የመገንጠል ምናባዊ ወጎች – አስራት አብርሃም

አንድ!

አስራት አብርሃም
አስራት አብርሃም

እስማኤል ዘ ጅግጅጋ፦ ጓዶች ኧረ አማራ ቀድሞን ሊገነጠል ነው፤ ጉድ መሆናችን እኮ ነው፤ እንዲህ ከሆነ ምን ብለን ልንገነጠል ነው?!

ጃዌ አባ መላ፦ ከመገንጠልማ አንቀርም፤ ባይሆን የምንገነጠልበት አጀንዳ ይቀየራል እንጂ!

እስማኤል ዘ ጅግጅጋ፦  ምን ብለን ነው የምንቀይረው?!

ጃዌ አባ መላ፦ ካለ አማራ መኖር ስለማንችል የመገንጠል መብታችን ይከበር ብለን ነዋ!

ሁለት!   

አቤ ዘ ሽሮሜዳ ፦ይህን ጉድ ሰሙ ፕሮፌሰር፥ አማራም ሊገነጠል ነው!

ፕሮፌሰር፦ “የሌለ ነገር እንዴት ይገነጠላል፤ ለመገንጠል እኮ መጀመሪያ ራሱ መኖር አለበት።”

እኔ፦ የዚች ቅኔ የዴካርትን ፍልስፍና ካነበብኩ በኋላ ነው በቅርቡ በደንብ የገባችኝ፤ ዴካርት “እንኳን ሌላውን ራሴ ለመኖሬም እርግጠኛ አይደለሁም” ብሎ፤ ከዚያ ነው “እኔ አለሁ ወይስ የለሁም?” በማለት ምርምሩን የጀመረው፤ ፈላስፋም የሆነው። እናም የፕሮፌሰርን አባባል እንዲህ ተረዳሁት፤ ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርማ ኖሮ እንዲህ መጫወቻ አይሆንም ነበር!

 ሶስት!       

ሀጎስ ዘ ደደቢት፦ “እሰይ፣ እሰይ ባርባ አመቴ፥ ስለቴ ሰመረ

ራዕዬ ተሳካ፥ ሁሉም መገንጠል ጀመረ”

ገሪሽ ወዲ አስመራ፦ ምን ተገኘ?

ሀጎስ ዘ ደደቢት፦ አማራ የመገንጠልን ጠቃሚነት ተረድቶ ሊገነጠል ነው!

ገሪሽ ወዲ አስመራ፦ ታዲያ ይሄ ምን ያመለክታል?

ሀጎስ ዘ ደደቢት፦ ከትምክህት ወደ ጠባብነት የተሸጋገረበት ሁኔታ ነው ያለው!

ገብሪሽ ወዲ አስመራ፦ እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ?

ሀጎስ ዘ ደደቢት፦ ዋይ ባለ ራዕዩ መሪያችን ቢኖር ሳይንሳዊ ትንታኔ ይሰጥበት ነበር፤ ምን ያደርጋል ተሰዋ! እንግዲህ ብፃይ በረከት እንዳለው ከመቶ አመት በኋላ ሌላ ባለራዕይ ስለሚወለድ እሱን በትዕግስት መጠበቅ ነው!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.