አስገራሚ ዜና! – በአዲስ አበባ አዲስ ክ/ከተማ የህገ ወጡ መጅሊስ አመራር የሆኑት አቶ አብዱ እና አቶ ሰኢድ በተለያዩ ክሶች ወደ እስር ቤት መግባታቸውን ታወቀ!

አቡ ዳውድ ኡስማን

በአዲስ አበባ አዲስ ክ/ከተማ የህገ ወጡ መጅሊስ ሰብሳበቢ የሆነው አቶ አብዱ እና የክፍለከተማው የመስጂድ እና አውቃፍ ዘርፍ ሃላፊ የነበረው አቶ ሰኢድ በተለያዩ ክሶች ወደ እስር ቤት መግባታቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ክ/ከተማ ህገ ወጡ መጅሊስ የመስጂድ እና አወቃፍ ዘርፍ ሃላፊ ተደርጎ በመንግስት የተሾመው አቶ ሰኢድ ኢብራሂም በህገ ወጥ መንገድ የግል ጥቅምን ለማስከበር በሚል ሊከሰስ መሆኑን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ቀኑ ደርሶም መንግስት ወደ እስር ቤት እንዲገባ እንዳደረገው ታውቋል፡፡

አዲስ ክ/ከተማ ህገ ወጡ መጅሊስ የመስጂድ እና አውቃፍ ዘርፍ ሃላፊ ተደርጎ ተሹሞ የነበረው ሰኢድ ኢብራሂም የተባለው ግለሰብ ከአዲስ ክ/ከተማ ህገ ወጡ መጅሊስ ሰብሳቢ ከነበረው አቶ አብዶ ጋር በነበረው ቅራኔ በመሳሪያ አውጥቶ አስፈራርቶኛል በሚል ክስ ባቀረበው መሰረት አቶ አብዶ በፖሊስ ታስሮ የነበረ ሲሆን በዋስ ተለቆ ጉዳዩን ሲከታተል መቆዩ ይታወቃል፡፡

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው ፍርድ ቤትም አቶ አብዲ ኢብራሂም በድጋሚ እንዲታሰር ያስደረገው ሲሆን በአሁኑ ወቅት አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ አብዶ ከአሰኢድ ኢብራሂም ጋር በነበራቸው የጥቅም ግጭት የተነሳ የአቶ አብዶ ዘመድ የሆነ የፌደራል ፖሊስ ለዚያራ ቤቱ መምጣቱን ተከትሎ ጠዋት ላይ ፖሊሱ በተኛበት አቶ አብዱ የፖሱን ሽጉጥ ይዞ በመውጣት ወደ ሰኢድ ኢብራሂም ጋር በመሄድ በሽጉጡ እንዳስፈራራው ታውቋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ሰኢድ ኢብራሂም ለፖሊስ ክሱን ያቀረበ ሲሆን አቶ አብዶ ጫት እየቃመ ከነበረበት ቦታ ላይ በፖሊስ ተይዞ መታሰሩን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አቶ አብዱ ፍርድ ቤት ቀርበው ለምስክር የቀረቡባቸው ግለሰቦች ተመሳሳይ የሆነ ነገር ባለመመስከራቸው ዳኛው በዋስ እንዲለቀቅ እንደወሰነለት ተዘጓል፡፡ አቶ አብዱም ከተፈታ ቡሃላ ከሚኖርበት አዲስ ክ/ከተማ ፈትህ አባቦራ መስጂድ አካባቢ ሲፎክር እና የሰፈር ምቀኞች ይኸው እኔስ ተፈታው እያለ በአደባባይ ሱለፈልፍ መታየቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ይህ ግለሰብ በክፍለከተማው የሚገኙ መስጂዶችን ከመንግስት ጋር በመሆን ሲያስነጥቅ የነበረ ሲሆን በርካታ ሙስሊሞችን እንዲታሰሩ ያደረገ ግለሰብ ሲሆን በሰለሃዲን መስጂድ በሙስሊሞች ላይ በተፈጸመው መንግስታዊ ሽብር ትልቁን ሚና ሲጫወት የነበረ ግለሰብ መሆኑ ታውቋል፡፡ እንዲሁም በኮልፌ ቁባ መስጂድም ሙስሊሞች ሁለተኛ ጀምአ ለምንሰገዳችሁ በሚል ሲያሳስር እንደነበር ታውቋል፡፡

በሚኖርበት አካባቢ ላይም በሙስሊሞች ላይ ሲፎክር የቆየ ሲሆን ይህን በተናገረበት ምላሱ አሁን ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው ፍርድ ቤት በድጋሚ እንዲታሰር ያደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም አራተኛ ፖሊስ ጣብያም ታስሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመሳሳይም በሽጉጥ አስፈራርቶኛል በማለት ክስ ያቀረበው ሰኢድ ኢብራሂም የተባለው ግለሰብም በህገ ወጥ መንገድ የራስን ጥቅም ለማስከበር ተንቀሳቅሰሃል በሚል ተወንጅሎ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲታሰር መደረጉን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ ክ/ከተማ ህገ ወጡ መጅሊስ መሰጂድ እና አውቃፍ ዘርፍ ሃላፊ ነበረው ሰኢድ ኢብራሂም ፈድሉ ከተባለው ባልደረባው ጋር ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተወስደው መታሰራቸው ታውቋል፡፡

በአዲስ ክፍለ ከተማ በሚገኘውን በቁባ መስጂድ ስር ካሉ ሱቆች ውስጥ አቶ ሰኢድ ከተከራይዋ 80.000 ብር የኪራይ ገንዘብ ከአቶ ፈድሉ ጋር በመሆን ከተቀበሉ ቡሃላ ለአዲስ አበባው መጅሊስ ገቢ ባለማድረጋቸው ሊከሰሱ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም በአዲስ ክ/ከተማ መርካቶ አደሬ ሰፈር የሚገኘውን የባዩሽ መስጂድን በየተራ በየቀኑ እንዲጠብቁ ከተመደቡት የአዲስ ክ/ከተማ ህገ ወጥ መጅሊስ አባላት መካከል ለአባላቱ ከሚከፈላቸው የቀን አበል መካከል የ 9 ቀናት የቀን አበላቸውን አቶ ሰኢድ ኢብራሂም እና አቶ ፉአድ ለግላቸው ማዋላቸው ታውቋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከፍተኛ ምርመራ ከተካሄደ ቡሃላ ወደ እስር ቤት እንዲወረወር መደረጉ ተዘግቧል፡፡

ሰኢድ ኢብራሂም የተባለው ግለሰብ በኮሚቴዎቻችን እና በበሌሎች ሙስሊሞችም ላይ በሀሰት ሲመሰክር የነበረ ግለሰብ ሲሆን መንግስር ከተጠቀመበት ቡሃላ ወደ እስር ቤት እንደወረወረው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ ግለሰብ ከኮሚቴዎቻችን ላይ በካሚል ሸምሱ፤ አህመዲን ጀበል፤ያሲን ኑሩ ሙሃመድ አባተ፤ አቡበከር አህመድ ላይ ያልሰሩትን ሰሩ ያላሉትን አሉ በማለጽ በሀሰት ፍርድ ቤት የመሰከረ ሲሆን በተለይም በኡስታዝ አቡበከር አህመድ ላይ በአንዋር መስጅድ ክርስቲያኖችን በገጀራ ከትክቷቸው ብሏል በማለት በሀሰት ፍርድ ቤት ቀርቦ መመስከሩ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም በነ ሙኒር አጽብሃ መዝገብ በተከከሰሰው አብዱረዛቅ ላይ የሀሰት ምስክር ሁኖ በመቅረብ ከአንድ አመት ከአራት ወር በላይ እንዲፈረድባቸው ማደረጉ ይታወሳል፡፡ በባዩሽ መስጂድ ጀምአ በነበረው ወንድም ሷዲቅ ላይም በሃሰት መስክሮ ያሳሰረው ሲሆን በሃምሌ 11 በተፈጠረው ችግር ላይም በወንድም ተማም ላይ በሃሰት መመስከሩ ታውቋል፡፡

በቅርቡም በአዲስ ክ/ከተማ ነዋሪነቱ ያደረገውን ኑርሁሴን የተባለ ሙስሊም ወንድም ላይ በግድግዳ ላይ ሙስሊሞች 2007 ምርጫን አንካፈልም፣ካድሬዎች ከመጅሊሳችን ይውጡልን ብሎ ሲፅፍ አይቸዋለው በማለት ባሀሰት መስክሮበት የ 7 ወራት እስራት እንዳስፈረደበት ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ወንድም ኑር ሁሴን በተያዘበት ወቅት ፍርድ ቤት ቀርቦ በ 10.000 ብር ዋስ የተለቀቀ ሲሆን ጉዳዩን ከውጪ ሆኖ ሲከታተል ቆይቶ አቶ ሰኢድ በሃሰት መስክሮበት የ 7 ወራት እስራት እንደተበየነበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

መንግስትም ለዚህ ውለታው ከፍትህ ሚኒስትር የምስጋና ደብደዳቤ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደግሞ በየወሩ ተቆራጭ ተደርጎለት የነበረ ሲሆን በተጨማሪ የቀበሌ ቤት ተሰቶት እንደነበር ታውቋል፡፡ ሙስሊሞች በታሰሩ ቁጥር በፍርድ ቤት በሀሰት ሲመሰክር በመቀየቱ በአዲስ ክ/ከተማ መጅሊስ ውስጥም የመስጂድ እና አውቃፍ ዘርፍ ሃላፊ ተደርጎ ወርሃዊ ደሞዝ እየተቀበለ መቆየቱ ተዘግቧል፡፡

አቶ ሰኢድ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከተለቀቁ ቤቶች ውስጥ መንግስት የሚኖርበትን ቤት የሰጠው ሲሆን ሚስቱ እኔ አስቸኩዬው እንጂ ሙሉ ግቢ ለብቻው ነበር ከበላይ አካል የታዘዘለት በማለት በየሰፈሩ በሙስሊሙ ላይ ስትፎክር መቆየቷ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የአቶ ሰኢድ ሚስቱ ቀበሌው ከሸለማቸው ቤት ከገቡ ቡሃላም ከጎረቤቷ ጋር ስትጋጭ የነበረ ሲሆን ለጊዜው ነው እንጂ የተሻለ ቤት ይሰጠናለ በማለት በአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ ስትመፃቅ መቆየቷ ታውቋል፡፡ የአቶ ሰኢድ ባለቤት በወቅቱ እርጉዝ ስለነበረች ከወለደች ቡሃላ ባለሙሉ ግቢ ቤት ውስጥ መንግስት እንደሚየስገባት በየሰፈሩ ስትፎክር ከቆች ቡሃላ ከ 2 ወራት በፊት የተባለውን ባለ ሙሉ ግቢ የመንግስት የቤት ሽልማት ሳታየው ወደ አኼራ መኼዷን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

አቶ ሰኢድ ባለቤቱ ከሞተች ሁለት ወራት ሳይቆይም መንግስት እንዳሻው ሲጠቀምበት ከቆየ በሁላ በመጨረሻም አብሮት በሀሰት ሲመሰክር ከነበረው ፈድሉ ከተባለ ግለሰብ ጋር በህገ ወጥ መንገድ የራስ ጥቅም በህገ ወጥ መንግድ ለማስከበር በመንቀሰቀስ በሚል በቂልንጦ ማረሚያ ቤት እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል፡፡

አቶ ሰኢድ ኢብራሂምም በመንግስት ተወንጅሎ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተወረወረ ሲሆን በማረሚያ ቤቱ ታስረው የሚገኙ ራሳቸውን ዱርየ ብለው የሚጠሩ ቡድኖች ከታሳሪዎች በጣም የሚጠሉት በግብረሰዶም የተከሰሰን እና በሀሰት ሲመሰክር የኖረን ሰው በመሆኑ አቶ ሰኢድ ኢብራሂምን እንዴት በኡስታዝ አቡበከር ላይ በሃሰት ትመሰክራለህ በማለት እንደፈነከቱት ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

የማረሚያ ቤቱ ፖሊሶችም ጉዳዩን ለማረጋጋት ከሞከሩ ቡሃላ ደብዳቢዎቹን በመለየት ይህንን ድብደባ የፈጸማችሁት ኮሚቴዎቹ ከፍለዋችሁ ነው በማለት በኮሚቴዎቻችን ላይ ለማላከክ የሞከሩ ሲሆን ዱርየዎቹ ግን ሙስሊሞችን የምናውቃቸው በመልካም ስነ-ምግባራቸው ነው ቅጣት የሰጠነው የሀሰት መስካሪ በመሆኑ ነው በማለት ምላሽ እንደሰጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡የማረሚያ ቤቱ ፖሊሶችም ጉዳዩ በመያዝ ክስ ለመመስረት እየተዘጋጁ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

በዞን ሁለት ያሉት ዱርዬ የሚባሉት ቡድች ድብደባውን ከፈጸሙበት ቡሃላ በድጋሚ ይደበድበታል በሚል ስጋት አቶ ሰኢድ ኢብራሂምን ወደ ዞን ሶሰት እንዲቀየር ያደረገት ሲሆን በዞን ሶስት የሚገኙ ዱርዬ ብለው እራሳቸውን የሚጠሩ ቡድኖችም እንዴት በሃሰት ትመሰክራለህ በማለት ሊደበድቡት ሱሉ በዞን ሶስት ታስረው የሚገኙ ኮሚቴዎቻችን እና ሙስሊም ታሳሪዎች እንዳስጣሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዞን ሶስት የሚገኙ ሙስሊሞች ከድብደባው ካስጣሉት ቡሃላ አቶ ሰኢድ ኢብራሂም እምባ ተናንቆት “ይህ አምባገነን መንግስት በጥቅምና በማስፈራራት አይኔን አውሮኝ መልሶ እኔኑ አሰረኝ ፡፡ ዛሬ ዱርየዎች ሊደብድቡኝ ሲሉ የደረሱልኝ ትላንት በሀሰት የመሰከርኩባቸው ናቸው፡፡ ባለቤቴን በሞት የነጠቀኝ እና እኔን ያስረኝ አላህ እንድቶብት ነው” ሲል ማልቀሱ ተዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በዞን ሶስት የሚገኙ ዱርየዎቹ ሳይታሰር በፊት በሰጠው የሀሰት ምስክርነት ለመደብደብ እንደሚፈልጉ የታወቀ ሲሆን የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎችም ድብደባ ከተፈጸመበት ሙስሊሞቹ አስደበደቡበት በማለት ክስ ለመመስረት እያሴሩ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ሱብሃን አላህ በሙስሊሞች ላይ ግፍ እየሰሩ የሚገኙ ሙስሊሞችን በዱኒያ አላህ እንዲህ እያዋረዳቸው ይገኛል፡፡

ይህ ለሁላችንም ታላቅ ትምህርት ነው፡፡ በተለይም ሙስሊሞችን ከመንግስት ጎን በመሆን እያስጠቁ ለሚገኑ ወገኖች ትልቅ ትምህርት ሆኖ አልፏል፡፡

አላህ አሁንም ሙስሊሞችን እየበደሉ የሚገኙ ግለሰቦችን እንዲህ ያዋርዳቸው!!

10858405_810618135685936_8431086323425063794_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.