ወያኔ የትግራይ ህዝብ ተወካይ አይደለም፣ (ባይሳ ዋቅወያ)

ባይሳ  ዋቅወያ

ክፍል ሁለት (ካለፈው የቀጠለ)

(ለውይይት መነሻ) 

ባለፈው ጽሁፌ ባጭሩ ለማስቀመጥ የሞከርኩት የወያኔ መንግሥት በታሪካችን ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በወገኖቻችን ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ ከልክ ያለፈና መደረግ ያልነበረበት ወንጀል መሆኑን እያወቅን፣ ደጋግሞ ስለተነገረን፣ ደጋግመን ስላየነውና ስለሰማነው ብቻ፣ መሆን የነበረበት ነው ብለን መቀበላችን የህሊናችንን መደንዘዝ ያመለክታል ብዬ ነበር። በመሆኑም ከዚህ የህሊና መደነዝ ተላቅቀን ባንድነት በመቆም ህገ መንግሥታዊ መብታችንን ለማስከበር ድምጻችንን እናሰማ ብዬ ነበር የደመደምኩት። በጽሁፉ ውስጥ የወያኔ ገራፊዎች አሰቃዮችና ገዳዮች እንዴት ቢሰለጥኑ ነው እንደዚህ በወገኖቻቸው ላይ ሊጨክኑ የቻሉት የሚል ጥያቄ አንስቼ ነበር። መልስ ጠብቄ ሳይሆን የጭካኔው ደረጃና የግፉ ብዛት ቀሪው የኢትዮጵያ  ህዝብ ወያኔን እንደውጭ ወራሪና ርህራሄ ቢስ አካል አድርጎ ከመቁጠር አልፎ፣ ሀ) ጠቅላላውን የትግራይን ህዝብ እንደ ወያኔ ጨካኝና ርህራሄ ቢስ አድርጎ በመቁጠሩና፣ ለ) ወያኔንም የትግራይ ህዝብ ተወካይ አድርጎ በመፈረጁ፣ አዝማሚያው ወዳልተፈለገ የርስ በርስ ግጭት ማምራት ብቻ ሳይሆን ጥላቻን ባንድ ህዝብ ላይ ያነጣጥራል የሚል ሃሳብ ስላሳደረብኝ፣ ይህንን የተሳሳተ ግምት በጊዜው ለማስተካከልና ወያኔም የትግራይን ህዝብ የማይወክልና የትግራይ ሰፊ ህዝብም ከወያኔ አንዳችም ዓይነት ልዩ ጥቅም ያላገኘ፣ ሰብዓዊ መብቱም ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩል የተረገጠና እነደ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በግለሰብ ደረጃ ጥሩም መጥፎም ሰዎች ያሉበት ማህበረሰብ  መሆኑን  በተቻለኝ  መጠን  ለማስረዳት  ነው።  መሰረታዊው  እምነቴ፣  በማንኛውም ህብረተሰብ ውስጥ የግለሰብ እንጂ የህዝብ ጥሩ ወይም መጥፎ የለም የሚለው ነው።

ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍና በደል፣ እንኳን እኛ የዓለም አቀፉም ማህበረሰብ ያወቀው ጉዳይ በመሆኑ፣ በደሎቹን ፈጽሟል አልፈጸመም ብሎ መሞገት ጊዜ ማጥፋት ይመስለኛል። ወያኔም ራሱ አልገደልኩም ሳይሆን “የጸጥታ አስከባሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን እንዲገድሉ ትዕዛዝ የሰጠሁት ህግና ሥርዓትን ለማስከበር ነው፣ የተወሰደውም እርምጃ ህዝቡ ያሳይ ከነበረው የማስፈራራት ድርጊት ጋር ተመጣጣኝ ነበር” ነው የሚለው።

እንደማንኛውም የአናሳ ብሄር ወይም ቡድን ገዢ መደብ፣ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሥልጣኑን ለማንሰራፋት ያለው አንድ ብቸኛ አማራጭ በጉልበት መግዛት ነው። ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር የበላይ ሆኖ እንዲገዛ ስለማይፈቅድለት እንደምንም ብሎ የውሸትም ቢሆን “ካሮትና በትር” እያሳየ በበላይነት መግዛት ነበረበት። እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ቢሆንማ ኖሮ ባገሪቷ ውስጥ ሊኖረው የሚገባ የሥልጣንም ሆነ የምጣኔ ሃብታዊ ድርሻ፣ የቆዳ ስፋትና የህዝብ ብዛትን መሰረት ባደረገው ያገሪቷ ፌዴራሊዝም ህገ መንግሥት መሰረት፣ ወያኔ ሊያስተዳድር የሚችለው ድርሻው ከአስር በመቶ አይበልጥም ነበር። በተግባር የሆነውና የኢትዮጵያን ህዝብ እያናደደ ያለው ዓይን ያወጣ አሰራር ግን፣ በፖሊቲካም ሆነ በምጣኔ ሃብት ይዘትና አስተዳደር ሙሉ በሙሉ የበላይ ተቆጣጣሪና ባለቤት ሆኖ የሚገኘው ወያኔና ባብዛኛው ከትግራይ ብሄር የተውጣጡ በወያኔ ዙርያ የተኮለኮሉና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ በላይ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦች መሆናቸው ነው።

የመከላከያ ሰራዊቱ የበላይ ሹማምንት፣ በሲቪል የጸጥታና የሚሊታሪ ኢንተሊጀንስ፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በጉምሩክ እንዲሁም በሌላ ገቢን በሚያስገኙ ወይም የፖሊቲካ ሥልጣንን በሚያጎናጽፉ መስኮች የአስተዳደሩን ቦታ የሚይዙት ትግርኛ ተናጋሪዎች መሆናቸው በገሃድ የሚታይ ዕውኔታ ነው። በየክልሉ የኤኮኖሚውን እንቅስቃሴ በበላይነት የሚመሩትና ባብዛኛው የሚያንቀሳቅሱት የትግራይ ብሄር ተወላጆች ናቸው። በጉሙዝና በኒሻንጉል ወይም በጋምቤላ ክልሎች ውስጥ ያሉትን ረጃጅም ህንጻዎች፣ የዕጣንና ሸምበቆ ማምረቻዎች፣ የወርቅና የዕብነ በረድ ማምረቻዎችን በሙሉ በባለቤትነት የያዙት የትግራይ ተወላጆች እንጂ የክልሉ ህዝቦች አይደሉም፥ በነቀምቴ ወይም አጋሮ፣ በሃዋሳ ወይም በጂማ የሚገኙትን ነፍስ ያላቸውን የንግድ እንቅስቃሴዎች በባለቤትነት የያዙት ከትግራይ ብሄር የተወለዱና ይባስ ብሎም ባካባቢው ይኖሩ ያልነበሩ አዲስ መጪዎች ናቸው። እንደሚታመነው ከሆነ እነዚህ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ይህን ሁሉ ሀብት እንዲያፈሩ የተደረገው ሥርዓቱ ሆን ብሎ እነሱን ለመጥቀም ያሰናዳም ባይሆን፣ በአሰራር ላይ በየመሥርያ ቤቱ ያሉት ትግርኛ ተናጋሪ ባለሥልጣናት “ባገር ልጅነት መንፈስ” ለሌላኛው ትግርኛ ተናጋሪ የሃብት ማግኛና ማካበቻውን መንገድ ስለሚያበጃጁላቸው መሆኑን ህዝቡ ያወቀው ጉዳይ ነው።

ሌላው ሆን ተብሎ   በግልጽ የሚደረገው “አድልዖአዊ” አሰራር ደግሞ የወያኔ መንግሥት ሆን ብሎ በየመሥርያ ቤቱ “በስውር” በከፍተኛው ሹመት ወንበር ላይ ሳይሆን “በምክትልነት” ወይም “በአማካሪነት” ከሥር የሚሸጉጣቸው በተግባር ግን፣ የመሥርያ ቤቱን ሥራ በተመለከተ ብቸኛና ወሳኝ የሆኑትን የትግራይ ግለሰቦችን መመደቡን ነው። አንድ በግሌ ያየሁት፣ ዘወትር የሚገርመኝና ከላይ ያሰፈርኩትን ግምቴን በመረጃ ለማስረዳት የሚያመቸኝ ገጠመኝን ባካፍላችሁ ዕውኔታውን ትረዳላችሁ ብዬ እገምታለሁ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.