አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ክስ እንዲቋረጥ ተወሰነ

የፌዴራ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የቀድሞ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር የየሆኑትን አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የሰባት ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ መወሰኑ ታወቀ፡፡

አቶ በቀለ መጀመሪያ የተከሰሱት በፀረ ሽብር ሕጉ ቢሆንም በኋላ ግን ክሳቸው ወደመደበኛ ክስ እንዲቀየር ተደርጎ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ክሳቸውን ሲከታተሉ አንደነበር ይታወልቃል፡፡

ይሁንና ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር የተከሰሱ አራት ግለሰቦች ፍርድ ቤትን በመድፈር ሁለት ጊዝ በተከታታይ የስድስት ወራት የእስራት ፍርድ ስለተፈረደባቸው እንዴት ሊፈቱ እንደሚችሉ አልታወቀም፡፡ ፍርደኞችን ይቅር የማለት ሥልጣን የፕሬዚዳንቱ ስለሆነ ጉዳያቸው ወደ ፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ሊመራ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.