107 ሻማዎች ሊበሩላቸው የሚገባቸው አባት! (ከአድናቂዎቻቸው)

Aba“ በእኔ ሀላፊነት የተገዛላቸውን ሙሉ ልብስ ፤ የተዘጋጀላቸውን ፓስፖርትና የኪስ ገንዘብ አስረክቤ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ውጭ ሀገር ከሸኘሗቸው መሀከል ፕሮፌስር አሥራት ወልደየስ አልነበረበትም። ቀደም ሲል በእንግሊዞች አስተባባሪነት ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተላከ ነው ። ለሀገራችሁ ያብቃችህ ብዬ ከሸኘሗቸው መሀከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረው ዶ/ር ምናሴ ሀይሌ፤ የጃንሆይ ችሎት ልዩ ፀሀፊ የነበረው አቶ መሀመድ ሀሚድ ኢብራሂም፤ እንዲሁም እነ ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ ይገኙበታል። አክሊሉ ወደ ሀገሩ ከተመለሰ በሗላ በተለያዩ ሀላፊነቶች አገልግሏል ። የቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንትም ነበረ ፤ ዛሬ በህይወት ከሉት የወቅቱ ወጣቶች አነዱ ነው። ከጥቂት ዓመት በፊት አሜሪካ ነዋሪ የሆኑ ልጆቼ ለጉብኝት ጋብዘውኝ ባጋጣሚ ፀሎት ከሚያደርግበት ቤተክርስቲያን ተገናኝተን ሰላምታ ተለዋውጠናል፤”

—[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-