተሰምቶት ከግንቦት 7 ጋር የቆመ ዐማራ ለአባቱ ገዳይ እናቱን የሚድር ወኔ ቢስ ነው> እንደዚህ ያለ ዐማራ ይኖራልንም ብለን አናስብ።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን! ዐማራነት ያብባል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.