የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳይ ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የብአዴን አመራሮች ከስልጣን ተነሱ ለሚለው ዜና “የህልም ዜና” ሲሉ አስተባብለዋል

የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳይ ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በብአዴን በጉዳዩ ላይ እንደሚከተለው አስተአይየት ሰጥተዋል።

የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን
የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን

የካቲት 10 ቀን 2010 ዓ.ም.
==================
“ዶሮ ብታልም ጥሬዋን”
===================
ብአዴን ስብሰባ ባካሄደ ቁጥር ለድርጅቱ እና 
ለአማራ ህዝብ መሪ መሾም መሻር የሚመኙ ህልመኞች እነሆ የሰሞኑን ስብሰባ አስመልክቶ ምንም ፍንጭ ሲያጡ እንደተለመደው የህልም ዜና ሰብረውልናል።

ብአዴን የጀመረውን ውይይት እጅግ በሰከነ እና መደማመጥ በሰፈነበት ሁኔታ እያካሄደ ሲሆን ውይይቱን እንዳጠናቀቅንም ለህዝባችን መግለጫ የምንሰጥ ሲሆን “ውስጥ አዋቂ ነን” በማለት ምኞታቸውን በዜና መልክ ፤ ያውም በሰበር ዜና ለሚያሰሙን ህልመኞች መሪውን የሚመርጠው ድርጅቱ እና የአማራ ህዝብ ስለሆነ “መመኘት ይቻላል ፤ እዉነት ግን ወዲህ አለች ” እንላለን።
ህዝባችንም ይህንን አይነት ዘመቻ የተለመደ ስለሆነ የድርጅቱን ውሳኔዎች ውይይታችን በሚቀጥሉት ቅርብ ቀናት እስኪጠናቀቅ እና ትክክለኛው መረጃ በድርጅቱ በኩል እስኪሰጥ ድረስ ለሚለቀቁ እንዲህ ዓይነት የህልም ዜናዎች ጆሮ እንዳይሰጥ እንጠቁማለን።
“ዶሮ ብታልም ጥሬዋን”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.