የአዲስ አበባ የታክሲ ባለንብረቶች ቦንድ ካልገዛችሁ ታፔላ መውሰድ አትችሉም መባላቸውን ገለጹ።

7811AddisTaxisበአዲስ አበባ በ10ሩም ክፈለ ከተሞች ለከተማው ነዋሪ የታክሲ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የታክሲ ባለንብረቶች እንደገለጹት ከሆነ በዛሬው እለት ታፔላ ለማሳደስ እና አዲስ ታፔላ ለማውጣት ወደመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣና ያቀኑት የታክሲ ባለንብረቶች እና ሹፌሮች ለአንድ ታፔላ የ500 ብር የአባይ ቦንድ ካልገዛቹህ ታፔላ አትወስዱም መባላቸውን ገልጸው በዚህም የተነሳ ባለንብረቶቹ ከመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ሰራተኖች ጋር ከፍተኛ እሰጣ እገባ ውስጥ የገቡ ሲሆን የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እኛ የምናውቀው ነገር የለም መመሪያው የመጣው ከላይ ነው እኛ የመጣላችሁን ስሩ ብቻ ነው የተባልነው በማለት ምልስ ሰጥተዋል።

ቦንድ ካልገዛችሁ ታፔላ አትውስዱም መባሉን ተከትሎ በዛሬው እለት በርካታ ታክሲዎች ከስራ ውጭ ሆነዋል ቦንድ ገዝተው ታፔላ የውሰዱት ባለታክሲዎችም ቢሆኑ ቁጥራቸው አነስተኛ በመሆኑ ለወትሮውም መጨናነቅ የሚታይበት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት በዛሬው እለት በባሰ ሁኔታ መጨናነቁን ክስፍራው ያገኘሁት መረጃ ያስረዳል።

‪#‎ሁኔአቢሲኒያ‬

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.