እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞና ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ከእስር ተፈቱ (ሙሉቀን ተስፋው)

“መፈንቅለ መንግሥት አድርጋችኋል” ተብለው ታስረው የነበሩ እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞና ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ከእስር ተፈቱ፤

 • ጀነራል ተፈራ ማሞ፣
 • ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣
 • ኮለኔል ደምሰው አንተነህና
 • ኮለኔል አለሙ ጌትነት
 • ኮለኔል ጌታቸው ብርሌ፣
 • ኮለኔል ፋንታሁን ሙሀባ፣
 • ኮለኔል አበረ አሰፋ፣
 • ኮለኔል ሰለሞን አሻግሬ፣
 • ሻምበል ተመሰገን ባይለየኝ
 • ዋና ሳጅን የሸዋስም
 • ኢንጂነር መንግስቱ አበበ፣
 • ሻለቃ መኮንን ወርቁ፣
 • ሻለቃ መሰከረ ካሳ፣
 • ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ፣
 • ኢኒስፔክተር አመራር ባያብል፣
 • ዋና ሳጅን ጎበና በላይ፣
 • ሳጅን ይበልጣል ብራሃኑ

ከ9 ዓመት እስር በኌላ ዛሬ ተፈተዋል።

************

አቻምየለህ ታምሩ ደግሞ ከእስር ስለተፈቱት የጦር መኮነኞች የሚከተለውን ጽፏል

ኮሎኔል ደምሰው አንተነህ በፋሽስት ወያኔ ማሰቃያ ቤት ዘጠኝ የመከራ አመታትን ከማሳለፊ በፊትና በኋላ፤

«መፈንቅለ መንግሥት አድርጋችኋል» ተብለው በፋሽስት ወያኔ ጠባብ የማሰቃያ ቤት ውስጥ ለዘጠኝ አመታት ያህል ሲሰቃዩ የነበሩት ጀግኖቹ ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣ ኢንጂነር መንግሥቱ አበበ፣ ኮሎኔል አበረ አሰፋ፣ ኮሎኔል ሰለሞን አሻግሬ፣ ሻለቃ መኮንን ወርቁ፣ ሻለቃ መሰከረ ካሳ፣ ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ፣ ኢኒስፔክተር አመራር ባያብል፣ ዋና ሳጅን ጎበና በላይና ሳጅን ይበልጣል ብራሃኑ በአሁኑ ሰዓት ከነበሩበት የፋሽስት ወያኔ የዝዋይ ጠባብ የማሰቃያ ቤት ወጥተው ሁላችን ወደታሰርንባት ሰፊዋ እስር ቤት ኢትዮጵያ በመዛወር ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሊቀላቀሉ ወደ መዲናችን አዲስ አበባ ጉዞ ጀምረዋል!

ውድ ጀግኖቻችን እንኳን እንደሁላችንም በእኩል አብራችሁ ለመታሰር ወደ ሰፊዋ እስር ቤት ወደ ኢትዮጵያ በመውጣት ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እናንተን ለማየት ወደ ዝዋይ እየተመላለሱ ሲሰቃዩ ከከረሙ ውድ ቤተሰቦቻችሁ ጋር ለመቀላቀል አበቃችሁ!

______________

ኮለኔል ጌታቸው ብርሌ በማዕረግ ኮሎኔል ቢሆንም ባለሞያ ስለሆነ ወያኔ የጀኔራልነት ማዕረግ ካደላቸው የትግራይ የገበሬ ወታደሮች እኩል ብርጌድ ይሰራ የነበራ ተወዳጅ ኮሌኔል ነበር።

ቀደም ሲል ያወሳነው «ጀብደኛው ተዋጊ» ኮለኔል አለሙ ጌትነት ወያኔ ማሰቃያ ቤት ከመግባቱ በፊት የድሬደዋ አየር ኃይል ምድብን በምክትል አዛዥነት ያገለግል የነበረ መኮነን ነበር።

አማራ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ማሕበረሰብ «ትንሽ ሥጋ እንደ መርፌ ትወጋ»፣ «ምንም ብጠላው በወንድሜ ግንባር ደም አልይበት» በሚለው የአባቶቻችን አባባል የሚኖር ብቻ ሳይሆን በቤተሰባዊ ግንኙነቱ ጠባቃና በተለይ ደግሞ የወዳጅ ዘመድ ሞት፣ እስርና ህመም በኖረ ቁጥር የግል ጠብ ቢኖር እንኳ ያንን በመርሳት የታትመመን የሚጠይቅ፣ የተጎዳን የሚያጽናና፣ የታሰረ የሚጎበኝና የወገን ሀዘን ሁሉ ግድ የሚለው ሕዝብ ነው። ይህንን ለመናገር የፈለግሁበት ምክንያት ስለ ኮለኔል ፋንታሁን ሙሀባና ፋሽስት ወያኔ ከሰሞኑ ምክትል ጠቅላይ ኢታማጁርና የአየር ኃይል አዛዥ አድርጎ ስላስቀመጠው ስለ ሙሉ «ጀኔራሉ» ስለ አደም መሃመድ ላወራችሁ ነው።

ኮለኔል ፋንታሁን ሙሀባ ባለፈው ሰሞን ፋሽስት ወያኔ ምክትል ጠቅላይ ኢታማጁርና የአየር ኃይል አዛዥ አድርጎ ካስቀመጠውና ሙሉ ጀኔራልነትን ካደለው ከአደም መሃመድ ጋር የእህትና የወንድም ልጆች ናቸው። ሆኖም ግን አደም መሃመድ ኮለኔል ፋንታሁን ሙሀባ ዘጠኝ አመታት ሙሉ በእስር ሲሰቃይ አንድ ቀን እንኳ ጠይቆት አያውቅም። ፋሽስት ወያኔ «የአማራን ተዋጽኦ» ለመጠበቅ ሲል ሙሉ ጀኔራልና ምክትል ጠቅላይ ኢታማጁር አድርጎ የሰየመውና የአማራን ተዋጽኦ የሸፈነው ሙሉው ጀኔራል አደም መሃመድ ይህንን ቅንጣት ታህል የአማራ ስነ ልቦናና ጠባይ የሌለውን ሆዳም የወያኔ ካድሬ ነው።

ሆዳሙ አገልጋይ አደም መሃመድ ለሚያውቀው የአክስቱ ልጅ ልጅና ለአብሮ አደግ ወንድሙ ለኮለኔል ፋንታሁን ሙሀባ ያልሆነ ለማያውቀው አማራ ሊሆን አይችልም። እንግዲህ ፋሽስት ወያኔ የአማራ ወኪል አድርጎ አድርጎ የሚሾማቸው አይደለም ለማያውቁት አማራ ይቅርና ለሚያውቋቸው የስጋ ዘመዶቻቸው እንኳ ደንታ የሌላቸውን እንደ አደም መሃመድ አይነት ጭድ የሚበሉ አጋሰሶችን ነው።
ምንጭ ፡ ወልቃይት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.