በዓለማችን ትልቁን የማፍያ ቡድን ያውቁታል?? (ማሙሽ ከማል)

እንግዲያውስ ስትሰሙ እንዳትደነግጡ . . . . ረጋ ብላቹ አንብቡት፡፡

Ndrangheta syndicate ይባላል፡፡ ዋና መቀመጫውን በጣልያኗ ካላበሪያ ከተማ ያደረገው ይህ ግሩፕ እንደ ኤ .አ በ1960 ዓ . ም የተመሰረተ ሲሆን ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ከኮሎምብያ እስከ አውስትራልያ የተዘረጋ ግዙፍ መረብ አለው፡፡ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በሗላ በቀጠናቸው ካላብሪስ የሚተላለፉ ስደተኞችን በማገት ስራውን ሀ ብሎ የጀመረው ቡድኑ ለተከታታይ አስር ዓመታትም እያገቱ ቤዛ ሊሆናቸው የሚችለውን በመልመልና በማሰልጠን ኮኬን የተባለውን አደገኛ ዕፅ ለማምረት መጠቀም መጀመራቸው ለቡድኑ እዚህ መድረስ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ ይነገራል፡፡

አብዛኞቹ የካላብሪያ ከተማ ነዋሪዎች ከዙህ ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል፡፡ በተለያየ አለም ላይ ያሉ የቡድኑን ካምፓኒዎችም በዚሁ ከተማ ተወላጆች ስውር ጠባቂነት የሚንቀሳቀሱ ሲሆን የቤተሰባቸው በከተማዋ መቀመጥ እንደ ተያዥ ይቆጠራል፡፡ ማንም ከቡድኑ የመገንጠል ጥያቄ ቢያነሳ ተቀባይነት አኖረውም፡፡ በድብቅ ከቡድኑ የተገነጠለ እንኳን ቢኖር ተከታትለው ይገሉታል፡፡ ለምሳሌ ካርሜሎ ኖቬላ የተባለ የቡድኑ የሎምባርዴ ክንፍ ሃላፊ የተወሰኑ የቡድኑን እሴቶች ይዞ ለመገንጠል ሲሞክር በ2008 ተገሏል፡፡

ይህ ቡድን ከውንብድና ስራው ውጭ ማንኛውም ለቡድኑ አስጊ የሆነን መንግስታዊም ሆነ የሌላ ማፍያ ቡድን አባል እሳዶ በመግደል የተዋጣለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በ1992 እና በ1994 ዓ. ም ሁለት ከፍተኛ የጣልያን የፀረ-ማፍያ ቡድን ግብረሃይል ሃላፊዎችን ገለዋል፡፡ የጣልያን መንግስት መሰል የማፍያ ቡድኖችን ለማጥፋት ብዙ ግዜ የፀረ- ማፍያ ህጎችን አውጥቶ ቢንቀሳቀስም በዚህ ቡድን ላይ ግን ሊሳካለት አልቻለም፡፡

ከሲሲሊ ፤ ኮሰታስትራስ ከተባሉ መሰል የማፍያ ጉርፖች እጅግ ስውርና ከባድ የአሰራር አደረጃጀት ያለው ይህ ቡድን 80% የሚሆነውን የአውሮፓ የኮኬን ዝውውር ብቻውን እንደሚሰራ ይነገራል፡፡
ባሁን ግዜ በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ከ500 በላይ ትላልቅ ካምፓኒዎች አንዳሉት ይነገራል፡፡ ከቅርብ ግዜ የሽብርተኞች እንቅስቃሴና የአውሮፓ የኢኮኖሚ ቀውስ ለቢዝነሳቸው ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረና ትርፋማነታቸውን እንዳሳደገው ይነገራል፡፡

ባሁን ሰዓትም 60 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ካፒታል እንዳለቸው ይነገራል፡፡
ይህ ማለት ከጣልያን የጂ .ዲ ፒ (GDP) መጠን ሶስት ፐርሰንቱ መሆኑ ነው፡፡
ወይም የአባይን ግድብ በጀት 11 እጥፍ ማለት ነው፡፡

11019585_1727717780787801_6516808062713285862_n (1)

በፎቶው ላይ የምትመለከቱት በቅርብ በቁጥጥር ስር የወዋለ ከቡድኑ ዋና አንቀሳቃሾች አንዱ ነው፡፡