ኦህዴድ ለአባዱላ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ፤ የአባዱላና የበረከት ፍቅርና ሌሎችም (ከሚኪ አማራ)

አባዱላ ስልጣን ከለቀቀ በኋላ ምክንያቱን ሳይናገር እንደገና እንደተመለሰ እናዉቃለን፡፡ ህወሀት አባዱላን አንተ ኦህዴድ ዉስጥ ያለዉን እብደት አስተካክል እንጅ ብትፈልግ ጠቅላይ ሚኒስቴር አለያም የመከላከያ ኢታማዘዦር ትሆናለህ ተብሎ ቃል ተገብቶለት እንደተመለሰ ታዉቋል፡፡ በረከትም ቢሆን አንተ ጥለህ ወተህ ድርጅቱን ማን ሊረከብ ነዉ፡ ተመለስና ነገሮችን አስተካክል ያስቀየምንህን ነገርም እናስተካክላለን አግባብም አልነበረም ተብሎ ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት ህዋሀት ሁለቱን ሰወች ነጻነት በመስጠት የድርጅቱን የቀድሞ ቁመና አንዲመልሱና እነሱም በሚፈልጉት ቦታ ላይ መስራት እንደሚችሉ ተስማምቶ ነዉ የመለሳቸዉ፡፡ትናንት እንዳልኩት ሀመድን የገፉት አባዱላና በረከት ናቸዉ፡፡

 

አባዱላና በረከት በህይወታቸዉ ተስማምተዉ አያዉቁም፡፡ አሁን ግን አባዱላና በረከት እፍ ያሉ ጓደኞች ሁነዉ አንድ ቢሮ ዉስጥ ቁጭ ብለዉ ነገር ሲቀጥሉና ሲበጥሱ ነዉ የሚዉሉት፡፡ እስካሁን ባለዉ ሁኔታ ከህወሃት ባብዛኛዉ ከሁለቱ ሰወች ጋር እየሰራ ያለዉ ጌታቸዉ አሰፋ ነዉ፡፡ ለወትሮዉ አባይ ጸሃየ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከሁለቱ ሰወች ጋር በስፋት እየሰራ ያለዉ ጌታቸዉ ነዉ፡፡

አባዱላ ሙሉ ለሙሉ የዶክተር አብይና የለማ ተቃዋሚ በመሆን ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ በነ ለማ የተገፉትንና የድሮ የራሱን ሰወች በዙሪያዉ በማደራጀት የእነ ለማ ቡድንን ለማጥቃት በመንቀሳቀሱ ኦህዴድ ከዚህ ስራዉ እንዲቆጠብ ማስጥንቀቂያ ሰቶታል፡፡ አባዱላ የነ ለማን ቲም በሁለት መንገድ እያጠቃ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ አንደኛ ዉጪ ካለዉ ከእነጃዋር ቡድን ጋር በመገናኘት የእነ ለማን ቡድን settle እንዳያደርግ የማድረግ ስራ በመስራት፡፡ አባዱላ ገመዳን ከእነ ጃዋር ጋር ያገናኛል ተብለዉ ከተጠቀሱት ሰወችም የኦሮሞ ባለሃብቶች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ የአባዱላ ጓደኛና የሪፍት ቫሊ ባለቤት አቶ ድንቁ የሚባል ሰዉየ ነዉ፡፡ ሁለተኛ አባዱላ ከጌታቸዉ አሰፋ ጋር በመሆን የዶ/ር አብይን ምርጫ ላይ እንዳይቀርብ የተለያዩ ስራወች በመስራት ነዉ፡፡ አባ ዱላ ጠቅላይ ሚኒስቴርነቱን እጅግ እንደሚፈልገዉ ህወሃትም እንደሚደግፈዉ ተናግሯል፡፡ አባዱላ ይሄን ሃሳብ በተደጋጋሚ ለእነ ለማ በማቅረቡና የዶ/ር አብይን ተወዳዳሪ ሆኖ መቅረብ ስለተቃወመ ማስጠንቀቂያ ተሰቶታል፡፡ ህወሃት ከአንድ ድርጅት እስከተጠቆመ ድረስ ሁለትም ሶስትም ሰዉ ሊወዳደር ይችላል የሚል መከራከሪያ በማምጣቱ ኦህዴድ ግን ድርጅቱ ያመነበት አንድ ተወዳዳሪ ያቀርባል ከዛ ዉጪ ሁለት ሰዉ ከአንድ ድርጅት አቅርቡ የምትሉን ከሆነ ዉድድሩ ላይ አንሳተፍም እረግጠንም እንወጣለን ብለዉ አስፈራርተዋል፡፡

የሰሞኑ ኦህዴድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተቀብሏል የተባለዉም በዋነኛነት አባዱላና ወርቅነህ ገበየዉ በመስማማታቸዉ ነዉ፡፡ የኦህዴድ የፓርላማ አባላትንም አባዱላ ያሳምናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ህወሃት ለማ መገርሳ እንዲወዳደር ፍላጎት የነበረዉ ሲሆን፡፡ እንደተባለዉ ከሆነ እቅዱ የነበረዉ መጨረሻ ላይ ለማ የፓርላማ አባል አይደለም በማለት መንገዱን ለአባዱላ ማመቻቸት ነበር፡፡ይሄም ሁሉ ሳይሆን አባዱላም ጠቅላይ ሚኒስቴር የመሆን ፍላጎቱን ለኦህዴድ አስረድቷል፡፡ ይሄን ጥያቄና ታክቲክ ሲረዱትና እነ ለማ ችግር ዉስጥ እንደገቡ ሲያዉቁት በፍጥነት የማስተካከል እርምጃ በመዉሰድና በገሃድ ዶ/ር አብይን endorse በማድረግ የመቅደም ስልት ተጫዉተዋል፡፡ ነገር ግን አባዱላ በበኩሉ ይሄን ስለተረዳ ዉጪ ላሉት የኦሮሞ አክቲቪስቶች (ለነ ጃዋር) ለማ ላይ የግልበጣ ሴራ ተሰርቶበታል ብለዉ መረጃ ስላቀበሉ እነ ጃዋርም፤ አባዱላም፤አሰፋ ጌታቸዉም ደ/ር አብይን እየቀጠቀጡት ይገኛሉ፡፡ ምናልባትም እነ ጃዋር የአባዱላን መሸብለል አላወቁምና የእነ አባዱላን መረጃ አምነዉ ተቀብለዋል አለያም ማንም ፖለቲከኛ እንደሚያደርገዉ የእነ ጃዋር ቡድንም politically relevant ሆኖ መቆየት ስለሚፈልግ ለማ እንደማይሆን እያወቁ ነገር ግን ህዝቡን በዛ መንገድ frame በማድረግ ቀጣይ የሚመጣዉን ጠቅላይ ሚኒስቴር ብለን ነበር በማለት already ያላቸዉን የፖለቲካል ካፒታል በመጠቀም ተጽእኗቸዉን ማስቀጠል ነዉ፡፡

ለማንኛዉም አሁን ባለዉ ሁኔታ ህወሃት የኢሃዴግ ሊቀመንበር ለመሆን መጀመሪያ የድርጅትህ ሊቀመንበር መሆን አለብህ የሚለዉን ሊተወዉ የፈለገ ይመስላል፡፡ በዚህም ምክንያት እስካሁን ድርስ እነ አባዱላም ሲራጅ ፈጌሳም ዉድድሩ ዉስጥ አሉበት ማለት ነዉ፡፡በነገራችን ላይ ለህወሃት የሚጠቅም ከሆነ የማይጣስ ህግ የለም ፓርላማ፤ የኮሚቴ አባል ምናምን የሚለዉ አይሰራም፡፡ለደብረጺወን የተደረገዉን ማየት ነዉ፡፡ በመሆኑም ነገሩ በዶ/ር አብይና በደመቀ መኮነን ወይም ሽጉጤ ብቻ ላይ አይደለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አድርገዉት የማያዉቁትን በሚስጥርና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ነዉ ምርጫዉ የሚካሄደዉ ብሎ ትናንት በረከት መግለጫ ሲሰጥ ነበር፡፡ ይሄ የሚያሳየዉ በድርጅቱ ዉስጥ ማን ይሁን ለሚለዉ ስምምነት ላይ አለመድረሱና ወደ ምርጫ መሄዱ ሽጉጤን ወይንም ደመቀን የሚጠቅም ሲሆን ዶ/ር አብይ ያለምንም ጥርጥር ተሸናፊ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ ሌላዉ አስገራሚ ነገር በረከት የሚኒስቴርነት ቦታ ሊሰጠዉ ይችላል፡፡ትናንት በረከት ኢሃዴግን ከበስተጀርባ ሁኖ ሙሉ ለሙሉ ተረክቧል ብያችሁ ነበር፡፡ ወዲያዉ ከሰአት በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ መስጠቱ ይሄን ያጠናክራል፡፡

በመጨረሻም ኢህአዴግ ሪፎርም የማድረግ ፍላጎት ሳይሆን በቀድሞዉ አካሄዱ ድርጅቶችን እንደገና በመቆጣጠር ስልጣኑን ማጠናከር ነዉ የፈለገዉ፡፡ በዚህም መሰረት ደህዴን የድሮወቹን የበሰበሱትን ሰወች እንደገና አመራር አድርጎ መጣ፡፡ ብአዴንም ያዉ ጥርሳቸዉ የወላለቁት ሰወች ናቸዉ የተመለሱት በረከትን ጨምሮ፡፡ ህወሃትም ጭራሽ ለመሞት ሁለት አመት የቀራቸዉን እነ አቦይ ስብሃት ሞንጆሪኖ ምናምን የሚባሉ የድናጋይ ዘመን ሰወችን ይዞ ተመልሷል፡፡ ኦህዴድ ነዉ እንግዲህ ትንሽ ተሻለ የሚባለዉ የነበር ያዉ አባዱላን እንደገና በመመለስ ቡድን ለማ የሚባለዉን የማፍረስ ወይም infiltrate የማድረግ ስራ ተሰቶት ጀምሮታል፡፡ ይሄ ሁሉ ታልፎ ዶ/ር አብይ ቢመረጥም እንኳን አይደለም ሪፎርም ሊያካሂድ ይቅርና የለበሰዉን ልብስ ሳይቀይር 2012 ላይ ህወሃት ትቀይረዋለች፡፡

እና ወገኔ በአባዱላ እስካሁን እየተገረምኩና እየተደመምኩ ነዉ ያለሁት፡፡ ድሮም ምርኮኛ እንኳን ሌላዉን እራሱን ነጻ አያወጣም ያለዉ ማን ነበር፡፡ፖለቲካ ምን አይነት ቆሻሻ ነገር እንደሆነ ተረድቻለዉ፡፡ ህወሃትም እንደ አህያ ዱላ የሚወድ ድርጅት በመሆኑ በዱላ ካልሆነ በሌላ ነገር እንደማይነቀሳቀስ ማወቀ አለብን፡፡

መልካም ቀን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.