ሐረር በሚገኘው ሐማሬሳ የስደተኞች ካምፕ የህወሃት ቅልብ ጦር አጋዚ

ሐረር በሚገኘው ሐማሬሳ የስደተኞች ካምፕ የህወሃት ቅልብ ጦር አጋዚ በከፈተው ተኩስ  10 ሰዎች መሞታቸው ታወቀ።በዚሁ የአጋዚ ጥቃት ከ20 የሚበልጡ ሰዎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን፤ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል የሚል ስጋት አለ።ከሞቱት 8 ሰዎች መካከል ሶስቱ የኦሮምያ ፖሊስን መለዮ የለበሱ ፖሊሶች መሆናቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመገናኛ ብዙሗን ከላኩት መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

በዚሁ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው የመጡ ሰዎች በተጠለሉበት ካምፕ ዉስጥ እድሜያቸው ለዓቅመ አዳም ያልደረሱ ሕጻናት፣ሴቶች፣ቤተሰባቸውንና እራሳቸውን መከላከል የማይችሉ አባወራዎች፣የእድሜ ባለጸጋ የሆኑ አረጋዉያን ይገኙበታል።እነዚህን የተቸገሩ ወገኖች ለመርዳትና መልሶ ለማቋቋም በመላው አለም የሚገኙ የኦሮሚያ ተወላጆችና ለሎችም ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻቸው ትብር እያደረጉ እንደሚገኝ ይታወቃል።ሰዎች በበጎ አድራጎት ተፈናቃይ ወገኖችን ለመርዳት በሚረባብረቡበት ወቅት አጋዚ ወደ መጠለያ ካምፕ መጥቶ የጥይት እሩምታን ማርከፍከፉ ህወሃት ህዝቡን በጠላትነት እንደፈረጀው አመላካች ነው ሲሉ የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

የአገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት መለዮ የለበሱ ታጣቂዎች የተፈናቃዮችን ደህንነት መጠበቅ የሚገባቸው ቢሆንም፤ በችግር ላይ ባሉት ዜጎች ላይ የጥይት እሩምታ መክፈታቸው «አጥፍቶ የመጥፋት ተልእኮና የሽብር ተግባር ነው» የሚል አስተያየት እየተሰጠበት ነው። ይህንን መሰሉ የሽብር ተግባር ከህወሃቱ አጋዚ በስተቀረ በተደጋጋሚ ሊፈጽም የሚችል ሐይል እንደሌለ የሚያስረዱት ያካባቢው ምንጮች የስርዓቱን የተሐድሶ ዲስኩር መልሶ መላልሶ ዜጎችን ለመግደል የሚቀርብ የሽንገላ ወሬ ነው ሲሉ ያጣጥሉታል።

በህወሃት የሚመራው የአጋዚ ጦር ቀደም ሲል በዚሁ ሐማሬሳ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ዉስጥ ከ10 የሚበልጡ ሰዎችን መግደሉ ይታወሳል።ይህንንም ቀጣይ የግድያ ወንጀል ቃኝተናል የሚሉ የመብት ተሟጋቾች ህወሃት የዜጎችን ደህንነት ከማስጠበቅ ይልቅ ዜጎችን አያደነ በጥይት መድፋቱ የህዝብና ቁጣ የሚያንር፣ህዝብና መንግስትን የሚያቃቅር ነው በማለት ያስረዳሉ።

ህወሃት በዚሁ ከቀጠለና እራሱን አሻሽሎ ለአለም አቀፍ መርሆዎች ተገዢ የማይሆን ከሆነ ወጥ የሆነ ህዝባዊ እምቢተኝነት የሚቀሰቅስ ይሆናል፣ ተቃዉሞ ያነሳሳል፣ጉዳዩ ‹ከድጡ ወደ ማጡ ነው!› የሚሆንበት በማለት ያለፉትን ወራቶች የለውጥ ሒደቶች የሚቃኙ ተንታኞች ያስረዳሉ።

ህወሃት ከሶማሊያ ክልላዊ መንግስት ጋር በመቀናጀት እንዲፈናቀሉ ያደረጋቸው ንጹሗን ዜጎች መገደላቸው እስከመቼውም ይቅር የማይባል ወንጀል መሆኑን የሚያስረዱት የሐማሬሳ ምንጮች የነርሱንም ሆነ የሌላዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ለማስጠበቅ የተጀረው ህዝባዊ እምቢተኝነት ተጠናክሮ ቀጥሎ ሁነኛ እና መሰረታዊ ለዉጥ ባገሪቱ ዉስጥ ሊመጣ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ BBN

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.