ህወሃት ያወሳሰበች ፕላን እየሰራላት አይደለም! – ልዑል ዓለሜ

 

ጫጫታዉን ማጦዝ ችለንበታል ብለዉ ነበር ኦህዴድ ገሰገሰ ህወሃት ተገረሰሰ አይነት ጨወታ…. ተያይዞ እስረኞች ተፈቱ ሊፈቱ ነዉ የሚል ብዥታ…. ሁሉም እየተሳካላቸዉ አይደለም ህዝቡ እንደማያምናቸዉ በሚገባ እየተረዱት መጥተዋል ዛሬ እነ እስክንድር ነጋ እና እነ አንዷለም ጥፋተኛ ነን ብለን አንፈርምም በማለታቸዉ እየተወያዩ ነዉ:: ባይፈርምሙም ይፈቱ የሚለዉን ሚዛን ሳይወዱት እየተስማሙበት ቢሆንም ብሄራዊ መረጃዉ ደስተኛ አልሆነም…… የህወሃት ማድቤት እየ ነደደች ነዉ።
እስረኛ ፈታን.. ኦህዴንን ፈታን.. በአዴንን በመጠኑ ለቀነዋል.. ፓርላማዉን ፈታነዉ…. እያሉ መሐበራዊ ሚዲያዉን አጨናንቀዉ ህዝባዊ ትግሉን የማክሸፍ ፕላን ቢ ያቸዉን ህዝብ ነቅቶባቸዋል::
ለማ መገርሳ እያደረገ የሚኘገዉ ጥረት መልካም ነዉ….! ነገር ግን ህወሃትን እያዳኑ የህወሃትን እድሜ ማሳጠር አይቻልም የሚል የህዝብ ድምጽ አስገምግሟል።

በዶላር እጥረት እብደት ላይ የሚገኘዉ ህወሃት አዳዲስ ዜማዎችን በመልቀቅ ይታወቅል ዘንድሮ ግን አጃቢዎቹ የሉም ባዶዉን ለልመና በማይመች ሁኔታ ቁልቁለት ላይ ነዉ።

እስረኞችን እንፍታ አለምን እናታልል ሊበላን ያለዉን ህዝብ እናዘናጋዉ የረጅም ግዜ እቅድ አሁን ዘጭ ብላለች ህዝቡ ኢትዮጵያ ትፈታ በማለት የነጻነት ጥያቄ ዉስጥ ከትሟል።
ደህና ሰንብቱ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.