ፓስተሩና ቄሱ የክርስቶስ ሳይሆን የሕወሃት አገልጋዮች ናቸው – ግርማ ካሳ

በቅድሚ የኢሳት አድማጭ እንደሆንኩ ይታወቅልኝ። ኢሳት ከኢቲቪ ( 400 እጥፍ ይሻላል)

10462314_344494249089254_1148989588243014785_n“አሉ አሁንም ፖለቲከኞች አሉ የሚያወሩ። ስንሰባሰብ ሁሉ ጄነራል እንትና ይሄን አድርገው፤ እና ኮሎኔል እንትና …እኔ ስሙን ልከየት እንደሚያመጡት አላወቅም። እንትን ሬዲይ ይጎረጉራሉ። አገር ቤት ጠዋት ተነስትው አንድ ወንድም ትልቅ የ እግዚባሄር ሰው ነው ፣ እኮ ተነስቶ ዜና ልሰማ ነው አለ። የምን የአገር ቤት … የሰማይ ዜና አይሰማም፤ እግዚአብሄር አይናገርም። ሃምበርገር እየበላህ እዚህ ሃገር ቤትልትሰራ ትፈልጋለህ ።በጣም ያስቃል። በእዉነት ያስቃል። እኔ የፈለጋችሁን በሉ። የፈለገዉን ፖለቲክ ግሩፕ ደግፉ መብታችሁ ነው። ግን እኛ እዚህ ቁጭ ብለን ያዉም ደግሞ ኢሳትን እያዳመጥን ? ሰዎቹ ቅዠት ላይ ናቸው። ቅዠት ዉስጥ ናቸው።ማንም አይናገራቸውም። እዚህ መድክ ውስጥ ግን ይሰማሉ። ቅዠት ዉስጥ ናቸው። ሰዎቹ ቃዥተው ሊያቃዧችሁ ነው። እስቲ ፖለቲካ ሰምቶ በሰላም የሚያደር ማን ነው ? በሰላም የተኛ አለ ? ስትቃዡ ታድራላችሁ ? አንድ ጊዜ ሸለቆ ዉስጥ ወስዷችሁ፣ አንድ ጊዜ ተራራ ላይ እየወሰዳችሁ፣ አንድ ጊዜ ሲያስተኩሳችሁ፣ አንድ ጊዜ እንትን ሲአይደርጋችሁ ….. ሲያደርግ ነው የሚያድረው”

አንድ ፓስተር ነኝ የሚሉ በመድረክ ላይ ከሰበኩት።

“እኔ በዚህ በፖለቲካው ላይ ኢሳት በሚባለው ፕሮግራም ላይ እከታተላለሁና እነርሱ የሚያስተላለፉት መልእክትና እዚህ ያለው መልእክት አንድ ዓይነት ነው። እንዴ አሸባሪ እንዴት አንባልም ታዲያ ቅዱስ አባታችን። በቤተ ክርስቲያን ሽብር አለ። ሰላም የለም መረጋግት የለም ለማሰኘት እኮ ነው። አልፎ ተርፎ እዚህ ቅዱስንዎቷ የሚመጣዉን ህዝብ በኢሳት ፕሮግራም ላይ እናየዋለን። ምን ማለት ነው ይሄ ?”

አንድ ቄስ ነኝ የሚሉ በማህበረ ቁዱስን ላይ በዘመተውና በፓትሪያርኪ በተመራው አንድ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት

እኔ የማይገባኝ፣ ቄሱና ፓስተሩ መጽሐፍ ቅዱሳትን የሚያነቡ አይመስለኝም። ጉድ እኮ ነው ባካችሁ። ማንም ምናምንቴ ቄስና ፓስተር እየሆነ ትክክለኛ ወንጌል መስበክና ማስተማር እኮ እየቀረ ነው ! ይቅርታ አድጉልኝና እነዚህ ሰዎች የእግዚብሄር አገለጋዮች ሳይሆን የሕወሃት ካድሬዎች ናችው !!!!!! አራት ነጥብ።

የእግዚብሄር ቃል በ 1ኛ ዮሐንስ ምእራፍ 4 ቁጥር 20 እና 21 እንዲህ ይላል “ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።”

ክርስቲያን ለወንድሙ ያስባል። ክርስቲያን የታሰሩትንና የታመሙትን ይጠየቃል። ክርስቲያን ለመበለቲቱ ይሟገታል። ክርስቲያን ለፍትህ ይቆማል። ክርስቲያን ያስታርቃል። ነፍሰ ጡር ሴቶች ሲደብደቡ፣ ሰላማዊ ዜጎች አጥንቶቻቸው ሲሰባበሩ፣ ዜጎች ባላጠፉት ወንጀል በግፍ ሲታሰሩ ፣ ዜጎች ላይ መንግስታዊ ዉንብድናና ሽብር ሲፈጸም ዝም ማለት፣ ራስ ወዳድነት ነው። ለወንድማችን አለማሰብ ነው።

አንድ ጥያቄ ልጠይቅ። ለምሳሌ ጋዜጠኛ ርዮት አለሙን እና እጮኛዋን ስለሺ ሐጎስ እንውሰድ። ርዮት በጋዜጦች ላይ ሐሳቧን ስለገለጸች ሽብርተኛ ተብላ በወህኒ ትገኛለች። የጡት ሕመምተኛም ሆና ሕክምና እንዳታገኝ ተደርጋለች። እጮጫዋም የጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነበር። ሰላማዊ በሆነ ሰልፍ ላይ በመገኘቱ መሬት ላይ አስተኝተው፣ እንደ አህያ ነው የደበደቡት። ከዚህም የተነሳ አጥንቶቹ ሕግ እናስከበራለን በሚሉ ወንበዴዎች ተሰባብሯል።

እስቲ ርዮት አለሙም ሆነ ስለሺ ሐጎስ የስጋ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ቢሆኑ ኖሮ ፣ ፖለቲካ አይሰማማኝም ብለን ዝም እንላለን? ቄሱና ፓስተሩ እነ ርዪት ልጆቻቸው ቢሆኑ ኑሮ አሁን የሰበኩት እና የተናገሩትን ይተነፍሱት ነበር ? አያደርጉትም ነበር።

እንግዲህ ወንጌልና ክርስትና ማለት፣ እኛ ላይ ሲደርስ፣ ወይም የስጋ ልጆቻችን ወይንም ወንድሞቻችን ላይ ሲደርስ ብቻ መነሳትና መቆርቆር ሳይሆን፣ የእግዚብሄር ፍጡር የሆኑትን ሁሉ እንደ ወንድምና እህት አይቶ፣ በማንም ሰው ላይ ግፍ ሲፈጸም እኛንም ያመናል ማለት ሲቻል ነው።

“ጌታ፣ ጌታ” ማለት ጥሩ ነው። የእግዚአብሄር ስም መጥራት ጥሩ ነው። ሆኖም ጌታን ስንጠራው “ወንድምህስ የታለ ?” ብሎ ይጠይቀናል። በመንደራቸውና ከቅያቸው እየተፈናቀሉ ያሉት የት አለ ? በየአገሪቷው ሽብርተኞች ተብለው የታሰሩት የታሉ ? የአገዛዙ ሽፍታ ታጣቂዎች የሚደበደቡ፣ የሚንገላቱ ወገኖች የታሉ ? የደሞዝ ጭማሪ የለም፤ የታረሰውን የተመረተው ወደ አረብ አገሮች እየተላከ፣ ከዚይም የተነሳ ጥቂቶች ሚሊየነር ሲሆኑ፣ ምግብ መግዛት አቅቷቸው ፣ አንድ ኩንታል ጤፍ 2400 ዶላር ሆኖባቸው፣ የሆቴል ቤት ፍርፋሪ በጉርሻ እየገዙ በቀን አንዴ ብቻ የሚመገቡት የት ነው ያለት ? የዚህ ዘር ነህ፣ ይሄን ቋንቋ ትናገራለህ ተብሎ የዘር ማጥራት ወንጀል የሚፈጸመብት ኢትዮጵያዊ የት አለ ? ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የት አሉ ? የነርሱ ነገር የማይሰማን ከሆነ ደፍሬ እናገራለሁ ክርስቲያን የሆንነው በስም ብቻ ነው።

ወንዴሜን ካልወደድኩ፣ ለወንድሜ ካልተቆረቆርኩና ካልተሟገትኩ እንዴት እግዚአብሄርን እወዳለሁ ለማለት እችላለሁ ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.