ቢቢኤን ሰበር ዜና: ….. የቄሮና የፌዴራል ፖሊስ ፍጥጫ ቀጥሏል

በአገሪቱ ዉስጥ የተጠራዉን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ ቄሮና ፌዴራል ፖሊስ ተፋጠዋል።የስራ ማቆም አድማው ቀጥሎ አዲስ አበባን አካሏል።

አየር ጤና፣ካራ፣ወለቴ፣ኖክ፣ጀሞና ፉሪ የንግድና የትራንስፖርት ግልጋሎት ተቋርጦ መዋሉ ታዉቋል።መንገዶች ተዘግተው ነበር።የቄሮን ትእዛዝ ተላልፈው የተከፈቱ የንግድ ድርጅታቸውን የከፈቱ ወይም መኪናን ያንቀሳቀሱ እርምጃ ተወስዶባቸውል ሲሉ ያካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢኤን ገልጸዋል።

ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅደመ ሁናቴ ይፈቱ።ህዝብን እየጨረሰ ያለው የመከላከያ ሰራዊት ወደ ካምፕ፡ይግባ የህዝባዊ እምቢተኝነቱ ተሳታፊዎች ጥያቄ ነው።

ከፍተኛ ተኩስ ተሰምቷል።ጉዳት ሰለምኖሩ የታወቀ ነገር የለም።ፍጥጫው እንደቀጠለ ነው።ቢቢኤን ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰአታት በኋል ይለቃል።

 

ብራቮ ሻሼ

ዛሬ ማለዳውን የጀመረው ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በሻሸመኔ በዚህ መልክ ተጠናክሮ ቀጥሎአል ።

የንግድ ቤቶች ፤ መንግስታዊ ቢሮዎች ፤ ባንክና ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው ።

የዛሬው የተቃውሞ መርሐግብር በተያዘለት ሰአት ተጠናቆአል ሁለተኛው ዙር ቀን 9 ሰአት ላይ የሚቀጥል ይሆናል

ለተከታታይ ቀናት በዚህ መልኩ የሚቀጥል ሲሆን አገሪቱ ከወያኔ የእጅ አዙርና ቀጥተኛ አገዛዝ ነፃ እስክትወጣ ይቀጥላል !!
Netsanete Kebru

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.