‹‹የወያኔ መንግሥት የፖለቲካ በትረ-ሥልጣን ነገረፈጆች!!! ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ዶክተር እሸቱ ጮሌ ክበብ››

‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ዶክተር እሸቱ ጮሌ ክበብ››

ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት TPLF WARLORDS STATE የወያኔ ፋሽስታዊ ‹የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ! ይነሳ!!! “

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣ ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች፡-

የህወሓት/ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ አውጆል፡፡ ወያኔ የተነቃነቀ በትረ ሥልጣኑን ለማስጠበቅ በአዋጅ ህዝብ ለመግደል ቆርጦ ተነስቶል፡፡ የኢትዮጵያ ‹‹ህገ-መንግሥት›› ተጥሶል፣ የክልል መንግሥቶች መብትና ሥልጣን ተሸሮል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች  መንግሥት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በኮማንድ ፖስት  ቁጥጥር ሥር ወድቆል፡፡ የወያኔ መንግሥት የፖለቲካ ቤተ ርስት መናጆዎች!!! የወያኔ ፖለቲካ አማካሪዎች ሲሆኑ፣ ሁሌ እንደመስቀል ወፍ ብቅ የሚሉ የወያኔ በትረ-ሥልጣን ምሶሶ በሚንገዳገድበት ወቅት ነው፡፡ የፖለቲካ ትንተና ላይ የተመሠረተ ፕሮፓጋንዳ፣ ወያኔ መንግሥት ከወደቀ የዘር ፍጅት ይከተላል!፣ አገር ይገነጣጠላል!፣ ኢንተር ሃሞይ ይከሰታል!! መሬት ይንቀጠቀጣል!፣  ህገ መንግስቱ ይቀልጣል!!!. እያሉ የሚተውኑ እንደ መስቀል ወፍ የሚታዩ ተዋናይ ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ ሰለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ፕራይቨታይዜሽን ዘረፋ ተናግረው አያውቁም፣ ስለወያኔ ኢፈርት፣ ሜቴክ፣ ወጋጋን ባንክ፣ ለገደንቢና ኢዛና ወርቅ፣ ስለ ሙስናና ኮንትሮባንድ ንግድ፣ የከተማና ገጠር መሬት ቅርምት ወዘተ ተናግረው አያውቁም፡፡  ለህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ለኢህአዴግ የምርጫ ፔስሜከር ወይም የፖለቲካ ቤተ ሥልጣን ወሳኚ  ከመሆን የዘለለ ምንም አልፈየዱም፡፡ በኢትዩጵያ ፖለቲካ የምርጫ ፔስሜከር ወይም  መናጆ ነት ይብቃ!!! የወያኔ መንግሥት የፖለቲካ ቤተ ሥልጣን ነገረፈጆች (Pace Makers) ወይም የወያኔ ፖለቲካ ሩጫ ፍጥነት ወሳኚ መሃል ሌተናል ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት፣ ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ልደቱ አያሌውና አቶ አማረ አረጋዊ በሪፖርተር ጋዜጣቸው ቃለመጥይቅ በማድረግ የወያኔ ስርዓት ጋሻ ጃግሬነትና፣ የነፍስ አባትነት፣ጥብቅናቸው ይታወቃሉ፡፡ አቶ አማረ አረጋዊ በሪፖርተር ጋዜጣቸው ይሄን ፅሁፍና የኢት-ኢኮኖሚ አትሞችን በጋዜጣዎ  ቢያወጡት በእውነት  ‹‹የፕሬስ ነፃነትን ከስቅላት ያድኑ!›› ያሉትን በተግባር ባዋሉ ነበር፡፡ የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት ወታደራዊ ጁንታ በመፈጸም ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በማወጅ በኮማንድ ፖስት የክልሎች መንግሥትን ስልጣንን በመንጠቅ አዋጅ ደነገገ፡፡ ከአዋጅ ውስጥ፡-

  • ይፋዊ ሆነ የድብቅ ቅስቀሳ ማድረግ፣ ፅሁፉ ማዘጋጀትና አትሞ ማዘጋጀት ትዕይንት ማሳየት፣ በምልክት መግለፅና ወይም ምልክትን በማንናውም ሌላ መንገድ ለህዝብ ይፋ ማድረግን ይከለክላል፡፡
  • ማንኞውም የመገኛኛ ዘዴ እንዲዘጋ ወይም ደግሞ እንዲቆረጥ ማድረግ፣
  • የህዝብና የዜጎችን ሰላምና ጸጥታ ለመጠበቅ ሲባል የአደባባይ ሠልፍና ሰልፍ ማድረግን መደራጀት፣ በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስን ይከለክላል፡፡
  • በህገመንግሥቱና በህገመንግሥታዊ ስርዓቱ ላይ የሚቃጡ ወንጀሎችን የጠነሰሰ፣ የመራ፣ ያስተባበረ፣ የጣሰ ወይም በማንኛውም መንገድ ወንጀል ድርጊት የተሳተፈ ወይም ተሳትፎል ተብሎ የሚጠረጠር ማንኛውም ሰውን፣ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር ያደርጋል ተገቢውን ማጣራት በማድረግ በመደበኛው ህግ ተጠያቂ ያደርጋል፣
  • ወንጀል የተፈጸመባቸውን ሊፈፀምባቸው የሚችሉ እቃወዎችን ለመያዝ ሲባል ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ ማንኛውንም ቤት፣ ቦታ፣ መጎጎዣ ለመበርበር እንዲሁም ማንኛውንም ሰው ማስቆም ፣ ማንነቱን መጠየቅ እና መፈተሸ ይችላል፤
  • በብርበራ ወይም በፍተሸ የተያዙ እቃዎችን በማስረጃነት ለፍርድ ቤት መቅረባቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ተጣርቷ ለባለመብቱ ይመለሳል፣ የስዓት እላፊ ተፈሚ የሚሆንበትን ሁኔታ ይወስናል፡፡ የመሳሰሉት አንቀፆች ይገኛሉ፡፡

ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ እንዳሉት ‹‹ከሁለት ዓመት በኃላ በምርጫ የሚፈልገውን መምረጥ እንደሚችል ይተማመናል፡፡ ስለዚህ ቤት ማቃጠል፣ ሰው መግደልና ኢንዱስትሪ ማፍረስ ይቆማል ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህ ሂደት በራሱ ወንጀልንና ትክክለኛ የፖለቲካ ጥያቄን ይለያል ብዬ አስባለሁ፡፡ በወንጀል መንገድ እሄዳለሁ በሚሉ ላይ የፀጥታ ኃይሉ ያለምንም ማቅማማት ዕርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ ላለፉት 27 ዓመታት የቆየ ህዝብ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት መታገስ አይችልም ብዬ አላስብም፡፡››  በማለት ለሪፖርተር ጋዜጣ የካቲት 4 ቀን 2010ዓ/ም ሠራዊቱን እንዲገድል ጥሪ አስተላልፈዋል፣ ለሠራዊቱ የሰው ነፍስ አትግደል፣ አስለቃሽ ጢስ ተጠቀም!፣ ወደ ሰማይ ተኩስ!፣ ካልሆነ ከእግሩ በታች ተኩስ፣ ብለው አልመከሩም ለእሳቸው ከሰው ነፍስ ንብረት በለጠባቸው!(የራያ ቢራ ፋብሪካቸው!) ነው የበለጠባቸው፡፡ በአሜሪካ በፈረንሳይ በእንግዚዝ ወጣቶች አመፅ ብዙ ሽህ መኪኖች በአንድ ሌት ያቃጥላሉ፣ ብዙ ሱቆችና ንብረቶች ያጋያሉ! ግን አንድ ወጣት አልሞተም፡፡ ጄነራል  በሸበጥ ጫማና በቁምጣ እንዳልገቡ፣ ቂጣ ፍሪዳው ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ ወጣቶች ላይ ሞት ፈረዱ፡፡ ጻድቃን ቦሌ የሠሩት መኖሪያ ፎቅ እንዳይቃጠል ፈርተዋል ሠላም! ሠላም ይላሉ፡፡ የሽግግር መንግሥት ይቆቆም አላልኩም፣ በህዝብ የተመረጠ መንግሥት እያለ የሽግግር መንግሥት ማቆቆም ህገ መንግሥቱን መናድ ነው አሉ በአሽሙር፡፡ ከቀናት በኃላ የካቲት 9 ቀን 2010ዓ/ም ወያኔ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ‹‹የሽግግር መንግሥት አይቆቆምም›› ሲራጅ ፌጌሳ አሉ፡፡ ምክራቸውን ሰምቶ የፍየል ወጠጤ አወጀብን፡፡ አቶ ልደቱም መከላከያ ሠራተዊቱ የሚለውን ማክበር እንዳለብን በሠራዊቱ ቀን ሲወሻክቱ ተሰማ!!! በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ ቦዶ የሠላም ዲስኩር አሰሙ፣ ወያኔን የሚቃወሙ በማስመሰል ትያትራቸውን ተወኑ!!! እነዚህ የወያኔ የነፍስ አባቶች፣ እንደ አሸን ወያኔ ለሞት ሲያጣጥር ንዛዜውን ለመቀበል የሚመጡ ቅጥረኞች ህዝቡን ሁሌ የሚያታልሉ ይመስላቸዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ የራያ ቢራ ፋብሪካ ሲያቆቁሙ ከንግድ ባንክ 970 ሚሊዩን ብር ብድር መውሰዳቸውና ራያ ቢራን ለቢጂአይ ዓየር በዓየር መሸጣቸው ይታወቃል፡፡ አሁን ደሞ ለቢጂአይ ኢትዮጵያ አዋሽ ባንክ 750 ሚሊዮን ብር ብድር እንዲሰጠው በማመቻቸት ቢጂአይ በራያ ቢራ ውስጥ ካለው የ42 በመቶ ድርሻው በተጨማሪ፣ ቀሪውን አክሲዬኖች ለመግዛት ከ2.5 ቢሊዮን ብር ለባለአክሲዮኖቹ ለመክፈል የዓየር በዓየር ንግድ ጻድቃን የባንኩን ብድር አመቻችተዋል፡፡ ልደቱ አያሌውም ጽላት የተባለ በላሊበላ ሆቴል በመሥራት ላይ ይገኛሉ፣ ድህነታቸውን ቀርፈዋል፡፡ ሌተናል ጄኔራል ስዬ አብርሃ ከአሜሪካ መጥተው በመቀሌ ከተማ ከ40 ዓመታት በፊት በቀይ ሽብር ለተገደለው ወንድማቸው መታወሻ ትምህርት ቤት ከፍተው ማስመረቃቸው ይታወቃል፡፡ በትግራይ የቀይ ሽብር ሰማዕታት በሙሉ መታሰቢያ ቢሆን በተሸለ ነበር!!! የወያኔ አጋዚ ጦር የገደላቸው ለጋ ወጣት ሠመዓታት ደም በከንቱ ፈሶ እንደማይቀር የወላጆች እንባ እንደሚታበስ ዘንግተዋል፡፡ በወያኔ መንግሥት  ለተገደሉ  ሠማዕታት መታሠቢያ ስንት መታሠቢያ ይቆም ይሆን!! ወያኔ ከደርግ ሥርዓት የተማረው ግድያ ነው፣ የቀይ ሽብር ወንጀለኞች በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር የተደበቁ ሁሉ ለፍርድ ቀርበዋል፡፡ የወያኔ ነጭ ሽብር ወንጀለኞች እጣ ፈንታቸው ይሄው ነው፡፡ በዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን እያንዳንዶ የግድያ ማስረጃ ተሰድራ ቀን ትጠብቃለች፡፡ በወያኔ  ሥርዓት የተገደሉ የጅምላ ግድያ ድብቅ ቦታዎች በትግራይ፣ በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሞ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ክልል ወዘተ ተቆፍሮ የሚወጣበት ጊዜ ደርሶል!!! ሌተናል ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት፣ ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ልደቱ አያሌውና፣ አቶ አማረ አረጋዊ ሁሌም የወያኔ ነፍስ አባት በመሆን በቀውጢ ጊዜ ወያኔን የሚታደጉ ‹‹ህገ-መንግሥቱን የናደውን ወያኔ ሥራ እያዩ ‹‹ህገ-መንግሥት ይከበር!!!›› በሙስናና በኮንትሮባንድ ሥራ ዋነኛ ተካፋይና የሥርዓቱ ተጠቃሚ በመሆናቸው የህዝባዊውን እንቢተኛነትና ተጋድሎ በመኮነን የሰው ነፍስ ከሚጥፉ አጋዚ ጦር ሠራዊት ጥይት በላይ በምላሳቸው የሚናደፉና በብዕራቸው የሚወጉ ናቸው፡፡ ‹‹ምላስ አጥንት የላትም፣ አጥንት ግን ትሰብራለች!!!› የህወሓት መንግሥት ከወደቀ ኢትዮጵያ ትበታተናለች›› ‹‹ኢንተርሃሞይ! የዘር ፍጅት ይከሠታል!!›› ይሉናል፡፡ ‹‹የእርስ በእርስ ጦርነትና የሃይማኖት ጦርነት ይኖራል›ይሉናል፡፡ ህዝቡን አርፋችሁ ተገዙ፣ መሬታችሁን ስጡ፣ ሃብታችሁን ተዘረፉ፣ይላሉ፡፡

አንድ የትግራይ ተወላጅ ምሁር በአንድ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር  መጠረት ወያኔ ይሄን ለምን እንደማይቀበለው እንገንዘብ፤የህወሓት/ማሌሊት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ሌላ አማራጭ መንገድ የማያውቁ በስታሊናዊ ጨካኝ አስተሳሰብ ተኰትኩተውና እንደ ዓሳራ ግመል ፊታቸውን ተሸብበው ያደጉ ናቸው:: መለስ ዜናዊም ብልጥ ነው:: ሆን ብሎ የህወሓት/ማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም በጭንቅላታቸው ውስጥ የገጠመላቸው ስለሆኑ ከዚያ አጥር ወጥተው ሌላ ሰፋ ያለ ዓለምና ሳይንስ የሚያዩበት መነፅር የላቸውም:: ቢተኩሱም! ቢነግሱም! ቢማሩም ያው ናቸው ምንም አይለወጡም:: ቀደም ብሎ በአእምሮኣቸው ከተገጠመላቸው የሶፍት ዌር ፕሮግራም ውጭ ሌላ የሚያውቁትና የሚናገሩት ሰላማዊ ቋንቋ የላቸውም:: ሁሉ ጊዜአካኪ ዘራፍ!! በለው ደምስሰው!! – ያዘው ልቀቀውየሚሉትን ቃላቶች ብቻ ናቸው በአእምሮኣቸው የሚታዩባቸው:: ሕግ አይገዛቸው! ባህል አይገዛቸው! ታሪክ አይገዛቸው! ሀይማኖት አይገዛቸው! ጊዜ አይለውጣቸው! ዕድሜያቸው ልክ አንድ ዓይነት መዝሙር እየዘመሩ ጭንቅላታቸውን በማሌሊታዊ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ እንደተቆለፈ ያልፋሉ:: በመሆኑም አሁን እየታየ ያለው ትልቁ አሳሳቢ ጉዳይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው በማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም መደንዘዛቸው ብቻ አይደለም ችግሩ:: ነገር ግን ከጫካ ይዘውት የመጡት መድሃኒት አልባ በሽታ ወደ ሌሎች ክልሎችም በፈጣን ሁኔታ እየተዛመተ መምጣቱ ነው:: ስለዚህቤቱን ሳይቃጠል በቅጠልእንደተባለው እኛም በተራችን ሳንታመም የመከላል ዘዴ መፍጠር ይኖርብናል፡፡ እነዚህ ዓሳራ ግመሎች ለህዝብ አሳቢ በመምሰልና ወያኔን የተቃወሙ በማስመሰል፣ የህዝብ አስተሳሰብን ለመበረዝና ለመከለስ ከወያኔ ጎዳ ተመካክረው አደባባይ አዲስ አጀንዳ በማንገብ የሚወጡ፣ የወያኔ የፖለቲካ መናጆዎች በመሆን የህወሓት መንግሥት እንዳይወድቅ የሚያደርጉ የዓሳራ ግመሎች ናቸው፡፡ እነሱ በፈለጉ ጊዜ ሁሉ መገናኛ ብዙሃኖች ይበረገዱላቸዋል፣ ጋዜጦች፣ቴሌቪዝኖች፣ ሮዲዮኖች፣ መፅሄቶች ፣ድረ-ገፆች ወዘተ ሁሉ ለዓሳራ ግመሎቹ፣ ሌተናል ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት፣ ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ አቶ ስዬ አብርሃና፣ አቶ ልደቱ አያሌው፣መሰሎች ስብከት ‹‹ህገ-መንግሥት ይከበር!!!›› ሰላም፣ ሰላም፣ ሰላም›‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› አስፈላጊነት ዲስኩር ‹‹መከላከያ ሠራዊታችን ህዝባዊ፣ የብሄር ብሄረሰብ ተዋፅኦ ያለው!!! መልካም አስተዳደርና ሙስና ችግር ወዘተ የአስመሳይ ምሁራዊ ትወና በተደጋጋሚ ሲሰሩብን አስተውለናል፡፡ ለእነሱ ዴሞክራሲ ይህ ነው ህዝቡን አፍነው እነሱ በየመድረኩ ያናፋሉ፣ እነዚህ ግለሰቦች አንድም ቀን ስለአገሪቱ ኢኮኖሚ ትንተና ሲሰጡ ተሰምተው አያውቁም፣ የፖለቲካ ዲስኩር ሌላ፣ የኢኮኖሚ ጥናታዊ ትንተና ሌላ፡፡ 30 ሚሊዮን ወጣቶች ሥራ ፈት በሆኑባት ሃገር ወጣቶችን ችግራችሁ ምንድነው ብሎ መጠየቅ የምሁራን ሥራ ነበር!!! ህዝቡ ያመፀው በወያኔ መሬቱን በመነጠቁ፣ በወያኔ ሃብቱን በመዘረፉ፣ በወያኔ መልካም አስተዳደር እጦት፣ በወያኔ የሙስናና ኮንትሮባንድ ንግዳችሁ ይቁም ነው የሚላችሁ፡፡ ሰው ይውደድህ፣ ድንጋይ ይጫንህ!!!›› አበው  የሚሉት ለዚህ ነው፣ የተጠላችሁ ሰዎች ናችሁ፡፡‹የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ያፈራቸው ወጣቶች የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ እውቀትና ክህሎት አስር እጥፍ እንደሚበልጡንና እድሉ ቢሰታቸው ሃገራችን ውስጥ ያለውን ችግር በሰለጠነ መንገድ በውይይት መፍታት እንደሚችሉ አትጠራጠሩ፡፡ ለዚህ ነው የወያኔ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››በሃገሪቱ የተከሠተውን  የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ ችግሮች የሃገር ውድቀት ያፋጥናልን፣ በማለት በተለይ ሦስቱን መሰረታዊ የሃገራችን የኢኮኖሚ ምሦሶዎችን እንደሚንድ ወጣት የምጣኔ ኃብት ጠበብት የሚያስገነዝቡት፡-

 

{1} የባህር ማዶ ልማት ትብብር (ODA፡ Official Development Assistance) ከ1991 እኤአ እስከ 2012 እኤአ ለህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት አርባ ቢሊዩን ዶላር የልማት እርዳታ ሰጥተዋል፡፡ በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በአማካኝ በአመት ሁለት ቢሊዩን ዶላር እርዳታ ሃገሪቱ እንዳገኘች ያስረዳል፡፡ በይፋ የተለያዩ ለጋሽ ሃገራት የሰጡትን ገንዘብ ብዛትን ለማስላት ያህል በትንሹ ስምንት ታላቁን የህዳሴ ግድብ ኤሌትሪክ ማመንጫን የሚችል ሜጋ ፕሮጀክቶችን በእርዳታ ገንዘቡ መስራት የሚያስችል ነበር፡፡ አልያም የቻይና መንግስት በ200 ሚሊዩን ዶለር ያሰራውን የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ህንፃን ዓይነት ሁለት መቶ ህንፃዎች ሊገነባ የሚችል ገንዘብ ነበር፡፡ የባህር ማዶ ልማት ትብብር እርዳታ ከ2008 እስከ 2015እኤአ ያለውን ብቻ ብናይ ከ3 እስከ4 ቢሊዩን ዶላር ሃገራችን የልማት እርዳታ አግጥታለች፡፡ በኦዲኤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ አድራጊ መንግስቶችና ተቆማት አሜሪካ መንግሥት፣ የእንግሊዝ መንግሥት፣ የአውሮፓ ህብረት ኢንስቲቲዉሽኖች፣ ኢንተርናሽናል ዲቨሎፕመንት አሲስታንስና ግሎባል ፈንድ ናቸው፡፡  የህወሓት/ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›እንዲያነሳ ጫና እንዲደረግበት የዲያስፖራው የትግል እንቅስቃሴ በነዚህ አገሮችና ድርጅቶች ላይ ማነጣጠር ይኖርበታል፡፡ ወያኔ የተነቃነቀ በትረ ሥልጣኑን ዴሞክራሲን በማፈን፣ ስብዓዊ መብቶችን በማፈን፣ ህገ-መንግስቱን በመጣስ የኢትዮጵያ ህዝብን አፍኖ በመግዛት ላይ መሆኑን በሠላማዊ ሠልፍ መግለፅ አስፈላጊ ነው፡፡

Net Total Official Development Assistance (NTODA)

Year 2008 2009 2010 2011 2012 2013 2014 2015 2016
NTODA 3316 3824 3455 3493 3224 3886 3585 3234
United States 811 726 803 659 693 679 665 746
United Kingdom 546 1038 665 709 741 955 877 692
EU Institutions 254 343 407 552 421 515 530 518
IDA 447 202 238 199 226 121 268 155
Global Fund 144 130 257 195 94 272 101 153

Source:-African Statistical Yearbook 2017, page 182   IDA (International Development Association)

የህወሓት መንግሥትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›የሃገሪቱን የፖለቲካ አቅጣጫ የዴሞክራሲ ስርዓት የሃዲድ መሥመር የጣሰና ወደ አንባገነን ስርዓት የጨለማ ሃዲድ የዘረጋ በመሆኑ የባህር ማዶ ልማት ትብብር  አጋር አገራቶች  ድጋፍ ለኢትዮጵያ ይቀንሳል ብሎም ይቆማል፡፡

የዲጅታል ቴክኖሎጅ ወጣት ትውልድ የዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት፣ በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመመስረት የብዙሃን ፓርቲዎች የውድድር ሥርዓት ዘርግቶ፣ በህዝብ ድምፅ አሸናፊው ሥልጣን የሚይዝበት የምርጫ ስርዓተ-አሥተዳደር መገንባት አለበት፡፡ በኢትዩጵያ የወያኔ ልማታዊ መንግሥት› ስም የወያኔ መንግሥታዊው ዘርፍ(ኢፈርት ሜቴክ፣ ኢዛና፣ ጥረት፣ ዲንሾ፣ ወንዶ ወዘተ) የግሉን ዘርፍ ኃብትና ሊሠራ የሚችለውን ኢንቨስትመንት ሥራ ሁሉ በመሻማት የግሉን ዘርፍ እድገትና ሚና በመላ ሃገሪቱ አጨናግፎታል፡፡ የወያኔ ኢፈርት ኢንተርፕራይዞች፡- በወያኔ ባለሥልጣኖች የሚተዳደሩ የሜቴክ ድርጅቶች የሙስና መፈልፈያዎች፣ የእውቀትና የብቃት ችግር የተንሠራፋባቸው፣ በሥልጣን በመጠቀም የግል ፍላጎት ተጠቃሚነትን የሚያስፋፉ፣እንዲሁም ከለላን የሚያበረታቱ፣ የፖለቲካና የዝምድና አሰራር የነገሰበቸው ናቸውና ለቀጣዮ ትውልድ የሥራ ዕድል ሊፈጥሩ አይችሉም፡፡  በሃገሪቱ 30 ሚሊዮን ወጣቶች ሥራ አጥ ናቸው፡፡ ወጣቶች በሃገራቸው ሠርተው መኖር መብት አላቸው፡፡ አድሎዊና ተመጣጣኝ ያልሆን የክልሎች እድገት ይወገድ!! በክልላችን የሚካሄድ የመሬት ቅርምት ይቁም!! በክልላችን ኃብት የዘረፉ ለፍርድ ይቅረቡ! ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለም! ወጣቶች የሚሉት ለዚህ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የኢህአዴግ መንግሥት ያወጣውን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ተቃወመ የህዝቡን የመሰብሰብና ሃሳብ መግለጽን መከልከልን፣ የዴሞክራሲዊ መብቶችን የመጸፍ፣ መናገር፣ መደራጀት፣ የሠላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማካሄድና መሰረታዊ መብቶች ክልከላ መፍትሄ አይሆንም በማለት ምክረ ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት በሃገሪቱ ዴሞክራሲን ማስፈን፣ የምጣኔ ሃብት እድገት ማስመዝገብ፣ ለህዝቡ ብልፅግና ሰላምና መረጋጋት ያመጣል እንጂ የስድስት ወር ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ማወጅ መፍትሄ አይሆንም በማለት ኮንነዋል፡፡ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አገራቶች የኢህአዴግ መንግሥት ያወጣውን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ› ተቃውመዋል፡፡

U.S. Embassy in Ethiopia

U.S. Embassy Statement on the Ethiopian Government’s Declared State of Emergency

Home Home | News & Events | U.S. Embassy Statement on the Ethiopian Government’s Declared State of Emergency

We strongly disagree with the Ethiopian government’s decision to impose a state of emergency that includes restrictions on fundamental rights such as assembly and expression.We recognize and share concerns expressed by the government about incidents of violence and loss of life, but firmly believe that the answer is greater freedom, not less. The challenges facing Ethiopia, whether to democratic reform, economic growth, or lasting stability, are best addressed through inclusive discourse and political processes, rather than through the imposition of restrictions. The declaration of a state of emergency undermines recent positive steps toward creating a more inclusive political space, including the release of thousands of prisoners. Restrictions on the ability of the Ethiopian people to express themselves peacefully sends a message that they are not being heard. We strongly urge the government to rethink this approach and identify other means to protect lives and property while preserving, and indeed expanding, the space for meaningful dialogue and political participation that can pave the way to a lasting democracy.

By U.S. Embassy Ethiopia | 17 February, 2018 | Topics: Fundamental Freedoms, Gender Issues, Human Rights, Press Releases | Tags: freedom of expression/Alert – U.S. Embassy Addis Ababa, Ethiopia ( Security Alert – U.S. Embassy Addis Ababa, Ethiopia (February 16, 2018)

Ethiopia crisis needs reforms not emergency rule – E.U. warns govt

Abdur Rahman Alfa Shaban

Ethiopia The European Union (E.U.) has cautioned Ethiopian government over the decision to impose a state of emergency on the heels of promised political reforms.In a statement released on Monday by E.U. spokesperson, Catherine Ray: “The announced reinstatement of the State of Emergency risks undermining this very objective. “It is therefore of the utmost importance that it should be as limited in time as possible and respectful of human rights and fundamental freedoms, notably those enshrined in the Ethiopian Constitution. Violence should also be avoided,” the statement said.It will be important for the new government to have the full capacity to pursue the positive reforms initiated by the Prime Minister to address the grievances of the population. Ethiopians criticize state of emergency #Ethiopia africanews reports https://t.co/pPAIJz9oCQ— Chika Oduah (chikaoduah) February 19, 2018

 

{2} ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት (Foreign Direct Investment Inflows) ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ለሃገሪቱን የኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያስከትለው ጉዳት በተመለከተ በሃገሪቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ይቀንሳል፡፡ ሰላም በሌለበት ሃገር የባህር ማዶ ኢንቨስተሮችን አይስብም፣ እንዲያውም ያፈሰሱትን ምዋለንዋይ ሸጠው ለመውጣት  ይገደዳሉ፡፡ በሃገራችን የኢኮኖሚ ነፃነት ከሚገለፅባቸው ዋና ዋና መርሆዎች ውስጥ አንዱንም አታሞላ፡፡ አንደኛው የህግ የበላይነት፣የፍትህ ሥርዓት መከበር፣የንብረት ባለቤትነት መብት መከበር፣ የመንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ያለው አቅም የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች የህግ ሉዓላዊነት ያለበት ሃገር መዋለ-ንዋያቸውን አፍሰው በነፃነት ኃብት ማፍራት ይሻሉ፡፡ ህግና ፍትህ ባለበት ሃገር ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት ከአመት አመት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በኢትዩጵያ ህግ የለም፣ ፍትህና ርትህ አይሠራም፣ የዜጎች ንብረት የማፍራት መብት የለም፡፡ በኢትዩጵያ የህወሓት መንግሥት በሞኖፖል የተያዙ ንብረቶችና ኃብቶች መካከል፡-በሃገሪቱ የመሬት ኃብት የህወሓት መንግሥት በመሆኑ የግብርና፣የማኑፋክቸሪንግና አገልግሎት ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ እድገቱ የቀጨጨ ለመሆን በቅቶል፡፡ ህዝባችን የመሬት ኃብት ንብረት የመያዝ መብትና ነፃነት ስለሌለው በርሃብ አለንጋ ይሰቃያል፡፡ ህዝቡን መመገብ የማይችል መንግሥት ህዝቡን መግዛት አይችልም፡፡ በሃገሪቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት በ2008እኤአ (109 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2009እኤአ (211 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2010እኤአ (288 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2011እኤአ (627 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2012እኤአ (279 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2013እኤአ (1281 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2014እኤአ (2132 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2015እኤአ (2168 ቢሊዮን ዶላር)፣2016እኤአ (አልተገለጸም)፣ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ነበር፡፡‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንት ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት በጣም ይቀንሳል፡፡››

Net Foreign Direct Investment Inflows FDII

Year 2008 2009 2010 2011 2012 2013 2014 2015 2016
FDII US$ (Million) 109 221 288 627 279 1,281 2,132 2,168

Source:-African Statistical Yearbook 2017, page 182

{3} የባህር ማዶ ጎብኝዎችንና በኢትዮጵያ ቁጥር ይቀንሳል በዚህም ምክንያት ከቱሪስቶች የሚገኝ ገቢ ያሽቆለቁላል፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ይቀንሳል፣

በ2008 እኤአ ኢትዩጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 383 ሽህ  ሲሆን ከዘርፍ 355400 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) 10.4 በመቶ እንዲሁም ለሥራ ዕድል 6.3 በመቶ አበርክቶ ነበር፡፡ በ2014 እኤአ 770 ሽህ ጎብኝዎች ወደ ሃገራችን መጥተው ነበር፣ በ2015እኤአ 717 ሽህ ቱሪስቶች መጡ (በ60 ሽህ ቀነሰ) በ2016እኤአ 491 ሽህ ሃገር ጎብኝዋች መጥተው ነበር(279 ሽህ ጎብኝዎች ቁጥር ቀነሰ)፡፡ ከ2008 እስከ 2009ዓ/ም  ወያኔ  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ› አውጆ የነበረበት ዓማታት መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ ቀሪውን ከሠንጠረዥ መረጃውን ይመርምሩ፡፡

VII TOURISM AND INFRASTRUCTURE

Year 2008 2009 2010 2011 2012 2013 2014 2015 2016
International tourist arrivals (thousands) 383 427 468 523 597 681 770 717 491
Tourism receipts US$ (thousand) 355400 316500 519200 750700 604300 661688 730436 763803 789474
Total contribution to GDP (%) 10.4 9.3 11.9 13.1 10.2 9.9 9.6 9.0 8.3
Total contribution to Employment (%) 6.3 5.8 7.2 7.9 6.6 6.4 5.8 5.7 5.2

Source:-African Statistical Yearbook 2017, page 180

  • በ2014 እኤአ ኢትዩጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 770 ሽህ ሲሆን ከዘርፍ 730436 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) 9.6 በመቶ እንዲሁም ለሥራ ዕድል 5.8 በመቶ አበርክቶ ነበር፡፡ በ2015አና 2016እኤአ የቱሪስቶች ቁጥር መቀነሱን፣የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) መቶኛ እንዲሁም ለሥራ ዕድል መቶኛ ቀንሶል ይታያል፡፡ የተገኘው ገቢ መጨመሩን ግን ያሳያል ከሠንጠረዡ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከ2008ዓ/ም እስከ 2010ዓ/ም በተቀሰቀሰው የኦሮሚያ ህዝብ የአንገዛም እንቢተኝነት ትግልና የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ምክንያት ወያኔ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ምክንት የቱሪዝም ዘርፍ በቱሪስቶች ቁጥር መቀነስና  የዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) መቶኛ እንዲሁም ለሥራ ዕድል መቶኛ ቀንሶል ይታይ ነበር፡፡ ከዚህ መረጃ በመነሳት የካቲት 9 ቀን 2010 የታወጀው ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ያሽመደምደዋል፣ የሆቴሎች ገቢ ይቀንሳል፣ የቱሪስት አስጎብኝ ድርጅቶች ገቢ ይቀንሳል፣ የውጪ ምንዛሪ ገቢ ይወድቃል፡፡
  • ‹‹በአሁኑ ወቅት የቱሪስት ፍሰት በአንድ ወር በአማካይ እስከ 88 ሺ እንደሚደርስምና የቆይታ ጊዜውም እስከ 16 ቀናት መሆኑን አቶ ገዛህኝ አባተ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አመልክተዋል፡፡ በጉብኝት፣በንግድ፣በኤግዚቪሽን፣ በኮንፍረንስ፣ዘመድ ጥየቃና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ አገሪ የሚመጡ የውጭ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ለዘርፉ ማደግ አስተዋፅኦ ማድገጉን ጠቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በአገልግትና በተለያየ የግንባታ ደረጃ  ላይ የሚገኙ ደረጃቸውን የጠበቁ 700 ሆቴሌች እና 460 አስጎብኝ ድርጅቶች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡›› ‹‹ኢትዩጵያ በጎብኒዎች ቁጥር ከአፍሪካ 18ኛ ከዓለም 121ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡!!!››
  • ከአፍሪካ አገራቶች ውስጥ 18 ደረጃ ላይ የምትገኝና ገና አንድ ሚሊዩን ጎብኝዎች ያላስተናገደች ሃገረ-ኢትዩጵያ በቱሪዝም እንዴት 5ኛ ደረጃ ለመድረስ ይቻላታል፡፡ ወያኔ ‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› አውጆ ዜጎቹን በመግደልና በማሰር በአፍሪካ 1ኛ ደረጃ ላይ እያለ!!!

በ2008፣በ2009ና 2010ዓ/ም በኦሮሚያ ህዝባዊ እንቢተኛነትና በአማራ ህዝባዊ ተጋድሎ የግብርና የታክስ ገቢ ቀንሶል፣ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ምክንት ለመከላከያ  ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ኃይል፣ ሚሊሽያ ወዘተ ከመደበኛ በጀት ሌላ ከፍተኛ ወጭ ያስከትላል፡፡ በ2010እኤአ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አስከትሎል፡፡ ከህዝብ ታክስ መሰብሰብ ያልቻለ መንግሥት በህዝብ የተጠላ መንግሥት ነው፡፡ የስልጣን እድሜውም አጭር ነው፡፡ ህወሓት ከህዝብ ግብር መሰብሰብ ካልቻለ ለመከላከያ ሠራዊቱ፣ ለፖሊስ፣ ለደህንነቱ፣ ለፊዴራልና ለክልሎች ለሲቪል ሠራተኞችና አስተዳደር የሚከፈል ደሞዝ ስለማይኖር ከሥልጣን መንበሩ ይወገዳል፡፡ ወያኔ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ዳግም በማወጅ በጉልበት ግብር ሊሰበስብ ይፈልጋል፣ የህዝብ ልጆች እየገደለ መግዛት ይፈልጋል፣ በሙስናና በኮንትሮባንድ ንግድ የከበሩ አይነኬ የጦር መኮንኖች በመላ ሃገሪቱ ህገወጥ የድንበር ዘለል ንግድ በመዘርጋት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ አውድመዋል፡፡ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የህዝቡን በነጻነት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት ኢኮኖሚ ነፃነት ያሳጣዋል፡፡ የወያኔ ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ንግድን በወያኔ መንግሥት ሠራዊት እየተጠበቁ እንዲነግዱ ሲያመጫች የግል ዘርፉን ንግድ እንቅስቃሴ እንዲታሸግ፣ የግብር ጫናና አድሎ በኮማንድ ፖስቱ ይፈፀምባቸዋል፡፡ በዚህም የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ፣ የንግድ መዛባትን በመፍጠር፣ ውድድርን በማክሰም፣ በመንግሥት እጅና ጥበቃ ከውድድር ውጭ ሆነው የሚተዳደሩ ድርጅቶች ይፈጠራሉ፡፡

ከ2008 እስከ 2009/2010ዓ/ም በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በተነሳ ህዝባዊ አመፅ የሃገር ውስጥ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ንብረት የሆኑ ፋብሪካዎችና እርሻዎች መውደም ምክንያት የታቀደው አልተሞላም፡፡‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የውጭ ንግድ ገቢ አሽቆለቆለ፣ በአንጻሩ የገቢ ንግድ ወጪ በማደጉ የንግድ ሚዛኑ ተናግቶል፡፡ በዚህም የተነሳ ያልተረጋጋ የብር ምንዛሪ ተመንና የውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት፣ የመንግሥትና የልማት ድርጅቶች በዕዳ ክፍያ ጫና ተከስቶል፡፡ በአጠቃላይ  የአገሪቱ የፋይናንስና የባንክ ኢንዱስትሪው ልማቱ የሚጠይቀውን ፋይናንስ የማቅረብ ብቃት ወድቆ ነበር፡፡ በሃገሪቱ የፋይናሻል ዘርፍ ውድቀትና ኪሣራ ደርሶባቸዋል፡፡ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ የዋጋ ግሽበቱንና የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፣ የውጪ ንግድ ገቢ በድርቅ ተመቶል፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በጣም ተባብሶል፣ በእጥረቱ ምክንያት የኮንስትራክሽን ስራዎች በአብዛኛው ተቆርጠዋል፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች ቆመዋል፣ በሃገሪቱ በታወጀው ‹አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ› የተነሳ በባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ሽሽት የተነሳ፣ ይደረግ የነበረው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት አሽቆልቁሎል፣ የሆቴልና ቱሪዝም ገቢም ይነጥፋል፡፡ ከዚህ ባለመማር ወያኔ ዳግም ‹አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ› አውጆል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በርሃብ፣በድህነት፣በበሽታ፣በስደትና በጦርነት አዙሪት ቀለበት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በሃገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት አለመኖር፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አለማበብ፣ የመልካም መሪዎችና መልካም አስተዳደር እጦት፣ የስራ አጦች ብዛት፣ ገበያ መር የኃብት አጠቃቀም አለመኖር፣ የረዥም ግዜ  ኢንቨስትመንት እቅድ አለመኖር፣ የተትረፈረፈ ምርቶች ለውጭ ንግድ አለማምረት፣ የውጭ ምንዛሪ እጦት እንዲሁም የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚክ ስርዓት ዘላቂ ያልሆነ፣ ፊሲካልና ከዓለም አቀፍ ንግድ የውጭና የገቢ ንግድ የተዛባ ሚዛን፣  የንግድ ኪሳራ መሆን በችግር ቀለበት ውስጥ እንድትሽከረከር ያደርጋታል፡፡ይህን ችግራችንን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› እና ኮማንድ ፖስቱ አይፈቱትም፣ ከመካላከያ ሠራዊት መደበኛ የደሞዝ፣ የቀን አበል፣የነትራንስፖርትና የነዳጅ ወጪ በጀት መጨመር ሌላ ለሃገሪቱ ኃብት አይጨምርም፡፡  ከመካላከያ ሠራዊት በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ዘርፍ አምራች ሳይሆን እንደ ጥገኛ ተሃዋሲያን ሆኖ አምራች ኃይሉን የሚጣባ ወታደራዊ ዘርፍ ነው፡፡ ከግብርናው ዘርፍ አምራቹ ገበሬና ከማኑፋክቸር ዘርፍ ከላብአደር አምራች ከሚሠበሰብ ገቢ መንግሥት የግብርና የታክስ ቀረጥ ሰብስቦ ደሞዝ የሚከፈላቸው ናቸው፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ወደ ሌላ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››  መሸጋገር ኢትዩጵያ ከደካማ መንግስትነት (weak states)፣ ወደ ሚሰበርና የሚፈረካከስ ሃገር (fragile states)፣ብሎም ወደ ወደቀች መንግስት  (failed states) ጎራ የመቀላቀላችን ግዜ  በእርስ በእርስ ጦርነት እየተፋጠነ መምጣቱ  አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ የወያኔ የጥላቻ ፖለቲካ የሚከሰተው የዘር ፍጅት (የጀኖሳይድ) አዙሪት ቀለበት ውስጥ  ለመውጣት፣ ከዚህ ከማያባራ የህዝብ አመፅ፣ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ለአንዴና ለዘለቄታው ለመውጣት፣ ብሄራዊ እርቅና የሰላም ጥሪ ውይይትና የዴሞክራሲ ስርዓት ሀ፣ሁ ለመገንባት የሽግግር መንግሥት መመሥረት ግዜው አሁን ነው፡፡ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››  እንዲነሳ ህዝባዊው አመፅ በኢትዮጵያ ምድር ተቀጣጥሎ ወያኔ ይወገዳል፣ እንደ ግብፅ፣ ቱኒዚያ፣ ሊቢያ ህዝባዊ ትግል፣ ጭቁን መከላከያ ሠራዊት ከህዝብ ጋር ወግኖ ታሪክ እንደሠራ የእኛም ሠራዊት አፈሙዙን ወደ ገዥዎቹ አዙሮ ህዝባዊውን ትግል ይቀላቀላል፡፡

‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በህዝብ ትግል ይነሳል!!!

ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለም!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.