ደኢሕዴን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ባጠናቀቀው ስብሰባው አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩን አቶ ሲራጅ ፈጌሳን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡

አዲሱ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ሽፈራው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ፓርቲው ለሳምንታት ያደረገውን ስብሰባ አዳዲስ ሊቀመናብርት በመምረጥ አጠናቋል፡፡

በቅርቡ ከኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢሕአዴግ) ሊቀመንበርነት ለመነሳት ጥያቄ ባቀረቡት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምትክ አምባሳደር ተሾመ ቶጋን የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንዲሆኑ መርጧቸዋል፡፡

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ መቼ ሊደረግ ይችላል ተብለው የተጠየቁት አቶ ሽፈራው፣ የስብሰባው ቀን ገና  እንዳልተወሰነ አስታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.