ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብ ውስጥ የነበረው ሽመልስ ከማል አሜሪካ ገባአርአያ ተስፋማሪያም –

shimelsየኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ የመጣው በግሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።

በዲሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ወንድሙ ዘንድ ያቀናው ሽመልስ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ለመቅረትአርአያ ተስፋማሪያም –

የኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ የመጣው በግሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።

በዲሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ወንድሙ ዘንድ ያቀናው ሽመልስ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ለመቅረት ሃሳብ እንዳለውና እንደሚፈልግ ምንጮቹ አጋልጠዋል።

ሽመልስ ከማል – አፋኙን የፕሬስ ህግ በማርቀቅ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከህትመት ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች ላይ የሞት ቅጣት እንዲበየን በመጠየቅ፣ እነእስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት እንዲፈረድባቸው በማድረግ፣ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች እስር ቤት እንዲገቡና በሽብርተኝነት እንዲከሰሱ በማድረግ እንዲሁም ሙስሊሙንና ተቃዋሚዎችን በጅምላ በመስደብና በማንጓጠጥ፣ ብርቱካን ሚዴቅሳ ለ2 አመት በጨለማ እስር ቤት እንድትማቅቅ በመፍረድ..ወዘተ የመብት ረገጣ ያካሄደና በበርካታ ወገኖች ህይወት ላይ የጭካኔ ፍርድ ያሳለፈ እንደሆነ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.