መለስ ዜናዊን የኢትዮጵያ ህዝብ የጠላዉ ትግሬ ስለሆነ አይደለም:: የመርዝ ፖለቲካን ስለሚያራምድ እንጅ

ሸንቁጥ አየለ
———————
ወያኔ/ኢህዴግ የድሜ ዘመኑን ለማራዘም አንዴ ከደቡብ ሾምኩ: አንዴ ከኦሮሞ ሾምኩ ስላለ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ሰፈነ ማለት አይደለም::ለማ : ገዱ: አቢይ : ደመቀ እንቶኔ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይደረጉልን እያሉ የሚንጫጩ የዲሞክራሲ ጠላቶች የኢትዮጵያን ህዝብ በጣም የሚንቁ ናቸዉ:: ለኢትዮጵያ ህዝብም እዉነተኛ ዲሞክራሲ እንደሚገባዉ የማያዉቁ ደንቆሮዎች ናቸዉ::

የኢትዮጵያ ህዝብ መለስ ዜናዊን የጠላዉ ትግሬ ስለሆነ አይደለም::በህዉሃት/ኢህዴድ የፖለቲካ ርዕዮተ አለም የተቃኘ የጥላቻ እና ኢትዮጵያን የሚያጠፋ መርዛማ አካሄድን በመከተል ብሄሮችን የሚከፋፍል ስልትን ተከትሎ ህዝባችንን ስላደቀቀዉ እና ኢትዮጵያዊነትን ስላጠፋዉ ነዉ::

ወያኔ በትግሬ የበላይነት የሚመራዉን ህዉሃት/ኢህአዴግ በደቡብ ተወላጅ በሀይለማሪያም አስመራሁት ስላለ ጠብ ያለ ለዉጥ የለም::አንዳንቹ የሀይለማሪያምን የፕሮቴስታንት እምነት እየቆጠሩ ጌታ ያነገሰልን ነዉ እያሉ ለሀይማኖት ወገናቸዉ በማገዝ ብዙ ሲጮሁ እንደነበረ እናዉቃለን:: አሜሪካ የመሸጉ የያዘመን ሽማግሌ ፖለቲከኞች ብሎም ተስፋ ሲቆርጡ የሀይማኖት ካምፖችን የተቀላቀሉ አስመሳዮችም ሀይለማሪያምን ሲያወድሱ እንደነበረ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝግቦ ይዟል:: ወያኔ/ኢህአህዴግን ለኢትዮጵያ ህዝብ እግዚአብሄር የላከዉ የሚሉ የቁጩ ነበያትም በዶላር ተገዝተዉ አንድ ሰሞን ለፍልፈዋል:: አሁንም ድምጻቸዉን በጣም ቀንሰዉ የሚያንቋርሩ አልጠፉም::

አሁን ደግሞ ከኦሮሞ ወገን የሆነ ሰዉ ወያኔ/ኢህአዴግ ከሾመልን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ትመጣለች የሚሉ የወያኔ/ኢህአዴግ ስዉር አሽቃባጮች ተነስተዋል::ኢትዮጵያን በመንከስ እና ህዝቡን በመከፋፈል የሚታወቁት የኦነግ ጋሻ ጃግሬዎችም ስለ እዉነተኛ ዲሞክራሲ ከመቆርቆር ይልቅ በህዉሃት/ኢህአዴግ በኩል የሚያገኙትን ንግሳ እና ጥቅም እየቆጠሩ ከኛ ወገን ካልነገሰልን ማለት አብዝተዋል:: አልፎ አልፎም ቢሆን ከአማራ ወገን ነን የሚሉ እና ገዱ ይሾምልን : ደመቀ ጠቅላይ ሚኒስቴር ካልሆነልን የሚሉም ይደመጣሉ::

እንዲህ አይነቶች በሙሉ ቆዳቸዉን እየቀያየሩ እና ተቃዋሚ እየመሰሉ ወያኔ/ኢህአዴግ እያመሳሰለ የሚልካቸዉ የዲሞክራሲ ጠላቶች መሆናቸዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ጥንቅቅ አድርጎ ያዉቃል:: የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ይፈልጋል?

የኢትዮጵያ ህዝብ የጎሳ ተሿሚዎችን: ወይም የግለሰቦችን ያለ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሹመት አይደለም የሚፈልገዉ:: ከዚህ ብሄር ከዚያ ብሄር የሚል ሹመት በሙሉ አደገኛ እና ጸረ ዲሞክራሲያዊ ነዉ:: እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተደርጎ አንደ ፓርቲ/ግለሰብ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ከተመረጠ እና ከተሾመ ያ ሰዉ ሶስት አባላት ካሉት ነገድም ቢሆን ወይም ሰላሳ ሚሊዮን አባላት ካሉት ነገድም ቢሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መሪ ተብሎ ይሰየማል::

ዋናዉ መከናወን የሚገባዉ ሂደት እዉነተኛ ምርጫ በፍትሃዊ ተቋማት እና በህግ የበላይነት በሚመራ ስርዓት መሆን መቻል አለበት::ከዚህ ዝቅ ወይም ከፍ የሚል ዲሞክራሲ የለም::ከዚህ ዉጭ ጎሳዬን አንግሱልኝ ብሎ እዬዬ ያዉ ወያኔአዊ አስተሳሰብ ነዉና እስከመቸረሻዉ እንዋጋዋለን::ለአንዲት ዲሞክራሲያዊት የበለጸገች ኢትዮጵያ መገንባት የዲሞክራሲያዊ ሂደቱ ወሳኝ ነዉ::

መጀመሪያ ግን የወያኔ/ኢህአዴግ መርዝ አስተሳሰብ ከኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ይነቀላል::የምርጫ ጉዳይ አይደለም::ከወያኔ ጋር ዉስጥ ዉስጡን የምትደራደር እና ተቃዋሚ ነኝ የምትል ሁሉ ብኋላ ታዝናለህ::አብረህ ተለቅመህ መመታትህ አይቀርም እና ፈቀቅ ብለህ ተቀመጥ::ጎሳ እየቆጠርክ እና የጎሳ ጥቅም ለማስከበር የምትሞዳሞድ ሁሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ገና በደንብ አላወቅከዉም እና ያዉ ቀኑ ሲደርስ ሁሉንም ታዬዋለህ::

ከወያኔ/ኢህአዴግ ጋር አብሮ ኢትዮጵያን ያጠፋ ሁሉ የኢትዮጵያ ጠላት ነዉና የኢትዮጵያ ተስፋም ሆነ ታዳጊ ሊሆን አይችልም::ጎሳህን እየቆጠርክ የዲሞክራሲ አስተሳሰብን አታደብዝዝ:: ጎሳህን እየቆጠርክ ከጎሳዬ እንቶኔ ይሾምልኝ የምትል ሁሉ ተስፋህን ቁረጥ::የትግል ፍንትዉታዉ ግቡን ሳይመታ ፈጽሞ አይቆምም::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.