መልስ ለቬሮኒካ መላኩ “ትግራዮች እና የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ ሁለቱ የተለያዩ ነገዶች /ብሔሮች ናቸው !” በማለት ስለ ጻፈቺው

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)

ይህ ታሪካው ሰነድ አስደግፌ ብዙ ሰው ያላወቀውን ሰነድ/ጽሑፍ ስታዩ የቬሮኒካን ጽሑፍ የለጠፋችሁ እኔ ያላየሁዋችሁ ድረገጾች ካላችሁ እባካችሁ ይህንን የኔን መልስ ኮፒ/በማድረግ ድረገጾቻችሁ ላይ ለጥፉት። በስንት ድካምና ምርምር ያገኘሁት ሰነድ ስለሆነ፤ ሙያችሁም ለማስተማር ከሆነ በአድልዎ ሃይቅ መዋኘቱን አቁሙና ለጥፉት።

አንባቢዎቼ ቬሮኒካ መላኩ ማን ናት የሚለው ከኔ መልስ ለማግኘት አትጠብቁ። በትክክል ልነግራችሁ  የምችለው  ግን  “ዘረኝነት  የሌለበት  ብሔርተኝነት ለአሁኑ የአማራ ትውልድ ያስፈልገዋል”፡ እያለች ስለ አማራ መደራጀት በግምባር ቀደም የምትከራከር ጸሐፊት ነች (ነች የምልብትም ከመጀመሪያ ስሟ በመነሳት ነው)። ሆኖም እውን ቬሮኒካ ዘረኝንትን ትጠላለች? ሕዝብን ከሕዝብ ለይቶ ከማራራቅ የራቀች ጸሐፊት  ነች?  መልሱ  አይደለችም።በ2/8/2018 (ፈረንጅ   አቆጣጠር)    በዘሐበሻ፤በኢትዮጵያን-ረቪው፤በሳተነው፤ ምን-አለፋችሁ በብዙ ድረገጾች  ጽሑፍዋ  ለጥፈውላታል።  አስገራሚ  የሚያደርግው  ይህ  የትግራይ ሕዝብ መረን የለቀቀ የጥላቻ ጽሑፍ በጥላቻ የታወሩ ‘የዛሬዋ በጣሊያን የተሰየመች ኤርትራ የጥንትዋ የባሕሪ ነጋሲ ልጆች እና የኢትዮጵያ ትግሬዎች “ትግራዮች እና የኤርትራ ብሄረ ትግርኛ ሁለቱ የተለያዩ ነገዶች /ብሔሮች ናቸው !የትግራይ ሕዝብ ብሄርተኞች የማንነት ቀውስና የትግራይ ትግርኛ ቅዠት (ቬሮኒካ መላኩ)” የሚለው ጽሑፍዋ በማያስፈልጋቸው ማንነት ፍለጋ ቀውስ ውስጥ የሚቃዡት “ኤርትራኖች” ጽሑፍዋን ወድደውላት ኤርትራ ድረገጾች በብዙዎቹ ለጥፈውላታል። አንዱን ልስጣችሁ፤ናይ ብሄረ – ትግራይ ናይ መንነት ቅልውላውን ሕልሚ ትግራይ ትግርኝን መጽናዕቲ ፥ ብቪሮኒካ መላኩ ትርጉም ፥ ብኢብራሂም መሓመድ

http://www.erinahda.org/index.php/eritrean-website-links/meskerem

ይህ ድረግጽ “የሻዕቢያ ነው።

 

መስከረም .ኔት ላይ ኢሳት ቴ/ቪዥን እና የግንቦት 7 ዜና በየቀኑ የሚተላለፈውን  እዛው ተልጥፎ ታገኙታላችሁ። ይህ የቬሮኒካ መላኩ ደንቆሮ ጽሑፍ ኢብራሂም መሓመድ የተባለ ኤርትራዊ ሻዕቢያ ወደ ትግርኛ ትርጉሞ ለጥፎታል። ያስሳቀኝ ደግሞ “የቬሮኒካ ጥናታዊ ጽሑፍ” ብሎ ጽፎታል። የቬሮኒካ ጥናታዊ ጽሑፍ እና የሻዕቢያ ጭብጨባ የምያሳየኝ ቬሮኒካም ሆነ ኢብራሂም መሓመድ እራሳቸውን ማጥናት ያልቻሉ መሆናቸውን ያሳያል። ቬሮኒካስ እሺ ይሁን እንበል; የሁለቱ ሕዝቦች ወንድማማችና እሕትማማችነት (ያንድ ቤተሰብ አጥንት ደም የተገኙ) መሆናቸውን ታሪክን አላወቀችም እንበል፡ ኢብራሂም መሓመድ ግን የትግራይ፤ የአማራ ነገዶች ኤርትራን እንዴት እንደመሠረትዋት ከ1981 ዓ.ም (ኢትዮ- ዘመን አቆጣጠር) ጀምሮ በሻዕቢያ  ታዋቂ  ሰዎች  የተገመገመ  ዛሬም  አስመራም  ውስጥ  ታትሞ የተሰራጨ የ300 አመት በላይ የተነገረውን አፈታሪክ ተለቅሞ በስዊዲናዊ አንትሮፖሎጂሰት ኮልመዲን እና በኤርትራ አውራጃዎች ካሉት ታላላቅ የነገድ አዋቂ ሰዎችና ባላባቶች (ዘሮች)

 

በሰጡት ቃል በተደረገው ጥናት በኤርትራዊው “መብራህቱ ዮሃንስ” አሳታሚነት የታተመውን የታሪክ ምርምር መጽሐፍ እንዴት ማንበብ እንዳልቻለ ገርሞኛል።

 

የኤርትራ ብዙዎቹ ቦታዎች ስሞችና የትውልድ ሐረጎች እየተጠሩ ያሉት በነዚህነገዶች ልጆች እና ልጅ ልጆች ቅድመ አያቶች መሆናቸውን በኤርትራኖቹ በራሳቸው እና በዮሐንስ ኮለመዲን (ስዊዲናዊ ትግርኛ ጣር  መጻፍን  መናገር  የቻለ  ባ1904  በራሳችን  ዘመን አቆጣጠ አገሩ ሄዶ በሞት የተለየ) ዋና አዘጋጅነት የተጻፈ በጥንት የትግርኛ አጻጻፍ ዘይቤ በተጻፈ መጽሀፍ እና ሌላም በሌላ ኤርትራዊ ጥንታዊ ያካባቢው ሕግና ትውልድ የሚያሳይ የትግርኛ መጽሐፍ የተጻፉ ሁለት በትግርኛ የተጻፉ ጥንታዊ መጽሐፍቶች መረዳት ነበረበት።

 

ቬሮኒካ መላኩ የአማራን ታሪክ አውቃለሁ ስትል ትግራይ እና ከመረብ ምላሽያሉት ትግርኛ ተናጋሪ ቤተሰቦች እንዲሁም “ሕዝባይ” የተባለ ኤርትራዊ የሓማሴን ተወላጅ ወደ ከአማቹ ጋር ተጣልቶ ጎንደር ለአቤቱታ ሄዶ 2 አመት ተቀምጦ ካንዲት ከአማራ ጎንደሬ የወለደው ዝነኛው “አተሽም” (አሁን በዚህ ስሙ እየተጠራ ያለው ዝነኛ ነገድ ከጎንደሬዋ የተወገኙት የደቂ-ሕዝባይ ልጆች ባንድ ዘራቸው የአማራ ዘሮች መሆናቸውንም ቬሮኒካ ያለማወቅዋ የሚገርም ነው። ቬሮኒካ ለምን እንዲህ ወዳለው የዘቀጠ ብልሽት ገብታ አንባቢን ልታስተምር እንደፈለገች የምታውቀው ራሷ ብትሆንም፤በኔ ግምት ግን በማንነት ቀውስ እየተሰቃዩት ያሉት እነ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚፈጥሩትን የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ ተንተርሳ እንጂ ታሪኩን በሚገባ ገብቷት እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ።

 

ከዚህ ቀጥሎ የማቀርበው ማስረጃየ “ዛንታ ሀዘጋን ጸዐዘጋን” የሀዘጋና የጸዐዘጋ (ሐማሴን) ከሚል የትግርኛ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ የጻፈው ስዊድናዊው ታዋቂው “ኮልምዲን የሃንስ” እና ባህታ ተስፋጽዮን በሚባሉ በዛው ዘመን ሲኖሩ በነበሩ ታዋቂ ባላባት ሰውየ ጋር ሆነው በሓመሳኔ፤ሰራየ፤አከለጉዛይ…….ያሉትን ነገዶች እየዞሩ አዋቂዎች፤ ሽማግሌዎች፤ ተወልጄዎች፤ የገዢ  መደብ  ባላባቶች፤ቀሳውስት፤ቃዲዎች….ወዘተ ባደረጉት ቃለ መጠይቆች የተገኘ 289 ገጽ ያካተተ በርካታ ያካባቢ እና የነገዶቹ ቦታዎች የሚገልጽ እጅግ የቆየ በጥንት የትግርኛ አጻጻፍና ያነጋገር ዘይቤ የተጻፈ መጽሐፍ ነው።

 

ትግረኛው አጅግ ጥንታዊ ከመሆኑ የተነሳ ቀስ ብለህ ፊደሎቹ በጥንቃቄ ካልተነበቡ ግራ የሚያጋቡ ናቸው። ቋንቋዎች እንዴት በፍጥነት አሁን ወደ አለው አነጋገር ዘይቤ ሊለወጡ እንደቻሉ እጅግ ይገርማል። አሁን ካለው የደገኛው ኤርትራም ሆነ የትግራይ ትግርኛ በጣም የተለጠጠ ርቀት እንዳላቸው ያሳያል። ቬሮኒካ ይህንን መጽሐፍ ብታነብብ ኖሮ በጽሑፍዋ የጠቀሰቺው “ኤርትራ ትግርኛ አነጋጋር ከትግሬዎቹ የተለየ አወጣጥ አለው” የምትለው ዝባዝንኬ እንኳን ቬሮኒካ ኤርትራኖቹ እራሳቸው ይህ መጽሐፍ ሲያነብቡ  የሚሰማቸው የቋንቋው እንግዳነት እንደሚገርማቸው እርግጠኛ ነኝ። በትግራይ በኩልም እንደዚሁ በተመሳሳይ ዘመን የተጻፈው በትግሬው ተወላጅ “ታሪኽ ኢትዮጵያ” የተባለው በደብተራ ፍስሐ አብየዝጊ የተጻፈ የእጅ ጽሑፍም የዛሬዎቹ እኛ ትግሬዎች ስናነበው ለመረዳት የሚሰማንን አንግዳ ትግርኛ አነባብ እኩል ይገርመናል።

 

 

ለቬሮኒካ እና ለቬሮኒካ ወዳጅ ለደንቆሮው ሻዕቢያ እንዲሁም ለኤርትራውያን አንባቢዎቼ ላስገነዝብ የምፈልገው፤ የዛሬቱ ኤርትራ ትውልዶች ከአማራና ከትግራይ ማሕበረሰብ ፈልሰው የተገኙ መሆናቸውን የሰፈረው መጽሐፍ ማንበብ እንጂ በሙሉ ማቅርብ ስለማይቻለኝ ባጭሩ ጥቂት ማስረጃዎችን እንደሚገባችሁ አድርጌ ነው የማሳያችሁ።

 

ቬሮኒካ አማራ ነኝ ትላለች። ከአማራዎቹ ድርጅቶች የአንደኛቸው ትሁን፤ ወይንም እራሱ “ተስፋየ ገብረአብ” ይሁን ብቻ አላውቅም ቬሮኒካን ለማወቅ የምጠረጥረው ቢኖርም በነዚህ ውስጥ ላስቀምጥ። ትግሬዎችን አግልላ እንዲህ ስትል ከኤርትራኖች ጋር እና ኦሮሞዎች አማራው መመስረት ያለበትን ዝምድና እንዲህ ታቀርበዋለች። ኤርትራኖች ከአማራው ጋር

መመስረት ያለበት ዝምድና ሰትገልጽ                                 በሚል ስታስቀምጠው

ኦሮሞ እና አማራ ደግሞ “ ኦሮማራ” (ኦሮሞ ኤርትራ) በሚል ታስቀምጠዋለች። እንዲህ ያሉ ስያሜዎች በማውጣት ሌሎችን በሚያገልል እና ቅር በሚያሰኝ ባሕሪ ያውም ልክ እንደ በሁለት አገሮች ሕዝቦች መካካል ያለ ግንኙነት እያደረጉ አዲስ ስያሜዎችን በመፍጠር “ሰግሪገሺኒስት” የሆነ የህሊና አዲስ አይነት የሕሊና አጠባ በማቀድ አዳዲስ “ነገዳዊ ቡድኖችን” እየፈለፈሉ እያደመጥን እንዳለው ሁሉ፤- ቬሮኒካም ትግራዩን ማሕበረሰብ እማሃል በመጨፍለቅና በማግለል “አማኤር” (አማራ-ኤርትራ) የሚል የማቧደኛ ሴራ በማበጃጀት ይህንን የለያይተህ አገናኝ ሴራ በመሞርከዝ አዲስ ስያሜ ይዛ ብቅ ብላለች።

 

ለዚህ አዲስ ስያሜ ምክንያትዋ አስገራሚው የቬሮኒካ ስትገልጽ እንዲህ ስትል በረዢሙ ያስቀመጠቺውን ቆርጬ ላስነብባችሁ እና ወደ ክርክርዋ እንገባለን። እንዲህ ስትል ልታስተምራችሁ ሞክራለች።

 

<ትግራዮች እና የኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች አንድ ቁዋንቁዋ ከመናገር ውጭ ምንም አይነት የተለየ ታሪካዊ ትስስር እንደሌላቸው ለማሳየት እወዳለሁ።>> ካለች በኋላ በሰፊው እንዲህ ትላለች።

 

<< ይህን ግኑኝነት አማኤር (አማራ-ኤርትራ) ማለት እንችላለን። አንዳንድ ብዝታዎች እየጠሩ ሲሄዱ በአንዴ ወዳጅነት መፍጠር ባይቻል እንኩዋ በጠላትነት መፈራረጅን እና በመፈራራት መተያየትን ይቀንሳል የሚል እምነት አለኝ። በመሆኑም ዛሬ ትግራዮች እና የ ኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች አንድ ቁዋንቁዋ ከመናገር ውጭ ምንም አይነት የተለየ ታሪካዊ ትስስር እንደሌላቸው ለማሳየት እወዳለሁ። ትግራዮች በተለምዶ ትግሬዎች እየተባሉ ይጠራሉ። ይሄ ትግሬ የሚለው ስም ሌላ ኤርትራ እና ሱዳን ውስጥ ካለ ትግረ (ሐይሻ) በሚል ከሚጠራ ብሔር ጋር እንዳይመሳሰል ላስገነዝብ ወዳለሁ። ኢትዮጵያውያን ትግሬ እያልን የምንጠራቸው ባብዛኛው አሁን ትግራይ እየተባለ በሚጠራው   ክልል   ውስጥ   በአደዋ፣   ሽሬ(ሽረ)፣ መቀሌ(መቐለ) የሚኖሩትን ትግርኛ ተናጋሪዎች ሲሆን አሁን ያሉት እነዚህ ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች የሚኖሩ ትግርኛ ተናጋሪዎች ራሳቸውን በክልላቸው ስም ትግራይ እንዲሁም ተጋሩ እያሉ መጥራትን ይመርጣሉ ። እኔም በዚህ ፁሑፍ ላይ መጠራት በፈለጉበት ስያሜ ትግራዮች

 

እያልኩ እጠራቸዋለሁ። ወደ ዋናው ነገራችን ስንመጣ ብዙ ወገኖች ትግራዮች እና ኤርትራ ብሄረ ትግርኛ አንድ አይነት ብሔር ይመስሉዋቸዋል። በመሰረቱ ግን ሁለቱ ፍፁም የተለያዩ ነገዶች ናቸው። ትግራዮች የ ኤርትራ ብሄረ ትግርኛን ትግራዮች ናቸው አንድ ብሔር ነን ብለው ያስባሉ። ብዙ ትግራዮችም ኤርትራዊ የመሆን ፍላጎት አላቸው። የባድመ ጦርነት ከመነሳቱ በፊት ብዙዎቹ ትግራዮች ራሳቸውን ኤርትራዊ እያሉ ይጠሩ ነበር። ከባድመ ጦርነት በሁዋላ እነዚህ ትግራዮች ከፍተኛ የሆነ የማንነት ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። በተቃራኒው ብሄረ ትግርኛዎች ስለ ትግራዮች ያላቸው ስሜት ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ትግራዮች ወይም አጋሜዎች እያሉ ይጠሩዋቸዋል። (Hassan Adem, M.T., Tekle B, 2010) እነዚህ ኤርትራውያን ብሄረ ትግርኛዎች ትግራዮችን የማይታመኑ እና ልባቸው የማይገኝ አድርገው በአሉታዊ መንገድ ይስሉዋቸዋል። ”Eritreans sometimes contemptuously refer to them-

 cannot be trusted and never could.” (Smith,et al. 2003, Africa, volume 73, p.377) በኤርትራውያን ብሄረ ትግርኛዎች ላይ በተደረገው በዚህ አንትሮፖሎጅካል ማህበራዊ ጥናት ላይ አንድ የ eplf ታጋይ የነበረ ለፕሮፌሰር ሪድ ”አባቶቻችን እና ቅድመ አያቶቻችን እነዚህ ትግራዮች አደገኛ ናቸው በደንብ እናውቃቸዋለን ብለው አስጠንቅቀውናል” ብሎ ኤርትራውያን ነፃነታቸውን ባወጁበት ዓመተምህረት በ አውሮፓ አቆጣጠር በ1991 ወይም በ1983 ኢ.አ ምስክርነት ሰጦ ነበር። “Be careful, these people are dangerous, we know them well!” (Smith,et al. 2003, Africa, volume 73,

p.377 )

ብሄረ ትግርኛዎች ከትግሬዎች የተለየ ማንነት እንዳላቸው እያሳወቁ  ትግሬዎች ብሔረ ትግርኛዎችን እንደራሳቸው ብሄር አድርገው ለምን ይቆጥሩዋቸዋል? ብሄረ ትግርኛዎች ኤርትራዊ የሚባል ሃገራዊ ማንነት ሲገነቡ ትግራዮች ከብሄረ ትግርኛዎች የተለየ ብሔራዊ ማንነት  መገንባት  ለምን  ተሳናቸው?  በትግራዮች  ዘንድ  የሚታየው  የማንነት ቀውስ ምንጩ ምንድን ነው? ለመሆኑ ይህ የብሔረ ትግርኛዎች ለትግራዮች ያላቸው አሉታዊ አመለካከት እንዴት ሊመጣ ቻለ? >> (አንዳንድ ቀለሞች የተጨመሩ)

ትላለች ቬሮኒካ መላኩ ከላይ በሰጠሁት ርዕስ እና ድረገጾች የተለጠፈው።

ይህንን ሳነብ እኔ የሳቅኩት በደንቆሮዋ ቬሮኒካ ሳይሆን በኢብራሂም መሓመድ ነበር። ሻዕቢያ ያችን ድንቁርናውን የሚያስፋፋለት ከኢትዮጵያ አንድ ያላዋቂ ሰው አገኘ እና ይህን ድንቁርና ወደ ትግርኛ ተርጉመላት በሻዕቢያ ድረገጽ ለጠፈላት።

ይህ የቬሮኒካ ኤርትራኖች ትግሬዎች ልባቸው አይገኝም፤ በስማቸው የተሰየመ ኤርትራ ውስጥ አስቸጋሪ መንገድ አለ ወዘተ… (ኢሳትን በተንታኝነት እያገለገለ ያለው የዛሬው ኢሳት አምደኛ ኤርሚያስ ለገሠ በሚባለው የድሮ የወያኔ አገልጋይ ሚኒስቴርም ይህንን ኤርትራኖች የሚቀባጥሩለትን ሲደግመው  አድምጬዋለሁ) ምናምን የሚለው ያልተማሩ ማይሞች የሚያወሩት ድንቁርናን እኔ ንቄ ካልተውኩት የያንዳንዱ ነገድ የሚሰደብበትን ጸያፍ ንግግሮች

 

ወደ መልቀምማ እንደ ደናቁርቱ መልሼ ማስተጋባቱ ወገኖቼን ማስቀየም ስለሚሆንብኝ እንደ ደናቁርቶቹ ወደ ገደል ላለመግባት እሱን ዘልየ፤ ወደ ታሪካዊ ክርክሬ ይዣችሁ ልግባ።

መጀመሪያ ነገር በታሪክ ኤርትራ ውስጥ ከትግራይ ትግሬዎች የተለየ ራሱን የቻለ “ትግርኛ” የሚባል ነገድ ኤርትራ ውስጥ የለም። ይህ የፈጠረው ከትግሬዎች ለመለየት ሻዕብያዎች የፈጠሩት አዲስ የነገድ መጠሪያ ስም ነው። ‘ትግርኛ’ ቋንቋ እንጂ ነገድ አይደለም። ነገዳቸው ልክ እንደ ትግሬ ማሕበረሰብ ‘ትግሬዎች/ተጋሩ/ ናቸው። ሁለቱም ቦታዎች በጥቅሉ በጥንት ዘመን ከብዙ የመጠሪያ ስሞች አንዱ “ምድሪ ትግራይ ትግርኚ” ይባላል ነበር። አጣቃላይ አንድነቱን ለማያየዝ ነው። “ኚ” የሚለው ቃል የገባበት ምክንያትም የተያያዘ/የተለጠጠ/የሠፋ/ ማለት ነው። “መረብ ምላሽ” የሚለው ቃል ከተፈጠረ በኋላ የተፈጠረ ቃል ነው። ላስረዳ ይህ ታሪክ ያገኘሁት ከእናቴ ቢሆንም በዚህ በጠቀስኩት መጽሐፍም ተጠቅሷል። እናቴ መረብ አካባቢ (ዓድዋ አካባቢና ኤርትራ አካባቢ) ባሉት ቦታዎች ቤተሰብ ስለነበርዋት ህጻን ሆና ከብት ጥበቃ ተሰማርታ ወደ ወንዙ እስከ እገላ ጾረና አካባቢ ያሉት በረሃማ ቦታዎች ድረስ ትጠጋ ስለነበር፤ ታሪኩም ቤተሰቦቿ ሲያወሩ  የሰማቺው  (ዢው  ስም  ስሞች ባትጠቅስም በደፈናው የትግራይ እና የምድሪ ሓማሴን “ራዕሲ” የነበሩት ትላቸዋለች የሁለቱ ሰዎች ስም አላወቀቻቸውም እና በደፈናው ስማቸው ሳትጠቅስ) እና እዚህ መጽሐፍ ሳነብም ያገኘሁት ታሪክ ሁለቱ ተመሳሳይ ታሪክ ሀኖ ስላገኘሁት ፤የመረብ ምላሽ ስያሜ ስለገረመኝ እዚህ ልግለጸው።

 

ገዢዎቹ በዚህ መጽሐፍ ባገኘሁት በኮልመዲን ስማቸው ተጠቅስዋል። ባሕሪ ነጋሲ ሰለሙን (በትግርኛ አጣራር ሰለሙን) የተባለ የምድሪ ባሕሪ (ኤርትራ) ገዢ በነበረበት ወቅት ገዢነቱን ለመንጠቅ  ራስ  ሚካኤል  (በዘመኑ የትግርኛ አጠራር ዘይቤ <<ምንኪኤል>> መረብ ወንዝን ተሻግረው ከባሕሪ ነጋሲ ሰለሞን ጋር ከማክሰኞ እስከ ዕሁድ ድረስ 6 ቀን ሙሉ “ዕዳጋ ረቡዕ” በተባለ ቦታ ውግያ አካሄደው ሁለቱም ሳይሸናነፉ ብዙ ድካምና ሞት ስላስከተለ፡ ካሕናት መስቀል ይዘው ሁለቱ ጦርነቱን እንዲያቆሙ ለምነው ዕርቅ በማውረድ፤ ባሕሪ ነጋሲ ሰለሞን ከመረብ ወዲያ ያለው ግዛት፤ ራስ ሚካልም  ከመረብ  ምላሽ ወዲህ ያለው ግዛት እንዲያስተዳድሩ ተስማምተው “የሁለቱ” የሥልጣን ተፏካካሪዎች ደረት “መረብ” ሆነ። ከዚያ ጀምሮ “መረብ ምላሽ” የሚል ቃል መጠቀም ተጀመረ እንጂ ሁለቱም የትግርኛ ተናጋሪዎች ‘ምድሪ ትግራይ ትግርኚ” ነበር ሲባል የነበረው።

1) ስለዚህ ቬሮኒካ << ኤርትራኖች ብሄረ ትግርኛዎች ኤርትራዊ የሚባል ሃገራዊ ማንነት ሲገነቡ ትግራዮች ከብሄረ ትግርኛዎች የተለየ ብሔራዊ  ማንነት  መገንባት  ለምን ተሳናቸው?>>  ሰትል  የምትጠይቀው ድንቁርና ብሔረ ትግርኛ የሚባል “አገራዊ” ማንነት ሲገነቡ የምትለው ስንመለክት ቬሮኒካ ድንቁርን መጠን የለውም።  አገራዊ ማንንት  ሳይሆን  የገነቡት  “የነገድ”  መጠሪያችን  ነው ነው የሚሉት። አገራዊ ማንነት እማ “ኤርትራዊ” በሚል ነው ራሳቸውን የሚጠሩት።

 

2)

ሌላው ቬሮኒካ እንዲህ ትላለች።

 

 

<<ብዙ ወገኖች ትግራዮች እና የ ኤርትራ ብሄረ ትግርኛ አንድ አይነት ብሔር ይመስሉዋቸዋል። <ትግራዮች እና የ ኤርትራ ብሄረ ትግርኛዎች አንድ ቁዋንቁዋ ከመናገር ውጭ ምንም አይነት የተለየ ታሪካዊ ትስስር እንደሌላቸው ለማሳየት እወዳለሁ።>> ስትል እልም ያለ ድንቁርና ስታስነብባችሁ ኢብራሂም መሐመድ የተባለ የሻዕቢያ ግብዝ ድግሞ ይህንን ተቀብሎ ወደ ትግርኛ ተርጉሞታል።

ትስስራችንን ላስረዳ!

 

እትብቴ በተቀበረባት በድንግልዋ መሬት በትውልድ አውራጃየ

በአክሱም ልጀምር።

የታወቁት ሁለት የኤርትራ አውራጃዎቹ ሠራየ እና አከለጉዛይ ከመሰሩትት  ነገዶች ውስጥ  ጎልተው  እስከ  ሓማሴን  ተዘርግተው  ከሚታዩት ከተለያዩ የትግራይ ቦታዎች የፈለሱ እና ከሌሎች እዛ ከነበሩ ነገዶች ነገዶች ተዋልደው በስፋት ከሚገኙት መካከል አክሱሞች አሉበት። የላምዛ ቤተሰቦችና አካባቢ፤ የይሁዳ ዘሮች አጼ ወረደ ምሕረት የተዳቀሉ ናቸው። እነሱም ከአክሱም መጥተው አከለጉዛይ፤ዐዲ እኽሊ ከተባለች ቦታ ሰፈራ  አድርገው  በነበሩበት ወቅት፤ አንዲት “መበለት” (ባልቴት) ለንጉሡ እራት እንዲት ላም ይዛ ወደ “ዐዲ እኽሊ” መጣች። ንጉሡም ዉበትዋና ደግነትዋን አይተው “ላሚቷን” ይዛቻት አንደትሄድ አድርገው እስዋ ግን ከንጉሡ ጋር እንድታድር ተደረገ። ሴቲቱም “ታዲያ ድንገት ጽንስ ብይዝና ወንድ ልጅ ብወልድ የማን ልጅ ልለው ነው?” ስትል ጠየቀቻቸው። ንጉሡም በላሚቷ ሰበብ አይደለም እንዴ አንቺን ያገኘሁሽ? ከወለድሽ እማ ስሙ “ወዲ ዛላም በሊዮ” (ወዲ እዛ ላም) (የዛች የላሜ ቦራ ልጅ) በይው ብለዋት ሄዱ። ከተወለደ በኋላም “ወዲ ላምዛ” (የዛች ላም ልጅ) ተባለ። እሱ ያፈራቸው ዘሮች “ላምዛ” እየተባሉ እስካሁን ድረስ በሃረጋቸው ይጠራሉ። የላምዛ ዘሮችም ለጎ ጭዋ ግማሹም ወደ ሠራየ እና አከለጉዛይ ተዘርግተው በስፋት እየኖሩ ይገኛሉ። ከነሱ  ከታወቁት  7  ላምዛ  እየተባሉ  የሚጠሩት  ቦታዎች  “  ዐደ-ዘማት ዐዲ ላምዛ፤ ዐደቀ፤ ዐጸናፍ ዐዲ ጎምሎ፤ ሕምብርቲ፤ድባሩባ፤ ዐዲ-ነሃባይ ይገኛሉ።

 

ከገረዐልታ (እንደርታ) የመጡ ደግሞ፡

እነዚህም ከጥንት ትግራይ የመጡ ወታደሮች ናቸው። ገለዐንታይ የሚባሉ ዘሮች ሐማሴን ውስጥ “ዐዲ ራእሲ”፤ ክትመውልዕ፤ ሸኸቲ ፤ገብራየ-ኸፈለት። የሚባሉ ቦታዎች ተንሰራፍተው የኖሩ ናቸው።

 

ሎ መኻዳ (ትግራይ) ኤርትራ የሄዱ፡

እነዚህ የአጼ ገብረመስቀል ዘሮች ነን ይላሉ። እምኒ ጸሊም ሠፍረዋል።

 

ከአንረ ባኳ (ትግራይ)

የደግያት (ደጃዝማች) ስብሃቱ፤ገዛ ዐዲ ዕዛር የሚባሉ እምባ ደርሆ ውስጥ የሚኖሩ እነዚህ ሁሉ ከአንከረ ባርኳ የመጡ የአይሁድ ዘሮች ነን ሲሉ ታሪካቸው ለሰው ይነግራሉ።

 

ረ ስሐርቲ (ትግራይ)

እነዚህ ሾብዐተ ሰሐርቲ የሚባሉ ከነገደ ስምኦን ናቸው። እዛው ከመጡ አቶ ሰርማጽ የሚባል እነ ደጃዝማች ፍሬ-ምኻእ አቶ አሰርማጽ፤ ደግያት (ደጃዝማች) ሰምበተይ፤ደጃዝማች ይፈረጅ፤ አጅማች ካራ፤ አጅማች ካራ ደግሞ ደጊያት ማራ፤ ደጊያት ማራ ራስ ፋርስ……..የተዋላለዱ ልጆች የሚባሉ ተባዝተው አሁን ያሉት ሕዝቦች መስረተዋል።

 

ደግያት/ደጃዝማች/ ፍሬ-ምኻእ ከስላዋ (ሳምረ-ሳሓርቲ ትግራይ እንደርታ) መጥቶ “ማይ ጻዕዳ” በሚባል ቦታ ሰፍሮ “ማይ መጣዕ” ተቀብሯል። ፍሬ መኻእ የሚከተሉት ልጆች ወለደ። ጸሊማይ፤እምኒ ጸሊም ወልዶ ጣም በርካታ የሆኑ ዘሮቹ ”ደቂ ሓርሽ፡ “ሕምብረቲ” በሚባሉ ቦታዎች በብዛት አሁንም ይገኛሉ። ደቂ ዕንግዳ (የእንግዳ ልጆች) የሚባሉ ከሳምረ የመጡ የስምኦን ዘሮችም በጣም በርካታ ትውልዶች ወልደው በርካታ ቤተክርስትያናት አሰርተዋል። ከስላዋ -ሰሐርቲ (ሳምረ ትግራይ) የመጡት እስካሁን ድረስ  “ሰሓርቲ”   ተብሎ           የሚጠራው         ገጠር   በነሱ         ስም    የተሰየመ     ነው (ሾውዓተ ሰሐርቲ ሰብዓይ ኮዳዱ”) ከሰሐርቲ የመጡ 7 ትውልዶች…….. ይመስለኛል፤ ትግረኛው ትርጉሙ እጅግ ጥንታዊ ስለሆነ ሙሉውን ትርጉም ለማወቅ ከባድ ነው) ይባላል። እነዚህ ብዙውን ኤርትራ መሬት ሸፍነውታል። በጣም በርካታ ገጽ የያዙ ስሞች እና ስፍራዎች ዘሮች ይዘረዝራል።

 

ሰራየ

ሰራየ ከትግራይ ጋር በመረብ ምላሽ ወንዝ ብቻ የሚለይ አካባቢ አንድ አይነት መልክአ-መሬት ነው። ሐማሴንም ዛግር በተባለ የገጠር  ሰፍረው  የመሰረቱ   ናቸው ነው። ዛግርን የመሰረቱ ከሽሬ አድያቦ (ትግራይ) የመጡ ዘሮች ናቸው። ደቂ ኸዳኒ

፤ደቂ ዘር…….ይባላሉ።

 

ተምቤን

 

ተምቤን አክሱም፤ ድድዋ እና ጎንደር ድምበር ይዋሰናል። ተምቤኖች በተለይ አበርገለ ከሚባል  የተምቤን  ቆላማ  ገጠር  የመጡ  አገዎች” ዛግርም ከሌሎቹ ጋር ሆነው መስርተዋል። በርካታ የሓማሴን ቦታዎች በርካታዎቹ የመሰረቱት እነሱ ናቸው።………………….በክፍል ሁለት ይቀጥላል።ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.