ንግስት ይርጋ ተፈራ! ተፈታች፥ – ዮናታን ተስፋዬ እስካሁን አልተፈታም (ጌታቸው ሺፈራው)

Truneh Yirga ንግስታችን ተፈታች፥ She is out !!!
ንግስት ይርጋ ተፈራ
===========
ጃሎ በል ጎንደር ፎክር አማራ
ንግስት መታለች የሴቶች አውራ፥

መንገድ ይጠረግ ፎናሱም ይብራ
ከፋሲል ግንቡ ገነት ተራራ

ይምጣ አርማጭሆ በለሳን ጥራ
ይነጠፍላት ነጭ ቀይ ሃምራ
ጋይንት ደብረታቦር፥ ጭልጋ ወገራ
ጎጃም፣ ወሎ ሸዋ መላው አማራ፥

ጀግና ይወላዳል አገሬ ጎንደር
ፍኖተሰላም ማርቆስ ባህርዳር፣
የኮሎኔል ደመቀ እና የንግስት አገር፥

ይደገስላት ዳሱም ይሰራ
ንግስት መታለች የእኛ ሙሽራ
እልል በይ ጎንደር ደሴና ወልዲያ
የድል ቀን ደርሷል ደስ ይበልሽ ኢትዮጵያ

የነጻነት ቀን ውሎ እንዳያድር
አማራ ፋኖ ግፋ፥ ኦሮሞ ቄሮ ወጥር
#Ethiopia Free all Political Prisoners!

 

ዮናታን ተስፋዬ ያለ ቅድመ ሁኔታ ይፈታ!

~መጀመርያ “አጥፍቻለሁ፣ ተፀፅቻለሁ!” ብለህ ፈርም ተባለ። አላጠፋምና አልፈረመም!

~ ለሁለተኛ ጊዜ “በ5 አመት ውስጥ አሁን የፈፀምኩትን ወንጀል ብፈፅም የተፈረደብኝ ተግባራዊ ይሁንብኝ” ብለህ ፈርም ተብሏል። እሱ ግን “ወንጀል አልሰራሁም፣ አልፈርምም” ብሏል!

~ለ3ኛ ጊዜ ምን ብለው እንደሚጠይቁት እየተጠበቁ ነው! ዮናታን ደግሞ ምን እንደሚያደርግ ያውቃል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.