ሕወሓቶች ማን አለብኝ ባይነታቸውን በአደባባይ መናገሩን ቆጥበው ወቅቱ ይመጥነዋል ያሉትን ፕሮፖጋንዳ ጀምረዋል (በጌታቸው ሽፈራው)

አቶ ጌታቸው ረዳ “ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት አልተፈፀመም አለ” ተብሏል! ይህ እውነት ነው፣ ሊባል የሚገባውም እንዲህ ነበር። ግን አቶ ጌታቸው ለምን ይህን ከትህነግ/ህወሓት የማይጠበቅ መግለጫ ሰጠ?

 

~ ትህነግ ወደ መቀሌ እየተመላለሰች ባደረገችው ስብሰባ አንድ ጉዳይ ላይ ስምምነት ተፈጥሯል። እስካሁን ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ፣ …… እያሉ በለበጣ ሲጠቀሙ ቆይተዋል፣ በቅርቡ እነ ለማ ተመሳሳይ ጉዳይ አንስተው በተቃዋሚው ጎራ ሳይቀር “አበጃችሁ” ተብለዋል። ስለዚህ ትህነግ፣እነ ለማ ለምን ተቀባይነት አገኙ፣እኛስ ለምን አላገኘንም ብላ ተወያይታለች፣ በዚህም መሰረት ቅቡልነት የሚያስገኙ ጉዳዮችን በትኩስነታቸው መጠቀም፣ ሕዝብ ከትህነግ የማይጠብቃቸውን አንዳንድ ሀሳቦች ማንፀባረቅ ላይ የተስማማች ይመስለኛል። አጀንዳ ተዘረፍን ብላ እሪሪሪ ያለች ይመስለኛል።

~በቅርቡ ተከስቶ በነበረው ጉዳይ ለይስሙላ የአማራ ክልል አስተዳዳሪ ነው የተባለው ብአዴን “የዘር ጥቃት ደርሷል” ብሎ መግለጫ ሰጥቷል፣ ግንቦት 7 ደግሞታል! ትህነግ ከእነዚህ ድርጅቶች የተሻለች ለመምሰል ትኩስ አጀንዳ አገኘች! የ”ዘር ጥቃት አይደለም” ብላ ከብአዴንና ከግንቦት 7 የተሻለ ተረጋግታ እያሰበች እንደሆነ ለመግለፅ ፈለገች

~ ነገም ከእነ ለማ የተሻለች የምትመስልበትን ቅብ እርምጃ ትወስዳለች፣ ባትወሰድ እንኳ በመግለጫ ታስነግራለች

~ በተግባር ግን እነ ጌታቸው አሰፋ የሚመሩት ቡድን የወልዲያ ወጣቶችን ዘር እየጠራ እየደበደበ ይሆናል! ጌታቸው አሰፋ እያስደበደበ፣ ጌታቸው ረዳ ተቃዋሚ ከሚለውም ለዘብ ብሎ ከትህነግ የማይጠበቅ መግለጫ ይሰጠል፣ ይህ አዲሱ ስልት ነው!

~ ጥላቻቸውን በመግለጫ፣ አፋኝነታቸውን በሚዲያ፣ ማን አለብኝ ባይነታቸውን በአደባባይ መናገሩን ቆጥበው ወቅቱ ይመጥነዋል ያሉትን ፕሮፖጋንዳ ጀምረዋል። ስልጣንን ለማስጠበቅ ሲባል ጥርሳቸውን ነክሰው ቀዝቀዝ፣ ለስለስ ለማለት ወስነዋል! “ሕዝብ ተላላ ነው” ብለው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.